21/04/2024
የአማራው በረሄርተኛ ሃይልን አለማድነቅ አይቻልም‼
★★★//🍂//★★★
(ማሳሰቢያ:— ሙስሊም ሆናችሁ በኮመንት የምትሳደቡትን ያለ ምንም ምህረት ወደ ብሎክ እንደማስገባ ይታወቅ)
የአማራው ብሄርተኛ ሃይል ድብቅ ፍላጎትና የትግል ፕሮፓጋንዳውን ክፋት ለመረዳት የከበደው ሙስሊም በብዛት ይታያል።
የአማራ ብሄርተኛው ሃይል ክልሉ ውስጥ ሙስሊሙ በብዛት የሳሳበት አካባቢ ላይ ሙስሊሙን ያግታል፣ ገንዘብ ይዘርፋል፣ ይገድላል፣ ያፈናቅላል፣ መስጅድ ያፈርሳል ያቃጥላል፣ ሀሪማ ይቀማል፣ የታቀደ ኦፕሬሽን ሰርቶ በየሙስሊሙ ቤት እየገባ ጥቃት ያደርሳል። መልሶ ይህን የሰራው መንግስት ነው፣ ፋኖ በዚህ ሰኣት ምን ሊጠቀም ይህን ይሰራል? የሚል ለልጆች የተሰራ ፕሮ ጋንዳ ይሰራል፣ በአማራ ክልል ያሉ ሙስሊም አመራሮችን አቀነባባሪዎች አድርጎ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት ይሰራል። አሊያም አህመድን ጀበልን ከኦሮሚያ ወስዶ ጎጃም ላይ ያሳድርና አህመድንና ውሃብያ ኦሮሞዎች ናቸው ብሎ ድርሰት ፅፎ መንጋውን ያስከትላል።
ክልሉ ውስጥ ሙስሊሞች በሚበዙበት አካባቢ ደግሞ ሙስሊሙን በጎጃምና በጎንደር እንደሚያደርገው በወሎ መግደል፣ ማፈናቀል እንደማይችል የወሎ ሙስሊም ዴሞግራፊን በቅጡ የሚረዳ ጎበዝ ስብስብ ነው። ስለዚህ ጥይቱን ትቶ በፕሮፓጋንዳ ይሰልበዋል።
የሙስሊም አማራውን በኦሮሚያ በብዛት መጨፍጨፍ፣ መፈናቀል ደግሞ ደጋግሞ ፕሮፓጋንዳ በመስራት፣ "ወላሂ ከእንግዲህ አማራ አልሆንም!" የምትል ህፃን አኢሻ ፈጥሮ ሰፊ ቅስቀሳ ያደርጋል!
በቢሮክራሲው እጅግ አሳፋሪና ቅኝ ግዛት በሚመሰል መልኩ ሙስሊሙን ይጨቁናል፣ ከመዋቅር ያጠራል፣ ያባርራል፣ የመሬት፣ የሀብት ሽሚያ ውስጥ ገብቶ ሰፊ ስራ ይሰራል። ወሎ ዩኒቨርስቲን ምሳሌ ብናነሳ በግቢው ውስጥ አንድም የመካከለኛው አመራር ፖዚሽን ላይ ሙስሊም የለም።
ለትግላቸው አስጊ ያልሆነ፣ የመወሰንና የአመራር ፖዚሽን ላይ ያልሆነን ሙስሊም የመንግስት ሰራተኛን ለቅመው እየገደሉ ለመንጋቸው ባንዳ ተላላኪ ላይ እርምጃ ወሰድን ብለው ጀስቲፋይ ያደርጉላቸውና ፋኒት የሰይዲ ልጅ መጥታ ታዝግሃለች‼
