
23/07/2024
#በወርሃ ነሃሴ 1945
ጃፓን ላይ ምን ሆነ.
=========================
ጊዜው ዓለም በ2ተኛው የአለም ጦርነት የተዘፈቀችበት ነበር።የጦርነቱ አውድማ ሆና የከረመችው አውሮፓ በጀርመን መሸነፍ ምክንያት ቀድማ እረፍት አግኝታለች ነበር።
ከወደ እሲያ አህጉር ግን የቀጠናው አውራ ነኝ የምትለዋ ጃፖን ማን አቅብጦት እኔን ሊነካ እያለች መንቀባረር ከጀመረች ሠነባብታ ነበር።ይባሱን ብላ በጦርነቱ ገለልተኛ ነኝ የምትለውን አሜሪካን ተነኮሰች.
በፐርሀርቨር(የአሜሪካ የባህር ሃይል ማለት ነው) 3 ሺ የባህር ሃይል አባሎችዋንና መርከቦችዋን 1 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አንዳልነበሩ የሆኑባት አሜሪካ 2ተኛውን የዓለም ጦርነት በይፋ ተቀላቀለች ።
#ከዚህ በሁዋላ የሆነው አንዲህ ነው።
ሠማይ ከተወጠረ ምድር ከተዘረጋ ጀምሮ አይን አይቶት ጆሮ ሠምቶት ያውቃል በማይባል የመከራ ማዕት ተቀጠቀጠች ከተሞቹዋ ሄሮሽማና ናጋሳኪ በአቶሚክ ቦንብ የውስጥ አፈራቸው ሽቅብ የላይኛው ቆጥኛቸውና ህንፃቸው ቁልቁል ተገለባበጡ.
አሜሪካ ጃፓን ላይ የበረታ የበቀል ክንዱዋን ዘረገች:
#ጃፓን በሁሉም የጦር ግምባሮች የሽንፈት ኮሶ ተግታ እጁዋን ሰጠች . 2ተኛው የአለም ጦርነትም በእሲያ ምድር ተጠናቀቀ።
✍️ሀገር በመሪዎች ትወከላለች የመሪዎችዋ ውሳኔ ሀገርን ያለማል ወይም ያፈርሳል ጃፓንም ላይ የሆነው ይሄ ነው።
የመሬዎችዋ ውሳኔ ከማይችሉት ሀይል ጋ ተጋጭተው 2 ከተሞችዋን እንዳልነበሩ ሆነዋል።
https://t.me/t_g16
#መቆያ(Mekoya)