30/07/2025
ሰበር መረጃ‼️
በሰላማዊ ዉይይት ችግርን ከመፍታት ይልቅ በህዝብ ላይ የሀይል ርምጃ የወሰደው የደሴ ከተማ አስተዳደር ‼️
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
ጉዳዩን ለማብራራት ያክል‼
በደሴ ከተማ መናፈሻ ክ/ከተማ ላይ ቦሩ ሜዳ በመባል የሚታወቀው ታሪካዊ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህይዎታቸውን ገብረው ለልጅ ልጅ ያስተላለፉት ነፍስ የተገበረበት ርስት ነው።ቦሩ ሜዳ የማይታረስበት አንዱ ምክንያት የአያቶቻችንን ደምና አጥንት ሰብል አምርተን አንበላበትም። ለዚህም በዙሪያው ያሉ ከአምስት በላይ የሰማእታት ሃፊዞችና የሸኾች መቃብር ህያው ምስክር ነው።
በአሁኑ ሰአት ሙስሊሞች በህጋዊ መልክ መሬታቸውን በመሬት ደብተር አስጠንተው በሰላም በሚኖሩበት አካባቢያቸው ከሀያ አመታት በላይ ባስቆጠረው ታሪካዊ መስጅዳችን ዛቻ እና በደል ሲደረሰስባቸው ሰነባብቷል።
ይህ ዛቻ እና በደል በዘመነ ህዋሀትም አልደረሰም።በለውጡ ማግስትም በተፈራረቁ የከተማ አሰሰተዳደሮችም(ከንቲባዎችም) አልደረሰም።ማንም ትንኮሳም ፈፅሞ አያውቅበትም። ከታሪኩ ግዝፈት አንፃር ፣ በወሎ መሻይኽዎች ላይ ከተሰራው ግፍ አንፃር ማንም ቀጥ ብሎ አይቶ አይኑ ያማተረ አንድም የመንግስት አመራር አላየንም።
ዛሬ ላይ ግን ለውጡ ያመጣን ሹማምንቶች ነን በማለት ራሳቸውን እንደ ዘመነ አፄ ዮሃንስ በህዝብ ጫንቃ ላይ አሳርፈው ታሪክን እና ታሪካዊ ቦታዎችን ከማስከበርና ከማስቀጠል ይልቅ ዳግም የመጥፎ ታሪክ አካል መሆን አለብን ብለው በአጭር ታጥቀው የተነሱ ትንሽ የከተማዋ አመራሮች ተንኮል ጀምረዋል።
♦️በከተማ አስተዳደር ዘርፍ በየ ደረጃው የጉዳዩ ባለቤት ሊሆኑ ይችላሉ ብለን የጠየቅናቸው መስሪያ ቤቶች ጉዳዩን ፈፅመው እንደማያውቁት እና ስንነግራቸው ገና ሰምተው የደነገጡ ሁሉ ብዙዎች ናቸው።የማይታለም የማይቻለውን በማለትም ጭምር በግርምት በድንጋጤ ተውጠው አይተናል።
በቦታው አካባቢውን የሚያስተዳድረው የቀበሌ አመራር ምንም አይነት መረጃ የለውም ። ለነገሩ ቢኖረውስ ምን ሲደረግ ህዝብ ይደፈራል፣ጥቁር ታሪክን ለመድገም ይሞከራል።የመናፈሻ ክ/ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በሙሉ መረጃው የለውም። አልተወያዩም። ቃለ ጉባኤ የላቸውም። ሲሰሙ ግራ ገብቷቸዋል።
ዋናው አጋፋሪ የክ/ከተማው አስተዳደር አቶ ጥላሁን (የቀድሞው ፖሊስ) ነው ለማፍረስ የተንቀሳቀሰው። ነገር ግን ብቻውን ነው የሰራው ። ለምን ተብሎ ሲጠየቅ አዝዞኝ አስገድዶኝ ነው በማለት ግልፅ መልስ አስቀምጧል ።የበላይ አካል ተብዬው ሁሌም ይታወቃል።
አበል የተቆረጠለት የመንደር ሚሊሻ ተሰባስቦ በተከታታይ ሁለት ቀናት በህዝብ ላይ #ጥይት ተኩሷል ‼️
♦️ በዚህ ዙሪያ ጥምጥም የሀይል እርምጃ ላይ በቀጥታ የከተማ አስተዳደሩ የጉዳዩ ባለቤት ለመሆኑ ለከተማዋ ኗሪ ህዝብ ግልፅ እና ግልፅ ነው።በአበል የሚታለልን ሚኒሻ ጭኖ እየላከ ጠላት ሲመጣ አብሮት በሚሞት ህዝብ ላይ የጥይት ሩምታ መክፈት መንግስትን ጠልፋችሁ ካልጣላችሁ የሚል ይዘት ያለው መልዕክት በግልፅ አስቀምጧል።
ለመረጃ ያክል የመናፈሻ ክ/ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፖርቲ ሀላፊዋ /ፕሬዝዳንቷ) ወ/ሮ Hawi እና የክ/ከተማው አስተዳደር በተደጋጋሚ ፋኖ ወደ ከተማዋ እየቀረበ መሆኑን ሲናገሩም ጭምር ነበር ። አቶ ጥላሁን ካፈርኩ አይመልሰብ ብሎ የትናንትናው እሁድ ፋኖ ለደሴ ከተማ ትኬት ቆርጦ እንደነበር እና ፈረሳውን ቀድመን ያደረግነው ለዛ አቀባበል ዝግጅት ነበር በማለት ማስፈራሪያ ጭምር ሲናገር ነበር። እነዚህ በብልፅግና ስም የተሰገሰጉ የከተማችን ፋኖዎች ናቸው፣ህዝብ ሊነቃባቸው ይገባል።
ዛሬም ነገም አያቶቻችን ከተቀበሩበት የሜዳ ደለል እኛም እንቀበራለን እንጅ በፍፁም እኛ በህይዎት እያለን የአፄዎቹን ታሪክ አይደገምም ‼️