22/03/2026
አለም አቀፉ የዲጂታል ሚዲያ ኮከብ ዲላን ፔጅ (Dylan Page) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ነው!
በአለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮኖች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈውና ፈጣን የዜና መረጃዎችን በማድረስ “የዜና አባት” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ዝነኛው የቲክቶክ Content Creator ዲላን ጄምስ (Dylan Page) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑ ተሰማ።
ይህንን ታላቅ የምስራች በትላንትናው እለት ይፋ ያደረገው የ2025 የኢትዮጵያ የዓመቱ ምርጥ ቲክቶክሩ አዶናይ ሲሆን፣ ከዲላን ጄምስ ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
አዶናይ በቅርቡ ወደ ለንደን በማቅናት ከዲላን ጋር እንደሚገናኝና እ.ኤ.አ May 15, 2026 ዝነኛውን ጋዜጠኛ ይዞ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ አረጋግጧል።
በቲክቶክ ብቻ ከ19 ሚሊዮን በላይ ንቁ ተከታዮች ያሉት ዲላን ፔጅ ወደ ሀገራችን መምጣቱ ከዘገባቸው ባሻገር የሚከተሉትን ትልልቅ ፋይዳዎች ይኖሩታል ተብሎ ይታመናል፦
1. ዲላን ስለ ጉብኝቱ የሚያጋራቸው ይዘቶች በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአለም ዜጎች ዘንድ ስለሚደርሱ፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ መስህቦች ለአለም ለማስተዋወቅ ተወዳዳሪ የሌለው አጋጣሚ ነው።
2.ኢትዮጵያ ሰላም፣ የእንግዳ ተቀባይ እና ለቱሪዝም ምቹ መሆኗን በአለም አቀፍ መድረክ በተጨባጭ ለማሳየት ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል ይሆናል።
3. የአለም አይን በዲላን በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚያርፍበት ይህ አጋጣሚ ሀገራችን በዲጂታል አለም ያላትን ተሰሚነት ከፍ ያደርገዋል።
ይህ ጉዞ ለሀገራችን ቱሪዝም እና ገጽታ ግንባታ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ይሆናል::
Via Adoney
👏👏👏
ጉርሻ page
🌴🌴🌴