የአማራ ብሄርተኛ ትግል «የቀራንዮ መዳረሻችን" ሀቲት ፣ "አራሽ ተኳሽ፣ ቀዳሽ" ሞቶ ወሎ ላይ ሲደርሱ ጥቂት ያሻሽሏትና " አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ፣ ሰጋጅ!“ ሲሉ እና ፋኖ ሰይዲን እና ፋኖ ማሜን ፊት ለፊት ይዘው በመምጣት የ"ሀበሻ አማራ ናው፣ የነጃሽ ተራራ ነው!“ ቂሷ እያስነገሩ ይመጣሉ።
ይህ በካውንተር ፕሮፓጋንዳ ኦቨር ዶዝ የነፈለለ እስላም መጨረሻውን ሳያገናዝብ "የተገደልነው በአማራነታችን እንጅ በእስላምነታችን አይደለም!" እያለ/እያለች የቡልሃ መንጢቅ ይዛ ታደርቅሃለች። ወለጋ ላይ ጎጃሜ ሰፋሪ፣ ትግሬ ሰፋሪ፣ ወሎየ ሰፋሪ እያለ ወሎየው ሰፋሪ ብቻ ተለይቶ ለምን እንደተጨፈጨፈ ለማስተዋልና የጎጃሜ ሸኔና ፋኖ እጅ ሊኖር እንደሚችልንኳ ማስተዋል አይችሉም።
በወሎ ኦሮሞ ሙስሊሞች ላይ ቀጥታ የፕሮክሲ ዋር ካውንተር ፕሮፓጋንዳን ሃይል ይጠቀምና የሸኔ፣ የኦሮሙማ ተላላኪና ኤጀንት ነው ብሎ ሰፊ ፕሮፓጋንዳ ይሰራና እስላሙን ጭምር በእስላም ወንድሙ ላይ አስዘምቶ መስጅድ ሲያስቃጥለው ያድራል‼
የአማራው ብሄርተኛና የአሃዳዊው ሃይል የፕሮፓጋንዳ አቅም እንኳን እኛን መንግስትን እንዴት እንደሚያንቀጠቅጥና አደገኛ የፕሮፓጋንዳ ፍሬሚንግ መሀንድስ እንደሆነ የማይረዳ የአማራ ክልል በርካታ ሙስሊም የፕሮፓጋንዳው ሰለባ ሆኖ መጠቀሚያ ሆኖ የነገ አስለቃሹን ሊያነግስ እንዴት ፊዳ እየሆነ እንደሆነ ስታየው ታዝናለህ!
የነሰይድ ድራርን ታሪክ ለፋኖ ሰጥታ እሷ ፋኒት ኻውለት ሆና የአሱሃቦቹን ታሪክ የሸኾቹን ማዲህ ወስዳ ለዘመነ ካሴ ሰጥታ በመንዙማ ስታሽሞነሙነው ስታይ ምንያክል ሙድ እንደያዙብን ይገለጥልሃል‼
ወንድሜ ምንድን አገኘህ?
ሽታየ ሳልስምህ ስትሄድ ሳላይህ
ቀረህ አሉኝሳ ለየት ብለህ
የናቴ ልጅ አንዱ በየት ላግኝህ
እሜዳ ጣሉህ ወይ ገደል ሰደዱህ
ለጅብም ሰጡህ ወይ አሞራ በላህ
ብቻህን ሆንክና እት እንደሌለህ
ክንዴ ፊዳ ልሁን ልሂድ አብሬህ
እያለች በመንዙማ የፋኖን እንቅስቃሴ ልታሰልም ስትፍገመገም ታያታለህ‼
የአማራውን ክልል ሙስሊም በጋራ እንዳያስብ የኮሌክቲቭ እሳቤውን በማሳጣት አሊያም የጋራ ግብ እንዳይኖረው እንደየአካባቢው ተጨባጭ በቅጡ የተቀረፀ የትግል ስልት እያደረገ እጅግ የሚደንቅ ስኬት ላይ ነውና በእስላሙ ግልብነት በብሄርተኛው አማራ ስኬት እየበሸቁ አለመደነቅ አይቻልም‼