Adabay-Media

Adabay-Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Adabay-Media, Media/News Company, Adabay አዳባይ , ሚዲያ, Debre Birhan.

ጠለፋ ወይስ ፍቅር ልጁ በጠለፋ ተፈላጊ ነው። ግራገባንኮ።
20/06/2023

ጠለፋ ወይስ ፍቅር ልጁ በጠለፋ ተፈላጊ ነው። ግራገባንኮ።

በአቶ ግርማ የሽጥላ ላይ የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ በማድረግ ስብእናውን ቀድው በመግድል ሞቱ የተገባ መሆኑን ለማሳየት ሲጥሩ የቆዩ ግለሰቦች እና አካላት ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው:: ሰውን ለግ...
28/04/2023

በአቶ ግርማ የሽጥላ ላይ የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ በማድረግ ስብእናውን ቀድው በመግድል ሞቱ የተገባ መሆኑን ለማሳየት ሲጥሩ የቆዩ ግለሰቦች እና አካላት ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው:: ሰውን ለግድያ ስታመቻች ቆይተህ እንደ ንጹሕ ሰው ልትንቀሳቀስ አትችልም:: ሰዎች ጉዳት እንዲደርስባቸው በአደባባይ ጥሪ ማድረግ በትንሹ ነውር፤ አለፍ ሲልም ወንጀል መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል:: መሞት ካለባቸው ሁሉም አማራ ብልጽግናዎች እንጅ ግርማ ብቻ መሆን የለበትም ።ቅርሻቱ የሁሉም ነው ። አንዳንዶች ግርማን የሚቃወሙት ሸዋ ስለሆነ ያሥመሥላል። በብቃት ሁሉም የክልሉ ሠዎች ቢደመሩ አይወክሉትም። ያ ሁሉ አማራ አልቆ ዶክተር ከፋለ የሰላም ስምምነት ፈርሞ መቀሌ አሸሸ ገዳሜ እያለ ነው። ግርምሽ ነፍስ ይማር።

12/04/2023
አማራ ክልል "የገባም አይወጣም የወጣም አይገባም" ።
10/04/2023

አማራ ክልል "የገባም አይወጣም የወጣም አይገባም" ።

የግንድ አግዝ ገብርኤል ያለህ"ወረታ" ከተማ ናትኮ።
10/04/2023

የግንድ አግዝ ገብርኤል ያለህ"ወረታ" ከተማ ናትኮ።

«የኢንተርኔት መዘጋት የኢትዮጵያ ህዝብ መብት አፈና!»ኢንተርኔትን (የሞባይል ኢንተርኔትን) መዝጋት፣መቆራረጥ የኢትዮጵያ  ህዝብ ባህል ሆኗል።በማህበራዊ ሚዲያዎች (በተለይ ፌስቡክ፣ቴሌግራምና ...
09/04/2023

«የኢንተርኔት መዘጋት የኢትዮጵያ ህዝብ መብት አፈና!»
ኢንተርኔትን (የሞባይል ኢንተርኔትን) መዝጋት፣መቆራረጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ባህል ሆኗል።በማህበራዊ ሚዲያዎች (በተለይ ፌስቡክ፣ቴሌግራምና ዋትሳፕ መጠቀም ቅንጦት ነው፡፡ ትኩስና ወቅታዊ በመሆናቸው፣እንዲሁም በግዢው ብልጽግና ቡድን ኢንተርኔት የሰብዓዊ መብት የሆነውን ከየካቲት 1/2015 አ.ም በሁሉም አካባቢዎች ኔትወርክ አይሰራም እንደልብ መደዋወል አይቻል ዳታም ጭራሽ እየሠራ አይደለም ቴሌኮምዬ ሆዬ ድምፃችንን ስማ ። ኢትዮ-ቴሌኮም ኔትወርክ ይልቀቅ፡፡ለመቼ ሊያገለግል ነው?Vpn እና psiphone የሠው ሀገር ዳታ ሰለቸን። ቴሌዎች ሁለት አይነት የአፈና ቴክኒክ አላቸው፤አንደኛው አገልግሎቱን በጣም ማንቀራፈፍ ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ አገልግሎቱ እንዳይኖር ማድረግ ነው። ድሮ የመጀመሪያው ነበር ያሁኑ የሁለተኛው ነው። ለማንኛውም፣መሰረታዊ ፍላጎት የሆነውን ኢንተርኔት ማስለቀቅ የሁላችንም ድርሻ ነው፤ኢንተርኔት የማግኘት መሰረታዊ መብት አለንና!

