
01/04/2025
• የንጸሐን ጭፍጨፋ በብራቃት።
"…ዐማራው ወገናቸውን ይወጉ ዘንድ ወደ ዘመቻ የገቡት የዐማራ አድማ ብተናውና በኦሮሙማው መካከል ግጭት ተፈጥሮ ትናንት መጋቢት 22/2017 ዓም ከተዋጉ በኋላ በንዴት የጦፈው መከላከያ በጎጃም ክፍለ ሀገር ሰሜን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ከተማና በዙሪያዋ ወደሚገኙ ቀበሌዎች በመግባት በመንገድም፣ በቤትና በእርሻ ላይ ያገኛቸውን የሃይማኖት አባቶችን፣ ሴቶች እና ሕፃናትን፣ አረጋውያንና ገበሬዎችን ሳይቀር ቤት ለቤት እየዞረ ለጊዜው የታወቁ በስምም የተለዩ 46 ንጹሐን የጎጃም ዐማሮችን መጨፍጨፉ ተሰምቷል።