Dembecha zuria Communication

Dembecha zuria Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dembecha zuria Communication, Media/News Company, Dembecha Woreda Government Communicationየደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን, Dembech'a.

‎የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር የ90 ቀን ዕቅድ የክረምት ተግባራት አፈፃፀም ገመገመ።‎‎በግምገማው የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መስፍን ልየውን ጨምሮ፣ የደምበ...
10/08/2026

‎የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር የ90 ቀን ዕቅድ የክረምት ተግባራት አፈፃፀም ገመገመ።

‎በግምገማው የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መስፍን ልየውን ጨምሮ፣ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይበልጣል ባለው፣የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ አላምር ፣ሁሉም የፖለቲካና የፀጥታ አመራሮች ተገኝተዋል።

‎የግምገማው አላማ የ90 ቀናትን ተግባራትን ዕቅድ አፈፃፀም በመገምግም ጥንካሬዎችንና በማስቀጠል ክፍተቶችን ለመሙላት እንደሆነ ተገልጿል።

‎አስተዳደር ም/ቤቱ የ90 ቀን ዕቅድ በማቀድ ወደ ተግባር በመግባት ከ30 ቀናት በላይ ያሳለፈ ሲሆን የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ ሰፊ ስራ እንደተሰራ ተገልጿል።

‎በቀሪ ቀናት ቀሪ ተግባራትን በመፈፀም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ቀይ መስቀል በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ማህበረሰብ ተኮር ሥራዎች እያከናወነ ነው።በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት በክረምቱ የበጎ ፈቃድ ...
10/08/2026

ቀይ መስቀል በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ማህበረሰብ ተኮር ሥራዎች እያከናወነ ነው።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ማህበረሰብ ተኮር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

የቅርጫፍ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ሰንደቅ እንዳሉት፣ ተቋሙ ሰራተኞችንና በጎ ፈቃደኛ አባላትን በማስተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል።

በዚህም ለ66 ሰዎች 12 ኩንታል ዱቄት፣ ለ62 አረጋውያንና ህፃናት ልዩ ልዩ አልባሳት፣ በችግር ውስጥ ለሚገኙ 25 ሰዎች ደግሞ ልዩ ልዩ ጫማዎች ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

ማህበሩ ከ47 ሺህ 600 ብር በላይ ወጪ በማድረግ የሁለት አረጋውያንን ቤቶች በመጠገን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑንም አቶ ጌታሁን ገልጸዋል።

የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኞችም ለ12 ድንገተኛ ህሙማን የመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ ከማድረግ ባለፈ፣ ደም በመለገስና ከ1 ሺህ 200 በላይ ችግኞችን በመትከል ለአካባቢያዊ ልማትና ለማህበረሰቡ ደህንነት የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑንም አንስተዋል።

በቀጣይም በሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች በንቃት እንደሚሳተፉም ነው የቅርጫፍ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ የገለጹት።
West Gojjam Communications

"ወደ ጫካ የወጣነው ምክክር ባለመኖሩ ነው" ካፒቴን ማስረሻ ሰጤበመርጦ ለማርያም ከተማ ነው የተወለዱት። በወጣትነት ዘመናቸው ለሀገራቸው በሀገር መከላከያ ሠራዊት በአየር ኀይል ካፒቴንነት አገ...
10/08/2026

"ወደ ጫካ የወጣነው ምክክር ባለመኖሩ ነው" ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ

በመርጦ ለማርያም ከተማ ነው የተወለዱት። በወጣትነት ዘመናቸው ለሀገራቸው በሀገር መከላከያ ሠራዊት በአየር ኀይል ካፒቴንነት አገልግለዋል። በሕገወጡ የሕወሃት ቡድን የሥልጣን ዘመን በእስር ላይ አሳልፈዋል።

በለውጡ ወቅትም ከእስር ነጻ ኾነዋል። በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት የታጣቂ ኀይሎችን ሲመሩም ቆይተዋል። የግጭትን አክሳሪነት እና በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጫና በመገንዘባቸው ከጓደኞቻቸው ጋር የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ምክክር ለአንዲት ሀገር አስፈላጊ መኾኑን ይገልጻሉ። ምክክሩ በ1960ዎቹ አካባቢ ተካሂዶ ቢኾን መንግሥታት ሲቀያየሩ የሚፈጠረውን እልቂት ማስቆም፤ የምሁራንን እና የዜጎችን ሕይወት ማዳን ይቻል እንደነበር ይናገራሉ።

የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ሂደት አካታች፤ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ መኾኑንም ገልጸዋል።

