
05/04/2025
ደሴና ኮሪደር ልማት
እኔ እሥሚገባኝ ከወሎ ባህል_አምባ_ሮቢት ቧንቧ ውኃ ያለው መንገድ ሥራ የተጀመረው የኮሪደር ልማት አጀንዳ ሳይመጣ ነው ምናልባት ትንሽ የማሥፋት ሥራ ተጨምሯል:: ነገር ግን ድሮ የተሠሩ ሥራዎችን ሁሉ እየለጠፋ የኮሪደር ልማት እያሉ ህዝብን ማደናገር ተገቢ አይመሥለኝም:: ድልድይ ተብላ በፌሥቡክ የምትቀርበው ነገርም ሮቢት ገበያን ከሥላሴ ጋር የምታገናኝ ሚጢጢየ ድልድይ ነች:: ቧተ ክህነቱንና ገበያውን ብቻ ነው የምታገናኘው:: የተሠራችውን ለቤተ ክርሥቲያኗ ብቻ ነው:: ለቤተ ክርሥቲያኗ መሠረራቱ ችግር የለውም:: ነገር ግን የኮሪደር ልማቱ ፍሬ አድርጎ ማቅረብ የደሴን ህዝብ ከመናቅ የመነጨ ነው::
ባጭሩ ሁለት ነገሯችን ማለት እፈልጋለሁ::
1] በሚድያ ጋጋታ ደሴ በኮሪደር ልማቱ የለለ እንደተለወጠች እያሥመሠልን ህዝብ ባናደናግር:: ደሴ እንደሆነች እርጅና እንደተጫጫናት ናት:: ያለማች ከተማን የኮሪደር ልማቱ ተጠቃሚ እንደሆነችና እንደለማች አድርጎ አለመሥራትን በሚድያ መሸፈን ካለማልማት የበለጠ በደል ነው:;
2] ኮሪደር ልማትን በተመለከተ እንደ ጅግጅጋና ጅማ ከመሳሰሉ ከተሞች
ልምድ ብንወሥድ:: እነዚህን ከተሞች ማየታችን ልምድ ማገኘት ብቻ ሳይሆን ደሴ ላይ የኮሪደረር ልማት አለመጀመሩን እንረዳ ነበር:: ይህ ደግሞ በአልሠራንም መንፈስ ተግተን እንድንሰራ ይረዳናል::