08/06/2026
ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ የለውጥ እና የብልጽግና ምዕራፍ ላይ ትገኛለች!?
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በታሪኳ ውስጥ ልዩና አስደናቂ የሆነ የለውጥ ምዕራፍ እያሳለፈች ትገኛለች። የሁለንተናዊው የልማት አብዮት እና የሀገራዊ ኢኮኖሚ ሽግግሩ በምድራችን ላይ እየታዩ ባሉ ተጨባጭ ውጤቶች እየተረጋገጠ ይገኛል።
በተለይም ግብርናን በማዘመን፣ በኢንዱስትሪ መስፋፋትና በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነትና በከፍተኛ ጥራት ወደፊት እየተራመደ ባለው የከተሞቻችን የመሠረተ ልማት ግንባታ ረገድ የተወሰዱት እርምጃዎች ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህ የዕድገት ጉዞ ውስጥ፣ በአቢቹ አመራር ስር ይህ ትውልድ ሙሉ ጉልበቱን፣ እውቀቱን እና የውስጥ አቅሙን ተጠቅሞ በገዛ ምድሩ ላይ ዘላቂ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ በተግባር አሳይቷል።
ይህ ሁለንተናዊ እርምጃ ጠንካራ የመንግሥት ሥርዓት ለመገንባት ያለንን አቅምና ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገረውን የኢትዮጵያን የብልጽግና ተስፋና መጻኢ ዕድል በታማኝነት የሚያበስር ነው።