Yeshum Media- የሹም ሚዲያ

Yeshum Media- የሹም ሚዲያ Yeshum Media is a community news enteprise whose mission is to inform and entertain people

27/02/2024

!
በሸዋሮቢት ከተማ የከተማው የፖሊስ አዛዥ ኢ/ር ዘርዓይ እና የከተማው ሰላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ ፍፁም በአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ አስደናቂ ኦፕሬሽን በጠራራ ፀሃይ እስከ ወዲያኛው መሸኘታቸውን የዕዙ አመራሮች ገልጸዋል።

ምንጭ ኢትዮ 251 ሚዲያ

27/02/2024

ሰበር ዜና!
የአማራ ፋኖ በጎጃም ደምበጫ ከተማን ተቆጣጥሯል

ፍኖተሰላም ጅጋ አማኑኤል ያላችሁ የወገን ኃይሎች ከደምበጫ ፈርጥጦ የወጣውን ኃይል በንቃት ተከታተሉ አምልጦ ሊወጣ አይገባም።

የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ የክተት ጥሪ አስተላለፈ   ዕዙ በዛሬው ዕለት ከጠላት ጋር እየተፋለመ ሲሆን ደላንታ እና ኩታበር እንድሁም አምባሰል ወረዳዎችን አጣቅሶ ለደሴ ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች ከ...
27/02/2024

የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ የክተት ጥሪ አስተላለፈ
ዕዙ በዛሬው ዕለት ከጠላት ጋር እየተፋለመ ሲሆን ደላንታ እና ኩታበር እንድሁም አምባሰል ወረዳዎችን አጣቅሶ ለደሴ ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ነው:: በተጠቀሱት ቀጠናዎች ያለ የወገን ሀይል በነቂስ ወጥቶ መንገድ በመዝጋትና የደፈጣ ጥቃት በመሰንዘር ጠላትን ድባቅ እንድመታ ትዕዛዝ ተላልፏል::

ሰበር ዜና "አሳማ ከመሆን አንበሳ መሆንን መርጬ ፋኖን ተቀላቅያለሁ" ፋኖን የተቀላቀለው ኮሎኔል!    የ6ኛ እዝ 301ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዓባይ የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝን ተቀላቀለ...
26/02/2024

ሰበር ዜና
"አሳማ ከመሆን አንበሳ መሆንን መርጬ ፋኖን ተቀላቅያለሁ" ፋኖን የተቀላቀለው ኮሎኔል!
የ6ኛ እዝ 301ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዓባይ የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝን ተቀላቀለ። ኮሎኔል ዓባይ ከ34 አመት በላይ በውትድርና ሀገሩን ያገለገለ ሲሆን ጀግና አዋጊ እንደሆነ ይነገርለታል።

ይኸ ኮሎኔል ባለፈው ሳምንት ፋኖን የተቀላቀለ ሲሆን። "አይቼው አይቼው መንግስት የአማራን ሕዝብ ለማጥፋትና አንገት ለማስደፋት እየሰራ መሆኑን ተገንዝቤ አሳማ ከመሆን አንበሳ መሆንን መርጬ ፋኖን ተቀላቅያለሁ" ሲል ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተናግሯል።

ይህ ኮሎኔል የትውልድ ቦታው አማራ ክልል ሲሆን የፋኖን ትግል አምኖበት በአሁኑ ሰአት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝን ተቀላቅሏል።

ዘገባው የኢትዮ 251 ሚዲያ ነው። ሙሉ ቃለመጠይቁን የኢትዮ 251 ሚዲያን ዩቱዩብ በመጎብኘት ያድምጡ።

26/02/2024

በብር ሸለቆ ስልጠና አጠናቀዉ ሲመለሱ በነበሩ ሆድ የአደር አድማ ብተና ምልምሎችል ላይ እርምጃ መዉሰዱን በአዊ የራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ አስታወቀ፡፡

ምንጭ (ኤቢሲ ቲቪ የካቲት 18 2016 ዓ/ም)

የብርጌዱ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ያሬድ ለኤቢሲ እንደተናገረዉ የብልጽግና ወራሪ ቡድን የደፈጣ ጥቃት እንደረሰበት እና ሙት እና ቁስለኛዉን ይዞ ወደ ከተማ መሸሹን አስታዉቋል፡፡
አገዛዙ በየአቅጣጫዉ በአማራ በፋኖ እየተወሰደበት ባለዉ ያላሰለሰ እርምጃ በጭንቀት ዉስጥ ወድቋል ሲል አክሏል።ወራሪው ኃይል እየተወሰደበት ባለው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በዳንግላ ከተማ ለእንቅስቃሴ እንደተቸገረ ፋኖ ያሬድ ገልጿል።

