Wube Electronics

Wube Electronics 😎

11/09/2025
11/09/2025

What is in your mind ?
ወጪ @

19/08/2025

ነሀሴ 13 2017

በኢትዮጵያ የደጋ አጋዘን ለማደን 15,000 ዶላር ያስከፍላል፤ ይህም ከፍተኛው የዱር እንስሳት የማደኛ ዋጋ ነው ተባለ፡፡

አንበሳን የሚያድን ሰው 4,000 ዶላር፣ ነብር 4,600 ዶላር ይታደናል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት ከዱር እንስሳት ህጋዊ አደን 193 ሚልየን ብር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ፡፡

በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደው 200 ሚልየን ብር ነበር፡፡

ሀገሪቱ ካላት የዱር እንስሳት ሀብቷ መካከል 54 የሚሆኑትን እንዲፈጸምባቸው ትፈቅዳለች፡፡

እንደ ዝሆን፣ ዋልያ፣ አቦሸማኔ እና ቀጭኔን ጨምሮ 48 የዱር እንስሳት ደግሞ ለአደን የተከለከሉ ናቸው፡፡

በዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የዱር እስሳት አጠቃቀም ዴስክ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ወርቁ የውጪ ሀገር አዳኝ ቱሪስቶች ወደ ሀገር ቤት ለአደን ከመጡ በኋላ የቆይታ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ ለማድረግ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማት ጥበቃና አጠቃቀምን በተመለከተ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው ደንብ ባስቀመጠው መሰረት አነስተኛው የማደኛ ዋጋ የጥርኝ ሲሆን 15 ዶላር፣ የጃርትን ደግሞ 20 ዶላር ያስከፍላል፡፡

የአየር ፊልም ቀረፃን ለማድረግ 15,000 ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን በመሬት ቀረፃ ለማድረግ 9,000 ዶላር ይጠይቃል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ማደን የሚቻለው ያረጁ ወንድ የዱር እንስሳ ብቻ ነው ያሉን አቶ ዳንኤል ወርቁ ሴቶችና ወጣት ወንድ የዱር እንስሳት ማደን የተከለከለ ነው ብለዋል፡፡

የተከለከሉ የዱር እንስሳትን ያደነ ሰው የተቀመጠውን የማደኛ ዋጋ እጥፍ ይከፍላል ተብሏል፡፡

አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ህጋዊ የዱር እንስሳት አደን ይካሄዳል፡፡

የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከነባሮቹ በተጨማሪ አዳዲስ ህጋዊ የማደኛ ስፍራዎችን ለመክፈት እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

11/08/2025
23/07/2025

ከአፋር ፖሊስ ኮሚሽን በክልላችንና በቀጠናው ያለ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የተሰጠ የአቋም መግለጫ!

የተከበረው መላ የአፋር ህዝብ እንዲሁም መላ ኢትዮጲያዊያን እንደምታወቀው የአፋር ህዝብ በታሪክ ለዚህ ሀገር ክብርና ልዑላዊነት እንዲጠበቅና እንከበር በርካታ ታሪካዊ ጀብድና ገድል እየፈፀመ የመጣና ዛሬም እየከፈለ ያለ ህዝብ ነው።

ቢሆንም ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የአፋር ህዝብ የሀገሩ ክብና ጥቅም እንዲጠበቅ በከፈለው መስዋዕትነት ልክ ተገቢ ክብርና ጥቅም ያላገኘ ህዝብ ሆኖ በገዛ ሀገሩና በገዛ ሀብቱ ላይ ባይተዋር እንዲሆን የተደረገ ህዝብ ነው!!

በዚህ ምክኒያት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ ፖሊስ ኮሚሽን የአፋር ህዝብ ክብርና ጥቅም የማስጠበቅ ህግ መንግስታዊ ግዴታ ያለበት በመሆኑ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የአቋም መግለጫ ለማውጣች ይገደዳል!

በመጀመሪያ ክልሉን በለውጥ ስም ስልጣን የተቆጣጠረውና ለ7 አመታት እየመራ የሚገኘው የብልፅግና ቡድን በማናለበኝነት የህዝብ ሀብት መበዝበዝና ጎሳን ከጎሳ በማጋጨት እየፈፀመ ያለው ሴራ እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም የስልጣናቸው እድሜ ለማራዘም ስሉ የአፋር ህዝብ ልዑላዊ ግዛት ለታሪካዊ የአፋር ጠላት ለሆነው ለኢሳ አሸባሪዎች አሳልፎ ለመስጠት መስማማታቸው እንዲሁም የአፋር ህዝብ ጠላት ከሆነው ከህወሓት ቡድን ላፈነገጠው ለነ ጌታቸው ሬዳ ቡድን ማሰልጠኛና እስትራቴጂካዊ ቦታ በአፋር ልዑላዊ ግዛት ውስጥ መስጠታቸው ደርሰንበታል!

በአጠቃላይ የአፋር ህዝብ ክብርና ጥቅም ያጠፋ የሚገኘው የብልጽግና ገዢ በአሁኑ ሰአት የሀገራችንን ህዝቦች ህይወት ለማጥፋትና አፋርን የጦርነትና የሽብር ሜዳ ለማድረግ የተለያየ ውሳኔ እየወሰደ የሚገኝ አፋርን በምንም መስፈርት የማይወክሉ ሞራል አልባ ስብስብ በመሆናቸው ምክኒያት እንደ ፖሊስ ኮሚሽን ባለን ህዝባዊ ወገንተኝነት ተገን በማድረግ ከስር ያለው የአቋም መግለጫ ለመውጣት ተገደናል!

1. የአፋር ፀጥታ ሃይሎች የአፋርን መሬት ለኢሳ አሳልፈው መስጠትን አይቀበሉም ።
2. የአፋር ጠላቶች የሆነ የተኛውም የታጠቀ ቡድን የአፋር መሬት ለጦርነት እንዲጠቀምና እንዲሰለጥንበት አንፈቅድም።

3. ቀይ ባህር ኢትዮጵያ አካል እናደርጋለን በማለት የአፋር ፖሊስና የአፋር ፀጥታ ሃይሎች እንዲሁም የአፋር ህዝብ ያልተገባ የመስዋዕትነት እንዲከፍሉ አንፈቅድም ።

በአጠቃላይ የአፋር ፖሊስ፣ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሺያ እና መላው የአፋር ህዝብ የክልሉን ገዢ ቡድን የአፋር ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆን አስጠቂና ባንዳ መሆኑን በግልፅ መረዳት ክብራችንና ጥቅማችን ለማስጠበቅ የኡጉጉሞ ትግል መቀላቀል አለባቸው።

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር!
22/07/2025

ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር!

Address

Zereyakob
Debre Birhan

Telephone

+251978162828

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wube Electronics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wube Electronics:

Share