18/01/2026
ያንተ ባርነትህ የሚረጋገጠው በልብሀ ባለው ንፁህ ንያህ በምትታገለው ጉዳይ ብቻ ነው። አላህ አንተ ለምን እንደምታገል ከምታውቀው በላይ ኮ ያውቃል። ግን ዝም ይልሃል!... ምክንያቱም በትግልህ መንገድ አንተነትህ ስለሚሰራ ነው።ሶሃቦችም የተሰሩት እንደዚህ ነበር። በረዝም ግዜ ረሃብ...ተስፋ አሰቆራጭ ብዛት ባለው ጠላት... የውስጥ ሴራ...የሰይጣን ፈተና! በዚህ ሁሉ ግን አላህን
" በልባችን ላይ ትግዕስትን አፍስስልን።እንደሚገባህ አልተገዛንህም🤲"
እያሉ ዱዓ ያደርጉ ነበር።
* የሚያስገርመው ነገር በዚህ ዘመን አብዘሃኛው ሰው አዕምሮው ውስጥ ስለሚያውጠነጥነው ጉዳይም ረሱልን ሰ.ዐ.ወ ጠይቀዋቸው ነበር...ጥያቄያቸው ሶሃቦች ትግዕስት ከማጣታቸው ሳይሆን ከልባቸው ውስጥ ካለው የኢማን የቂንን ከማረጋገጥ የመነጨ ነበር።...እንዲህም አሉ..!
"... አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሁሉም ነገር ተፅፎ ካለቀ እኛ ለምን እንለፋለን!..ለምንስ ነው ትግላችን?¿ .." ሲሉ
ረሱል ሰ.ዐ.ወ ...
" ስራን ስሩ ሁሉም ሰው ለተፈጠረለት ነገር የተገራ ነው!" ብለው መለሱላቸው
ከዚህ መልሳቸው የምተወስደው ትምህርት በመጀመሪያ የምትሰራውን ስራ ዘወር ብለህ እንድትመለከት ነው። የምትሰራው ስራ ይቀለሃል ሳይሆን ትርጉሙ ነፍስህ ሁሌም መጀመሪያ የምትናፍቀው ሁሌ የምትጠማው ሁሌ እንቅልፍ የምታጣለት ነገር ማለት ነው። አየህ ሰዎች የሚለያዩት እዚህ ነጥብ ላይ ብቻ ነው! ነፍስህ የምታስበው ልብህ የሚቃጠለው ዱንያ ላይ ለሚያበቃ ነገር ከሆነ ወንድሜ ራስህን ካሁኑ አስተካክል... ምክንያቱም አኺራን ብታውቅም ብታምንም ለመስራት ፍላጎት የላትም, ያ ማለት ስለ አኺራ ጉዳይ የላትም!...
ነፍስህ ያዘነበለችው ቅድሚያ ወደአኺራ ስራ ከሆነ፣ ቅድሚያ ወደ ሶላት መስጂድ ከሆነ፣ቅድሚያ ወደቁርዓን እና አላህ ወደማወቅ ኢልም ከሆነ በርታ...ምክንያቱም ነፍስህ ለዚህ ተገርታለች!
..ይቀጥላል!
✍️ Hussu ahmed