በአዊ ዞን ከእንጅባራ ከተማ ዉጪ ያሉ ሁሉም አካባቢዎች ከጠላት ነጻ ወጥተዋል ሲል በአዊ የራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ያሬድ አስታዉቋል፡፡

መረጃ ከጎጃም ‼️የአማራ ፋኖ በጎጃም 10 - አስር ብርጌዶች ውጊያ ላይ ናቸው። ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎጃም "ሳሙኤል አወቀ ብርጌድ" ግንደወይን፣ "ገረመው ወንድ...
26/02/2024

መረጃ ከጎጃም ‼️

የአማራ ፋኖ በጎጃም 10 - አስር ብርጌዶች ውጊያ ላይ ናቸው።
ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎጃም "ሳሙኤል አወቀ ብርጌድ" ግንደወይን፣ "ገረመው ወንድ አውክ ብርጌድ " ቋሪት፣ "ቀኝ አዝማች ስሜነህ ብርጌድ" እንጅባራ ዙሪያ፣ "ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ" አዲስ ቅዳም፣ "ፊትአውራሪ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ" ዳንግላ፣ "ዘንገና ብርጌድ" ቲሊሊ፣ "ግዮን ብርጌድ" ሰከላ፣ "ደጋ ዳሞት ብርጌድ" ፈረስ ቤት ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ ይገኛል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም

ከቢትወድድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ | ዳንግላ ..‼️‼️ከቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ በሁሉም የእድሜ ደረጃ ለሚገኝ የከተማችን ህዝብ የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት!እንደሚታዎቀው በህዝባችን ላ...
25/02/2024

ከቢትወድድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ | ዳንግላ ..‼️‼️

ከቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ በሁሉም የእድሜ ደረጃ ለሚገኝ የከተማችን ህዝብ የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት!

እንደሚታዎቀው በህዝባችን ላይ የተቃጣውን ጥፋት ለመቀልበስ በፍፁም ፅኑነት እና ለህዝባችን ታማኝ በሆነ ሁኔታ የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ የህዝብ ልጆች ከሌሎች የወገን አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር እስከ ሞት መስዋዕትነት ትግል ላይ መሆናችን ይታዎቃል፡፡

በመሆኑም ለፋሽስቱ እና ፀረ አማራው ስርዓት ወንበር አስጠባቂ የሆኑ ጠላቶቻችንን ስርዓት ለማስያዝ እንዲሁም በግፍ ያለሃፂያታቸው ለሚጨፈጨፉ ንፁኃን ወገኖቻችን ደምን በደም የማጥራት ዘመቻ ከነገ ጀምሮ ለሚተገበረው እርምጃችን ህዝባችን አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ያደረግ ዘንድ ማሳዎቅ ግዴታ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ስለሆነም የግልም ሆን የመንግስት ትጥቅ የያዛችሁ የከተማችን ነዋሪዎች ከነገ ጀምሮ በሚደረገው ኦፕሬሽን ከታጋይ ወንድሞቻችሁ ጎን መቆም ግዴታ መሆኑን አውቃችሁ። ጥሪያችንን እንድትቀበሉ እያስገነዘብን እድሜያችሁ ለትግል የደረሰ የከተማችን ወጣቶች ደግሞ በቅርባችሁ ያገኛችሁትን ገጀራም ሆነ መጥረቢያ፤ አንካሴም ይሁን ቢላ ይዛችሁ በመውጣት ያለበደላችሁ ሊያጠፋችሁ የመጣውን ደም መጣጩ አረመኔ ጠላታችሁን ማርካችሁ ትታጠቁ ዘንድ ታሪካዊ የአርበኝነት ጥሪ ተደርጎላችኋል፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ የአማራ ፋኖ በጎጃም ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት አቅመ ደካሞች፤ ሴቶች እህቶቻችን እና እናቶች ደግሞ ከነገ ጀምሮ ከተማችን ላይ ምንም አይነት የትራንስፖርትም ሆነ የስራ እንቅስቃሴ አለመኖሩን አውቃችሁ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ከወዲሁ ታደርጉ ዘንድ ብርጌዱ ያሳውቃል፡፡

ድል ለጭቁኑ ህዝባችን!
ድል ለአማራ ፋኖ!
የቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ!

