
27/04/2025
አደገኛ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቀቁ‼️
ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ፣ ሕወሓትን በድጋሚ በምርጫ ቦርድ የማስመዝገብ ፍላጎት እንደሌለው በድጋሚ አስታውቋል።
ቡድኑ፣ ቦርዱ የሠረዘው የቀድሞ ሕጋዊ ሰውነቱ ካልተመለሰለት፣ አደገኛ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።
ፌደራል መንግሥቱ ጉዳዩን ወደ ቴክኒካዊ ጉዳይ እያወረደው ይገኛል በማለት የከሰሰው ቡድኑ፣ መንግሥት የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት መንፈስ እንዲያከብር ጠይቋል።