ደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት

ደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት Trade and market development

13/03/2025
12/02/2025

የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ
==================
አዲስ አበባ ጥር 30/2017 ዓ.ም (ንቀትሚ) የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ ሚኒስቴሩ አሳስበዋል፡፡

01/01/2025
የንግድ ፈቃድ ዕድሳት በደጀን ወረዳ ያሉ ቀበሌዎች የንግድ ፈቃድ የዕድሳት ግዜ የሚጠናቀቀው ታህሳስ 30/2017 ነው ። ስለሆነም በዚህ ቀናት እንድታሳድሱ እየገለፅን ከጥር 1 ጀምሮ 1500 ...
12/12/2024

የንግድ ፈቃድ ዕድሳት
በደጀን ወረዳ ያሉ ቀበሌዎች የንግድ ፈቃድ የዕድሳት ግዜ የሚጠናቀቀው ታህሳስ 30/2017 ነው ። ስለሆነም በዚህ ቀናት እንድታሳድሱ እየገለፅን ከጥር 1 ጀምሮ 1500 ተቀጥቶ የሚታደስና በማንኛውም ኬላ የንግድ ዕቃው በፀጥታ ሀይል ቢያዝ ፈቃድ የፀና ንግድ ፈቃድ ስላልሆነ ምርቱ ውርስ የሚሆን መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ፈቃድ እንድታሳድሱ እናሳውቃለን ።

የሐዘን መግለጫየስራ ባልደረባችን አቶ ታደሰ ሽመልስ በአደረባቸው ህመም ምክንያት ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በተወለዱ በ41 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።አቶ ታደሰ ሽመልስ በምስ...
24/10/2024

የሐዘን መግለጫ
የስራ ባልደረባችን አቶ ታደሰ ሽመልስ በአደረባቸው ህመም ምክንያት ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በተወለዱ በ41 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ታደሰ ሽመልስ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት በገበያ ዋጋ መረጃና ትንበያ ባለሙያነት ከ2005 ጀምሮ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አቶ ታደሰ ሽመልስ ታማኝ ትሁት፣ ሰው አክባሪና በስራ ባልደረቦቻቸውና በሚኖሩበት ማህበረሰብ ዘንድም ተግባቢና ተወዳጅ ነበሩ ።

አቶ ታደሰ የ1 ወንድ ልጅ እና 2 ሴቶች አባት ሲሆኑ የቀብር ስርዓታቸው በተወለዱበት አካባቢ በደጀን ከተማ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ቦታ ተፈፅሟል።

በአቶ ታደሰ ሽመልስ ህልፈት የደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጸ/ቤት ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን ለልጃቸው፣ ለቤተሰባቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይንመኛለን።

በደጀን ወረዳ የትኖራ ንዑስ ከተማ የጎጃም ወተት ልማት ማህበር በአዲስ መልክና ጥራት የወተት እና የወተት ተዎጽዖ ምርቶቾን በማቀነባበር ፓስቸራይዝድ በማድረግ ለተጠቃማዎች ማቅረብ ጀመረ ። ከ...
24/07/2023

በደጀን ወረዳ የትኖራ ንዑስ ከተማ የጎጃም ወተት ልማት ማህበር በአዲስ መልክና ጥራት የወተት እና የወተት ተዎጽዖ ምርቶቾን በማቀነባበር ፓስቸራይዝድ በማድረግ ለተጠቃማዎች ማቅረብ ጀመረ ።
ከታች የምታዩት ፖስቸራይዝድ እርጎ ነው ። የተሻለ ጥራትና ሙሉ የወተት ንጥረ ነገሮችን የያዘ እርጎ በ45 ብር ብቻ
አድራሻ : _ የትኖራ ከተማ
በማንኛውም ግዜና ቦታ መጠቀም ይቻላል ። እርጎ አማረኝ ቀረ !!

03/05/2023

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ
===============================
አዲስ አበባ 24/08/ 2015 (ንቀትሚ) በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረ።
የዋጋ ማስተካከያው ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቆይ ነው።
በዚሁ መሠረት፡ -
ቤንዚን ----------- 69 ነጥብ 43 ብር በሊትር
ነጭ ናፍጣ ----------- 71 ነጥብ 08 ብር በሊትር
ኬሮሲን ----------- 71 ነጥብ 08 ብር በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ----------- 66 ነጥብ 60 ብር በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ ----------- 57 ነጥብ 84 ብር በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ ----------- 56 ነጥብ 50 ብር በሊትር
በሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ መሰረት የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች በዚህ ዙር ተጨማሪ የነዳጅ ዋጋ እንዲከፍሉ ስለማይደረግ የሚያገኙት የድጎማ መጠን ይጨምርላቸዋል።
በዚህ መሰረትም አዲሱ ዋጋ ተግባራዊ ሲደረግ ቀደም ሲል 17 ነጥብ 22 ብር የነበረው የቤንዚን ተጠቃሚዎች የድጎማ መጠን ወደ 25 ነጥብ 47 ብር የሚያድግ ይሆናል፡፡
የናፍጣ ተጠቃሚዎች ደግሞ ከ22 ነጥብ 68 ብር በሊትር ወደ 26 ነጥብ 46 ብር በሊትር ከፍ ይላል፡፡
የህብረተሰቡ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ምንም አይነት ጭማሪ የማይደረግ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኝ የመንግስት መዋቅርና የጸጥታ አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ ተገቢውን መከታተልና የመቆጣጠር ሚና ሊወጣ ይገባል፡፡

11/03/2023

Address

Dejen

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት:

Share