
20/06/2023
. ™
#የእንጀራ #እናት #ጡጦ ( #)
የእንጀራ እናት ጡጦ (pacifier)
እንጀራ እናት ጡጦ በተለይ ባደጉ ሃገራት ላይ አሁን አሁን ደግሞ በሀገራችን ዉስጥ ወላጆች ለልጆቻቸው ሲጠቀሙት ይስተዋላል።
በብዙ የሀገራችን ወላጆች ላይ ከሚፈጠሩ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የእንጀራ እናት ጡጦ ለልጆች ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ የሚለው ነው።
የእንጀራ እናት ጡጦ ጥቅምም ጉዳትም አለው::
ጥቅሙ
👉ከህፃናት ትንታን ይቀንሣል
👉በምቾት የተረጋጋ እንቅልፍ ለረጅም ሠአት እንዲተኙ ይረዳል
👉ጋዝ በቀላሉ ከሆዳቸው እንዲወጣ ይረዳል
👉ለስቅታ ለመቀነስ/ለማቆም ይረዳል
👉በተፈጥሮ ያለጊዜያቸው ለተወለዱ ህፃናት የመጥባት አቅማቸው ቶሎ እንዲጨምር እና በደንብ ከሚከሰትባቸውን የመተንፈስ መቋረጥ ችግርን ይቀንሳል።
👉እንቅልፋቸው ሲመጣ እና በተለያየ ምክንያት በሚነጫነጩበት ጊዜ ለጊዜያዊ ማባበያ እና ማረጋጊያ ይጠቅማል።
ጉዳቶቹ
👉 ንፅህናው ካልተጠበቀ ለሆድ ህመም(ለተቅማጥ እና ትውከት ህመም ) ይጋለጣሉ::
👉ከ6ወር በኃላ ለረጅም ሠዐት ምንሠጣቸው ከሆነ ለጆሮ ኢንፌክሽን ሊጋለጡ ይችላሉ::
👉ይዘውት ለረጅም ጊዜ ሚቆዩ ከሆነ የማውራት ጊዜ መዘግየት ያመጣል::
👉ከ2-3 አመት ባለው እድሜ ካላቆሙ የጥርስ አቀማመጥ መበላሸት ሊያመጣ ይችላል::
👉እድሜያቸው ከ አንድ ወር በታች ለሆኑ ህፃናት ከተጀመረ የእናት ጡት ወተት እንዲቀንስ ያደረጋል።
ጥንቃቄ
👉የእንጀራ እናት ጡጦን ከመጠቀማችን በፊት ሁልጊዜም ንፅህናው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
👉በተጠቀሙ ቁጥር መታጠብ እና መከደን በንፁህ ነገር መቀመጥ አለበት
👉በፍፁም ከወደቀ ሣይፀዳ አይሠጥም
👉ዙሪያውን ጀርም የመያዝ እድሉ ሠፊ ነው
በደንብ በሣሙና ንፁህ ስፓንጅ ለብ ባለውሃ አድርጎ ማጠብ ያስፈልጋል::
👉ሢገዛ በተቻለ ሚቀቀለውን መግዛት ያስፈልጋል አፍ ውስጥ ስለሚሆን ባክቴርያ የመያዝ እድሉ ሠፊ ነው:: ስለዚህ በደንብ እስከ 15ደቂቃ መቀቀል አለበት::
👉የእንጀራ እናት ጡጦ ልጅዎ እንዲለምድ ብለው ጫፉ ላይ በፍፁም ጣፋጭ የሆኑ ነገሮችን መቀባት አይመከርም፡፡
👉አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት የእናት ጡት ወተት መጥባት መልመድ ስላለባቸው እና ከእናታቸው ጋር ያለውን ትስስር ለመጨመር ሲባል 1 ወር ሳይሞላቸው የእንጀራ እናት ጡጦ መስጠት አይመከርም።
👉በተቻለ መጠን እድሜያቸው ከ 1 - 6 ወር ላሉ ህፃናት ብቻ የሚጠቅማቸው ከሆነ መስጠት ነገረግን ከ 6 ወር በኋላ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የእንጀራ እናት ጡጦ ቶሎ ማቆም ያስፈልጋል።
👉እንዲሁም ልጅዎን የሚያጎድልበት ነገር ስለማይኖር የእንጀራ እናት ጡጦን አለመጠቀምም ይችላሉ።
" አዘጋጅ "
ዶ/ር ቤዛማርያም ፍሰሀ
የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት
#የልጆቾዎ # #ጤና # #አመጋገብ #
ያሳስበዎታል እንግዳውስ ወደ ዶ/ር ቤዛማርያም ፍሰሀ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ጋር በልጀዎ ዙሪያ ላይ የማማከር ሆነ የማንኛውንም የህፃናት ህክምና እንሰጣለን.
#አድራሻ
📍Wollo [ #] 💖 #ደሴ #💖
📍🚑 W/ro Siheen General Hospital
ወ/ሮ ስኂን ጠቅላላ ሆስፒታል 🚑
📧 .com
📲 Tel. +251 946 49 00 59
.
and
/ ወደ ፌስቡክ ፔጃችን ይቀላቀሉ /
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093102187311&mibextid=ZbWKwL
. ™