የአሳምነው ክፍለ ጦር አመራሮች ከላስታ
25/02/2024

የአሳምነው ክፍለ ጦር አመራሮች
ከላስታ

25/02/2024

የድል ዜና ከጎጃም
ፈረስ ቤት ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖዎቻችን ከወራሪውና ፋሽስቱ የአብይ አህመድ ሰራዊት ነጻ መውጣቷ ተረጋግጧል።

የጠላት ኃይል ፈርጥጦ ወገም ጊዮርጊስ እንደሰፈረም ለማወቅ ተችሏል። ወገም ጊዮርጊስ ከፈረስቤት ከተማ ከ7 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቀት ላይ ትገኛለች።

ድል ለህዝባችን!
የፈራ ይመለስ

25/02/2024

ካድሬው ገቢ ሆኗል:- የራያ ቆቦ ወረዳ የትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊና የብልፅግናዉ ካድሬ ትናንት ወርቄ አፋፍ ላይ የቀበሌዉን ህዝብ ሰብስቦ የፋኖን ስም ሲያጠፋ ዉሎ ወደ ቆቦ ለመመለስ ወደ መኪናው እያመራ እያለ በፋኖዎች ድንገተኛ ከበባ የአፋፍ ሊቀመንበር ጋር ተይዞ ተወስዷል::

25/02/2024

ሰበር ዜና | የመርጡለማርያም ከተማ 2 ኮር አመራሮች በወታደር አዛዦች መደብደባቸውን የሹም ሚዲያ ማረጋገጥ ችሏል። ካድሬው በሚቀልበው ሰራዊት እየተወገረ ነው። የባንዳ መጨረሻው ይህ ነው።

ከምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ የተላለፈ ጥብቅ ትዕዛዝ! የአማራ ፋኖ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች አንፀባራቂ ድሎችን እየተጎናፀፈ ይገኛል። በዚህም አገዛዙ አለኝ የሚለውን "የመከላከያ ሰራዊት" ገሚሱን...
25/02/2024

ከምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ የተላለፈ ጥብቅ ትዕዛዝ!

የአማራ ፋኖ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች አንፀባራቂ ድሎችን እየተጎናፀፈ ይገኛል። በዚህም አገዛዙ አለኝ የሚለውን "የመከላከያ ሰራዊት" ገሚሱን ደምስሰነዋል ቀሪውን ደግሞ እየደመሰስነው እንገኛለን፣ ገሚሱን ማርከነዋል ቀሪውን ደግሞ እያስከዳነው እንገኛለን። ከዚህ በፊት ያለውን ትተን ከሰሞኑ እንኳን ኮረኔሎችን ጭምር የፋኖን ትግል ደግፈውና ዓላማችን ገዝቷቸው ወደ እኛ የመጡ ሲሆን እኛም እነሱን የፋኖ አባል አድርገናል፣ በገባንበት አውደ ውጊያ ሁሉ በትንሽ መስዋዕትነት ከፍተኛ ድሎችን ተቀዳጅተናል።

በዚህ የተበሳጨው አገዛዝ ንጹሃንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት በወሎ፣ በጎጃም፣ በጎንደር እና በሸዋ እየፈፀመ ይገኛል። በመሆኑም በፋኖ ጠንካራ በትር ሲመታ ንጹሃንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት የተለመደ የአገዛዙ ባህሪው ነውና መላው የአማራ ፋኖ ከሰሞኑ ጠንካራ ኦፕሬሽኖችን እየፈፀምን ስለሆነ አገዛዙ በንጹሃን ላይ ሊያደርሰው የሚችለውን ጥቃት ለመቀነስ መላው የወሎ ጠቅላይ ግዛት መንገዶች ከየካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት እንዲዘጉ የወሰን መሆኑን እየገለጽን ሕዝባችንም ለውሳኔያችን ተገዥ እንዲሆን ካለንበት ከበረሃ ሁነን ጥብቅ መልዕክታችን እናስተላልፋለን። ከዚህ ትዕዛዝ የሚወጣ ካለ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ራሱ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እንገልጻለን።

ድል ለአማራ ፋኖ!

የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ
የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Address

Dese

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeshum Media- የሹም ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share