11/05/2025
"የቱልት ቅጠል እየተመገቡ ይኖሩ የነበሩት እማሆይ"
//በዲማ የምታበራ ጸሀይ//
//እስኪ ይሄን እውነተኛ ተአምር ሼር ያድርጉት//
አማራ ክልል ጎጃም ብቸና ከተማ ከሸገር 265 ኪሎ ሜትር በእንጦጦ አድርገን እነ ሚዛንን፣እነ ሱሉልታን፣እነ ጫንጮን፣እነ ኩዩን፣እነ አሊ ዶሮን እነ ፍቼን አለፍ እንበል እና ገብረ ጉራች ለይ አፍሪካ ሆቴል ምሳ በላ አድርገን ጉሀፂዮንን እየቃኘን አባይ ደረት ደረቱን እየተመለከትን በአስፓልቱ ዳር ለዳር በተኮለኮሉት ዝንጀሮዎች አማካኝነት አቀባበል የሚያደርግልንን የታላቁን አባይ በርሀን "ተፈጥሮን ካስተዋልናት ገራሚ መሆኗን" እየቃኘን የፍቅር እስከ መቃብር ፍፃሜ የሆነችዋን በአባይ በርሀ ውስጥ የምትገኘዋን በርኸኛዋ ከተማ ተብላ የምትጠራዋን ፍልቅልቅን አሰስ እያደረግን የአባይን በርሀ በምናባችን እንሻገር እና ይሄን አስገራሚ ወሬ እንይ!
መቼም የታላቁን የፍቅር እስከ መቃብር ሀገር ዲማን ብዙዎቻችን በሀካልም ባይሆን በስም እናውቀዋለን ብዬ አስባለሁ።
እሙሀይ ብርሐን ይባላሉ በታላቁ በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ለዘመናት የሚኖሩ ሲሆን ከፈጣሪ የተሰጣቸው ፀጋ ለሰሚ ጆሮ በጣም ሊከብድ ይቻላል።
እናታች በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ከ30 አመት በላይ ኖረዋል። በነዚህ ዘመናት ምንም አይነት የቆርቆሮ ከለላም ሆነ ከፅሀይ እና ከዝናብ ሊከላከልላቸው የሚችል ነገር በሌለበት ባዶ ሜዳ ለይ እነዚህን 3 አስርት አመታት ተቀምጠው ዝናብ ሲዘንብ እሳቸው የተቀመጡበት ቦታ እና የሚኖሩበት አካባቢ ደረቅ ሆኖ እሳቸውንም ሆነ የተቀመጡባትን አካባቢ ዝናብ አያገኘውቸም እሙሀይ በዚህ ቦታ መኖር ከጀመሩባቸው ቀናቸው ጀምሮ ምንም አይነት ምግብ መብላት አለመቻላቸው የሰው ልጅ ለካ በምግብ ብቻ አይኖርም የተባለው ብሂል እውነት እንደሆነ እናምናለን።
የእማሆይ ይመገቢ የነበሩት ቱልት የተባለውን ቅጠል ሲሆን ብዙ ተማዕራትን በተለያየ ግዜ ሲያደርጉ በአካባበው ምዕመናን ታይተዋል።
ከዚህ አልፎ በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ አባቶች ከሰማይ በቀስተደመና አምሳል ከሰማይ ብርሐን ሲወርድላቸው አይተው መጥተው የእሙሀይን በረከት በረከትዎ ይድረስብን እናታችን ብለው እጅ ነስተዋል የእናታችን በረከት በጣም አስገራሚ እና አስደናቂ ነው እሰኪ ሁላችንም የእሙሀይ ብርሐን በረከት በየአለንበት ይድረሰን።
አያችሁ ሰው በፈጣሪ ፀጋ ብቻ እንዲህ ይኖራል እኔ እና እናንተን ግን አለም አሸንፋን፣ፍቅርን አጥተን፣አንዱ አንዱን እየበላ፣የሀሜት ማህተብ አንጠልጥለን፣የሰይጣን ምርኮኞች ሆነን፣ይሄው ከመኝታችን እስክንነሳ በልቶ የማይጠረቃው ሆዳችንን እየራበን ይሄው አለን፡፡
በልተን እንዳንጠግብ ምግባችንን ሰይጣን እየባረከብን ስንቶቻችን ነን ሺ ግዜ ምግብ ፊት የምንደቀን።
ብቻ ቤት ይቁጠረን!
አያችሁ የሰው ልጅ መልካም ከሰራ እና ከፈጣሪው ጋር ከታረቀ እስከመጨረሻው ያለምግብ መኖር እንደሚችል።
@የወሬውን ምንጭ ያገኘሁት ከዲማ ጊዮርጊስ ገፅ ነው
https://t.me/orthodoxtewohido
.
. #ገዳማትንይርዱ #ቤተክርስቲያናትንይጎብኙ #አብነትትምህርት #ቤቶችንይርዱ
የመፀሐፍ ቅዱስ ጥናት፤የቅዱሳን ገድል፣የአበው አባቶቻችን፤ጥንተ ቤተክርስቲያን እና የገዳማት ታሪኮች ይዘከርበታል።