"ወደ ጫካ የወጣነው ምክክር ባለመኖሩ ነው" ያሉት ካፒቴን ማስረሻ የእኔ ቁስል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቁስል ነው ብሎ መነጋገር ባለመቻሉ የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርገው እንደነበር ያነሳሉ። በትጥቅ ትግል የሕዝብን መከራ ማራዘም ብቻ እንጅ ጥቅም የለውም የሚል አቋም አላቸው።

ፍላጎታቸው መነጋገር ብቻ ስለነበር ከመንግሥት ጋር ድርድር በማድረግ የሰላም አማራጭ መቀበላቸውን ገልጸዋል። አሁንም የሀገራቸውን እጣ ፈንታ ለመወሰን በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ላይ እየተሳተፉ መኾኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እንድንከፋፈል አድርገውናል ነው ያሉት። በግጭት፤ በጦርነት ያመጣነው ለውጥ የለም ይልቁንም በግጭት ትውልድ እየገደልን፤ ሕዝብ እያሰቃየን፤ የሀገርን ዕድገት ወደ ኋላ እየመለስን ነው ብለዋል።

አንዱን ጨቋኝ አንዱን ተጨቋኝ፤ አንዱን ተጠቃሚ ሌላውን ደግሞ ተጎጅ በማድረግ ሀገር ልናራምድ አንችልም ብለዋል። የውጭ ኀይሎች በስሜት የሚነዳ ትውልድ እንዲፈጠር እየሠሩ መኾኑን ጠቅሰዋል። ለሀገር በማሰብ ውይይትን በማስቀደም የጠላቶችን ሤራ ማክሸፍ ይገባልም ነው ያሉት።

ታጣቂዎች በሕዝብ ጥያቄ ስም የራሳቸውን ጥቅም እንደሚያፈሩ ተናግረዋል። ሀገር የምትመሠረተው በምክክር መኾኑንም ገልጸዋል።

ሕዝብ ያለ ልዩነት በመምከሩ፤ ጽንፍ የረገጡ አስተሳሰቦች በሃሳብ የበላይነት እና በመነጋገር ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በምክክሩ ላይ ትልቅ ተስፋ እንዳሳደረባቸው አንስተዋል።

#አሚኮ #ሀገራዊምክክር #ኢትዮጵያ🇪🇹

‎ የአካባቢያቸውን ሰላም በጋራ ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከመንግስት ጎን በመሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የጨረቃ ከተማ ነዋሪዎች  ተናገሩ‎‎‎በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በየጨረቃ ከተማ "ለዘላ...
09/08/2026

‎ የአካባቢያቸውን ሰላም በጋራ ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከመንግስት ጎን በመሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የጨረቃ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ


‎በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በየጨረቃ ከተማ "ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የማህበረሰቡ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ፣ ወቅታዊ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታዎችን እንዲሁም የክረምት የልማት ስራዎችን ትኩረት ያደረገ የህዝብ ውይይት ተካሂዷል።

‎የህዝባዊ ውይይቱ አላማ ማህበረሰቡን በማደራጀት የአካባቢውን ሰላም ከሌቦችና ከአጭበርባሪወች ለመጠበቅ ራስ የማስቻል ስራ መሆኑን የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አቅም ግንባታና ፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ‎አቶ ብርሃኑ አላምር ገልጸዋል።

‎የሰላም መደፍርስ ድህነትን፣የሰወችን አመረጋጋት ያስከትላል። ሰወች እንደፈልጉት ተንቀሳቅሶ አለመስራት የማህበራዊ ግንኙነቶች መሻክርን መላላት እንዲሁም የሰባዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰቶችን ያስከትላል ነው ያሉት።

‎የልማት መሰረቱ ሰላም ነው ያሉት አቶ ብርሃኑ አላምር ሰላም የሁሉም ሰው የመንተፈሻ አካል ሳንባችን ነው ብለዋል። አክለውም ሁሉም ማህበረሰብ የሰላም አምባሳደር መሆን እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎እንደ ባለፉት 3 ዓመታት ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጭ አይሆንም ያሉት ሃላፊው ወላጆችም ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎ትምህርት ለማስጀመር በሚደረገው ርብርብ ሁሉም
‎ማህበረሰብ የትምህርት ቤት የገጽታ ግንባታ ላይ
‎በመሳተፍ የመማር ማስተማሩ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር
‎የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።

‎የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የጨረቃ ከተማ ነዋሪዎች የአካባቢያቸውን ሰላም በጋራ ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከመንግስት ጎን በመሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የህብረተሰብ ተወካዮችና የሃይማኖት አባቶች እንደተናገሩት፣ ሰላም የእድገትና የደህንነት መሰረት በመሆኑ የአካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበቅ የሚደረገውን ጥረት በሙሉ አቅማቸው እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

"የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል ትልቅ ፋይዳ አላቸው"- ዕድሜዓለም አንተነህየዞን፣ የፍኖተ ሰላምና የጃቢጠህናን ወረዳ መንግስት ሰራተኞችን ያካተተ የ...
08/08/2026

"የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል ትልቅ ፋይዳ አላቸው"- ዕድሜዓለም አንተነህ

የዞን፣ የፍኖተ ሰላምና የጃቢጠህናን ወረዳ መንግስት ሰራተኞችን ያካተተ የሸማቾች ህብርት ስራ ማህበር ለማቋቋም ያለመ ውይይት ተካሒዷል።

ውይይቱን የመሩት የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዕድሜዓለም አንተነህ እንደገለጹት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ፍላጎትና አቅርቦትን በማጣጣም ገበያን በማርጋጋት ጤናማ የገበያ ስርዓት ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው እንደሆነ ገልጸዋል።

መንግስት ሰራተኛውንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው የማህበረሰብ ክፍል ገበያው ላይ እያጋጠመው ያለውን ችግር ለማቃለል የሸማች ህብረት ስራ ማህበር በማቋቋም ገበያው ላይ ድርሻውን መወጣት አለበት ነው ያሉት።

ተግባሩ ሰው ተኮር ስራ ነው ያሉት አቶ ዕድሜዓለም ሰራተኛው ዓላማውን ተረድቶ ምስረታውን እንዲያሳካ ኀላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኀላፊ አቶ አጉማሴ አንተነህ እንደገለጹት ህብረት ስራ ማህበራት ገበያን በማረጋጋት ጤናማ የግብይት ስርዓትን ለመፍጠር ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሁሉም ሰው የሸማች ህብረት ስራ ማህበሩ ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባ ድርሻውን መወጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት ምሰረታ የረጅም ጊዜ የሰራተኛው ጥያቄ እንደሆነ የገለጹት ደግሞ የምዕራብ ጎጃም ዞን ህብረት ስራ ተጠሪ ጽ/ቤት ኀላፊ አማረች ነግሬው ናቸው።

ምስረታው የተሳካ እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።
West Gojjam Communications

በሰሜን ጎንደር ዞን የሰላም አማራጭን የመረጡ ታጣቂዎች በሰላም መግባታቸዉ ተገለጸ፤በሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ወረዳ የሰላም አማራጭን በመምረጥ ከትጥቅ ትግል ተለይተው ወደ ለሰላማዊ ሕይወ...
08/08/2026

በሰሜን ጎንደር ዞን የሰላም አማራጭን የመረጡ ታጣቂዎች በሰላም መግባታቸዉ ተገለጸ፤

በሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ወረዳ የሰላም አማራጭን በመምረጥ ከትጥቅ ትግል ተለይተው ወደ ለሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ የወሰኑ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግሥት ሰጥተዋል።

ታጣቂዎቹ ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሰላምን በመምረጥ በሰላማዊ መንገድ ለሀገርና ለማኅበረሰቡ የሚጠቅም ሕይወት ለመመሥረት በመወሰን በርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎችንም ለመንግሥት አካላት አስረክበዋል።

በእለቱ ለታጣቂዎቹ በዘሪማ ከተማ የዞን፣ የወረዳና የመከላከያ አመራሮች በተገኙበት ለታጣቂዎቹ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ተደርጎላቸዋል።

የሰላም አማራጭን መምረጣቸው በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን በማስፈን፣ ማኅበረሰቡን ከግጭት በመጠበቅና ልማትን በማፋጠን ረገድ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው በስነስርዓቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም ሌሎች ታጣቂዎችም የግጭትና የጥፋት መንገድን በመተው የሰላም አማራጭን እንዲመርጡና ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው የሰሜን ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን ነው።

‎በምዕራብ ጎጃም ዞን የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ህብራት ስራ ተጠሪ ጽ/ቤት "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ " በሚል መሪ ቃል ከአጋር አካላት የሰበሰበውን 88 ደርዘን ደብተር ለሁለተኛ ጊዜ...
08/08/2026

‎በምዕራብ ጎጃም ዞን የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ህብራት ስራ ተጠሪ ጽ/ቤት "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ " በሚል መሪ ቃል ከአጋር አካላት የሰበሰበውን 88 ደርዘን ደብተር ለሁለተኛ ጊዜ ለሴቶች፣ ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት አስረከበ።

‎የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ህብራት ስራ ተጠሪ ጽ/ቤት ሃላፊ
‎ አቶ በውቀት አታላይ በቀጣይም ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት
‎የሚደረገውን ማነኛውንም ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

‎በመማሪያ የቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ርቀው ለሚገኙ ህፃናት መድረስ በምድር የመልካምነት ስራ የሚገለጽበት በሰማይም ደግሞ ጽደቅን የምናገኝበት ተግባር ነው ብለዋል።

