06/03/2023
ዕለተዕለት ለብዙ ሃጃችን ብዙ እንኳትናለን፣እንለፋለን፣እንፈጋለን። ግን ያ የምንለፋበት ሃጃ ዱንያን ብቻ ያለመነው ወይስ ለአኺራም ጭምር ነው? ራሳችንን ወደ መጥፎ ሁኔታ ለመክተት ሌት ተቀን ደፋ ቀና የሚሉ ጠላቶች አሉን።እነሱም ነፍስያ እና ሰይጣን ናቸው።በነዚህ ዛሬ ብንፈተን ወደ ኸይር ስራዎች ከተሽቀዳደምንና እጃችንን ያዝ የሚያደርግ ከባድ ፈተና ሲገጥመን ራሳችንን ዝቅ በማድረግና ለሀያሉ ጌታችን አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እጃችንን ከፍ በማድረግና በመዋደቅ የራህመቱን ደጅ እናንኳኳ።
ምንም ምክንያት ቢገጥመን አስርም ቢሆን የዱንያ ሀጃ ፊታችን ቢደቀን ከኸይር ስራዎች እና ከጀመአ ውልፍት ማለት የለብንም። አለዚያ ወደ ነፈሰበት የምንነፍስ ከሆነ አወዳደቃችን ከባድ ነው።
እነሆ በወንጀል የቆሸሸች ልብ የምትጸዳበት፣የታጠፉ እጆች የሚዘረጉበት፣ምላሶችና ልቦች በቁርአን የሚረጥብበት ውድና የተከበረው ተናፋቂው ወር እየተጠጋን ነው።ስንቱ የረመዳንን መምጫ ሳይመለከት ወደ አኺራ የሄደ አለ፣ስንቱ በአሁን ሰአት በከፋና በማይድን ህመም የአልጋ ቁራኛ የሆነ አለ።እኛ አላሁ ሱ.ወ ለኛ በአፊያ እድል ሰጥቶናል ግን ወሩን ለመቀበል ተዘጋጅተናልን?ምን ያህል ራሳችንን አዘጋጅተናል?አሁንም አልረፈደም።የበደለንን ንጹህ የሆነ ይቅርታን እንበል፤ያስቀየምናቸውን አውፉ እንበል፤የተጣላን እናስታርቅ፣ጀመአን ከመበታተን ይልቅ እናጠናክር፤ምላሳችንን በቁርአን እንግራ፤የማይነጥፍ አጅር ከአላህ እናፍስ ዘንድ።
ወሩን የኸይር፣የፍቅርና የእውነተኛ ውዴታ ወር ያድርግልን።አሚን!!
✍ወንድም አንዋር ሱሴ
🕌رمضان مبارك