09/04/2023

ደብረ ብርሃን !!
ሰ/ሸዋ የደብረብርሃን ከተማ
★ በአማራ ክልል ሰ/ሜን ሸዋ ዞን ትገኛለች
★ በከተማዋ መጋቢት 10 ቀን 1446 ዓ/ም ብርሃን ከሠማይ በመውረዱ ምክንያት ቀደም ሲል ደብረ-ኤባ ተብላ ትጠራ የነበረችው ደብረብርሃን በሚል የሥም ለውጥ አድርጋለች
★ ከተማዋ ከ600 አመት በላይ ታሪክ ያላት የሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች አያት ከተማ ናት
★ የሐገራችን የታሪክ የጥበብ የዕውቀት መፍለቂያ ጥንታዊ ከተማ
★ የኢንቨስትመንት መዳረሻና የለውጥ ከተማ
* በሪጂዮ ፖሊቲያን መዋቅር በአምስት ክ/ከተማ ተዋቅራ በሐገር ባለውለታዎች የሠየመች
★ ብርሃን ከሠማይ የወረደባት የዓፄ ዘርዓይቆብ ከተማ
★ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት እና የኢትዮጵያ ሥልጣኔ አባት የሆኑት የእምዬ ሚኒልክ የትውልድ ከተማ
★ ለ300 ዓመት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና ያገለገለች የምርምርና የዕውቀት መፍለቂያ ከተማ
★ የኢትዮጵያ የአማርኛ ፊደል አባት እና ከ300 በላይ ሐይማኖታዊ መጽሐፍትን ለሐገራችን የአበረከቱት የቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረስላሴ ዘብሔረ-ቡልጋ ሐገር
★የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማና ስማቸውን በጨረቃ ላይ እንዲቀመጥ ያደረጉት እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት ዶክተር አፈወርቅ ተክሌ ሐገር
★የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጳጳስ የአቡነ ባስልዮስ ትውልድ ሐገር
★ በኢትዮጵያ የሥነ-ፅሁፍ ታሪክ ግንባር ቀደምና ፈር ቀዳጅ የሆኑት የተክለሐዋሪያት ተክሐማርያም ፣የከበደ ሚካኤል ፣የዳኛቸው ወርቁ፣የተክለፃዲቅ መኩሪያ የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ ወዘተ የትውልድ አካባቢ
★ የዓፄ ቴወድሮስን ታሪክ የፃፉት የአለቃ ዘነበ ሐገር
★ ትክክለኛዋ ለኢንቨስትመንት መዳረሻነት ተመራጭ ከተማ
★ ከ400 በላይ የውጪና የሐገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ሐብታቸውን ያፈሰሱባት የሠላም ከተማ
★ ከ208 በላይ ኢንዱስትሪዎችን ተቀብላ በአጭር ጊዜ ወደ ለውጥ የገባች ከተማ
★ የሐገር ውስጥና የውጪ ባለሐብቶች አይን የጣሉባት የኢንቨስትመንት ጥያቄን በአንድ ቀን ምላሽ የምትሰጥ ብቸኛ የኢትዮጵያ ከተማ ነች
★ የፌድራልና የክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች መገኛ ከተማ
★ አራት የኢንዱስትሪ መንደሮችን ከልላ እያስፋፋች ያለች የኢንዱስትሪ መናኸሪያ ከተማ
★ ለጅቡቲ ወደብ የቀረበችና ለደረቅ ወደብ ማስፋፊያነት የምትመረጥ
★ ከአፍሪካና ከኢትዮጵያ መናገሻ ከተማ አዲስ አበባ ከተማ በ109 ኪ/ሜትር ርቀት የምትገኝ
★እንግዳ ተቀባይ ታታሪና አገሩን ወዳድ ህዝብ ያለባት ከተማ
★ በዙሪያዋ የወተት ጅረት የሚፈስባት ደጋማ የሸዋ ብርሃን
★ በዙሪያዋ የአንኮበር ሎጅ የጓሳ ጥብቅ ደን የቀይ ቀበሮና የጭላዳ ባቡን መገኛ የወፍ ዋሻ ደን እኃ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነችው የሶረኔ ወፍ መገኛ ከተማ ናት
★ የአንባላጌው ጀግና የአደዋዉ ሠማዕት ግንባሬን ከተመታሁ ሐገሬ ወስዳችሁ ቅበሩኝ ጀርባዬን ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ ያለው የእምዬ ምኒልክ
⚫️የእራስ አበበ አረጋይ የሀይለ ማርያም ማሞ የሸዋ እረገድ ገድሌ ደጃዝማች ከፈለው የበሻህ ሀይሌ የአክሊሉ ሀብተወልድ
★ሳጥናኤልን ከእግዚአብሔር ለማስታረቅ አማላጅ ሆና ወደ ሲኦል የሔደችው የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ አካባቢ ሐገረ ማርያም ቡልጋ፡፡
★የአቡነ ተክለሐይማኖት የትውልድ ሐገር
★ ደብረብርሃን ብርሀን የወረደበት ቅድስት ሥላሴ ወደ ምሥራቅ ከተጓዙ በሬአገር ሐመረ ብርሃን መዳህኔአለም ገዳም ፣ ሚጣቅ አማኑኤልን፣ አንኮበር መዳህኔአለምንና አንኮበር ሚካኤልን የጎርጎ ዋሻ ገብርኤልን የመሥጫ ማርያም /እህል ከሠማይ የወረደበትን/ የደረፎ ማርያምን ይጎበኛሉ ወደ ምዕራብ ምርጫዎ ካደረጉ ሠሚነሽ ኪዳነ ምህረት /አንጎለላ/አፅም የማይበሰብስበትን አቡነ መልከ ፀዲቅ ገዳም ፣ አቡነዜና ማርቆስን ፣ታሪካዊዉን ደብረ-ሊባኖስ ገዳም ፣ደራ ገብረ ክርስቶስ ገዳም እና በልበሊት ገዳምን ወዘተ ጎብኝተው በረከት ያገኛሉ
ወደ ሠሜን ከቀጠሉ ቅድስት አርሴማን ፣ዳግማዊ ጎለጎልታ ገዳም ፣ኩክ የለሽ ማርያም ፣ፃድቃኔ ማርያም ፣አጃና ሚካኤል ፣የዘብር ገብርኤል ፣የአርባራ መዳህኔ አለም ስእሉ የሚያረግደው ሰማዕቱ መርቆሪዎስ ሸዋዕሮቢ አቡነ ጎርጎሪዎስ ወዘተ
ጎብኝተው በረከት አግኝተው በፀበላቸውም ተፈውሰው ይመለይመለሣሉ።

