10/10/2025
የዕለቱ መልዕክት!
“ለማኅበረሰባችን የኤኮኖሚ እድገት እየሠራን ነው”
~ አቶ ተፈራ ወንድማገኘሁ
የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ
በዓለማችን በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ማቆጥቆጥ የጀመረው የአነስተኛ ገንዘብ ብድርና ቁጠባ (ማይክሮ ፋይናንስ) በእስያ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት በባንግላዴሽ እ.አ.አ በ1970ዎቹ በእነ መሐመድ የኑስ ገቢራዊ ምርምርና ትግበራ በመላው ዓለም ቀዳሚ የፋይናንስ አገልግሎት መስጫ ሆኗል።
እ.አ.አ በ2006 መሐመድ የኑስን ለኖቤል ሽልማት ያበቃቸው የማይክሮ ፋይናንስ ተደራሽነትና አሳታፊነት ላይ ዓለምን በማሳመናቸው እና ባመጡት የኤኮኖሚ አብዮት ነው።
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስም አድማሱን እያሰፋ በዛሬው ዕለት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ብቻ 3 ቅርንጫፎችን #በደብረማርቆስ፣ #በፍኖተ-ሠላም እና #በአንጅባራ ከተሞች ከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።የቅርንቻፎቹም ቁጥር 50 ደርሷል። በቅርብ ቀናት ተጨማሪ ቅርንጫፎችን እና ንዑስ-ቅርንጫፎችን በተለያዩ ዞኖች ከፍተን አገልግሎት እንሰጣለን።
ይህን በ7 ክልሎች እየተስፋፋ ያለውን የተቋሙን የፋይናንስ ተደራሽነትም በመላው የአገሪቱ ክልሎችና ኮርነር በማሳደግ ለአገር እና ለሕዝባችን ኤኮኖሚ አጋር ለመሆን እየሠራን ነው።
ስኬትን በተግባር!