‎በድጋፉ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይበልጣል ባለው እና የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አቅም ግንባታና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ አላምር ተገኝተዋል።

‎ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ።‎‎በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በ2ቀጠናዎች ስር በሚገኙ ቀበሌዎች ከልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር "ለዘላቂ...
08/08/2026

‎ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ።

‎በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በ2ቀጠናዎች ስር በሚገኙ ቀበሌዎች ከልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር "ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የህብረተሰቡ ሚና " በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት ተካሂዷል

‎ውይይቱን የወረዳው የፖለቲካና የፀጥታ አመራሮች ተገኝተው አወያይተዋል።

‎በውይይቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አቶ መስፈን ልየው እንደገለፁት ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት የህብረተሰቡ ሚና የጎላ ነው ብለዋል።

‎ታሪካዊ ጠላቶቻችን በሰጡት አጀንዳ ተጠልፎ ሃገር ለማፍረስ የሚሰራን ሃይል ማህበረሰቡ በውል በመረዳት እረፍ ማለት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

‎ ታሪካዊ ጠላቶቻችን 130 ሚሊዮን ህዝብ የወደብ ጥያቄ ስንጠይቃቸው ከዚያም ከዚም ያኮረፉ አካላትን በማሰባሰብ ሀገርን ለመበጥበጥ እየሰሩ መሆኑን ማህበረሰቡ መረዳት አለበት ነው ያሉት።

‎ህዝባችን በዚህ የ3 ዓመት ግጭት የገጠመንን የሰላም ዕጦት መመርመር አለበት ያሉት ምክትል አስተዳዳሪው ትርፍና ኪሳራውን አመዛዝኖ በማየት ለሰላም ዘብ መቆም አለበት ብለዋል።

‎አቶ መስፍን አክለውም በሰላም ጉዳይ አባቶች የአባትነት እና እናቶች የእናትነት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ይህ ደግሞ ለሰላም ግንባታ በጎ አስተዋፅዖ አለው ሲሉ መክረዋል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የተሰማራው መከላከያ ሠራዊት ሀገራዊ አደራውን በላቀ ጀግንነት እየተወጣ ነው።   ​የምሥራቅ ዕዝ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል መላኩ ገላነህ በፀጥታ ማስከበር እና በግዳጅ ...
08/08/2026

በምዕራብ ጎጃም ዞን የተሰማራው መከላከያ ሠራዊት ሀገራዊ አደራውን በላቀ ጀግንነት እየተወጣ ነው።

​የምሥራቅ ዕዝ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል መላኩ ገላነህ በፀጥታ ማስከበር እና በግዳጅ ላይ የሚገኘውን ሠራዊት እየተዘዋወሩ ያለበትን የዝግጁነት ደረጃ ቃኝተዋል። አዛዡ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ሠራዊቱ የሕዝብን ሰላም ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ሕግ የማስከበር ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አዛዡ፣ የምሥራቅ ዕዝ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ የተላላኪዎችን ሴራ በማምከን ድልን መቀዳጀት የተለየ መለያው እንደሆነ አስታውሰዋል።

የኮሩ የሠራዊት አባላት የሕዝብ መገልገያ ተቋማትን ደህንነት በመጠበቅ ሰላም አስተማማኝ ከማድረግ አንፃር እያከናወኑት ያለው ግዳጅ ውጤታማ መሆኑን አዛዡ አረጋግጠዋል።

​ኮሩ ትልቅ አሀድ እንደመኾኑ መጠን በተሰጠው ተልዕኮ ሁሉ ትልልቅ ድሎችን እና ታሪካዊ ስኬቶችን ማስመዝገቡን እየቀጠለ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል።

የቀደሙት አባቶቻችን በደምና በአጥንት ዋጋ ከፍለው ያቆዩልንን ሀገር፣ እኛ የዛሬዎቹ ትውልዶች ነፃነቷን እና ሉዓላዊነቷን አጽንተን በማስጠበቅ ሀገራዊ አደራችንን በብቃት መፈፀም አለብን ብለዋል።

​ ጄኔራል መኮንኑ፣ ኮሩ የባዕዳንን ረጅም የጥፋት ዕጅ በመቆራረጥ የተጣለበትን ታሪካዊና ሀገራዊ አደራ ከክልሉ የፀጥታ ኃይል ጋር በመጣመር በውጤታማነት መወጣቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የሠራዊቱ አባላት በላቀ የሥነ ልቦና ዝግጅት፣ በጽናትና በወታደራዊ ዲሲፕሊን በመታነፅ የሕዝብ እና የመንግሥትን አደራ እስከ መጨረሻው በድል አድራጊነት እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።

ዘገባው የምሥራቅ ዕዝ ነው

Address

Dembecha Woreda Government Communicationየደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን
Dembech'a

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dembecha zuria Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dembecha zuria Communication:

Shortcuts

Share