ሠበር ዜና 😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍ሸዋ ሞረትና ጅሩ ወረዳ መጋቢት 30 ቀን 2015 አ.ም አንድ የጅሩ ሰንጋ በሬ 260 ሺህ ብር በመሸጥ የኢትዮጵያን የእንሰሳት ግብይት ሪከርድ ሰበረ።
08/04/2023

ሠበር ዜና 😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍ሸዋ ሞረትና ጅሩ ወረዳ መጋቢት 30 ቀን 2015 አ.ም አንድ የጅሩ ሰንጋ በሬ 260 ሺህ ብር በመሸጥ የኢትዮጵያን የእንሰሳት ግብይት ሪከርድ ሰበረ።

ሰበር ዜና 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭ከአዲሥ አበባ ወደ ለሚ______መራቤቴ እስከ ወሎ የሚያገናኘው አንድ ለናቱ ጀማ ድልድይ ምክንያቱ ባልታወቀ ነገር ተደረመሠ ተባለ። በጣም ያሳዝናል...
05/04/2023

ሰበር ዜና 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭ከአዲሥ አበባ ወደ ለሚ______መራቤቴ እስከ ወሎ የሚያገናኘው አንድ ለናቱ ጀማ ድልድይ ምክንያቱ ባልታወቀ ነገር ተደረመሠ ተባለ። በጣም ያሳዝናል። ወደ ወሎና መራቤቴ የሚጓዙ አካላት ያለመረጃ እንዳይንቀሳቀሱ እና እንግልት እንዳያጋጥማቸው እናሳስባለን።

Address

Adabay አዳባይ , ሚዲያ
Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adabay-Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share