Wello times/ ወሎ ታይምስ

Wello times/ ወሎ ታይምስ No

19/05/2022
02/04/2022
03/02/2022

የአማራ ወጣት ሆይ:-
***
እድል ፋንታህ ሚወሰነው በፖለቲከኛህ ብቃትና በሚያስመዘግበው ውጤት ነው። ለዚህም እጣህ ጠረጴዛ ላይ ቀርቧል ወይ ሊፈረድልህ አልያ ሊፈረድብህ።

ፖለቲካህ ሳይስተካከል መማርህም መመረቅህም ምንም ነው። ዲግሪህ ተራ ወረቀት ነው። ገበሬው አጎትህ የዘራውን ስንዴ ሌሎች ያጭዱበታል። የውበታሟ እህትህ ውበት አይቀጥልም ይከስማል። ሁሉንም ነገሮችህን ተራ በተራ ትነጠቃለህ።

#ፖለቲካህ የደም ስርህ ነው:-

በፖለቲካ ውክልናህ ብልጫ ከተያዘብህ ሁሉንም ነገሮችህን ተራ በተራ ትነጠቃለህ። በሁሉም ነገርም ብልጫ ይወሰድብሀል። በምድር ሁሉ ጎስቋላና ተቅበዝባዥ ሆነህ በጓደኛሞች ንግግር መሀል ሁሉ የመክሰር ምሳሌ ትደረጋለህ።

የሰሜን ኮከብ

እሆላሎይ እዋ እሆ ላሎ...!በተፈጥሯዊ ውበታቸው ላይ የአምላክ ረቂቅነት ቁልጭ ብሎ የሚስተዋልበት  ፥ ውቦቹ የወሎ ሳዱላዎች ፥ ወገብ ለወገብ ተቃቅፈው ክብ በመስራት ፦ >>>>በማለት ግጥም ...
23/01/2022

እሆላሎይ እዋ እሆ ላሎ...!

በተፈጥሯዊ ውበታቸው ላይ የአምላክ ረቂቅነት ቁልጭ ብሎ የሚስተዋልበት ፥ ውቦቹ የወሎ ሳዱላዎች ፥ ወገብ ለወገብ ተቃቅፈው ክብ በመስራት ፦

>
>
>
>
በማለት ግጥም እየተቀባበሉ በመዞር ጨዋታውን ድምቅ ፣ ሽብርቅርቅ ያደርጉታል፡፡ ጎረምሶቹ ደግሞ ጎፈሬአቸውን ነስንሰው ፥ ሚዷቸውን ሰክተው ሳዱሎቹን በመክበብ የጨዋታው አካል ይሆናሉ፡፡ በአብዛኛዎቹ በእጆቻው አርቲና ሎሚ ይይዛሉ፡፡ ከዚያም በዙሪያቸው ተውበው ጨዋታውን ካደመቁት ሳዱላዎች መካከል ቀልባቸው የከጀላትን ሳዱላ "እንኪ ውሰጅ!" ሲሉ እጃቸውን ይዘረጋሉ ፥ ይሻማሉ፡፡ እሷም ዘወር ዘወር ብላ ቀልቧ ከወደደው ክምክም ጎፈሬ ሎሚውን ትቀበላለች፡፡ ጨዋታው ይቀጥላል፡፡ ብዙ ሎሚ መቀባበልም ይቀጥላል፡፡ የምትታጭ ሳዱላ ላይ አደስና ሎሚ የመጣል ሂደትም የዚሁ ክዋኔ አካል ነው፡፡ መታጨቷን ለመግለፅም " እገሊትኮ ዛሬ አደስ ተጣለባት !" ይባላል፡፡ ክዋኔው ብዙ አይረሴና ምናልባትም ዛሬ በብዛት የተዘነጉ አስደሳች ባህላዊ ይዘቶችን የያዘ ነበር፡፡ በመሀል ግን ከሳዱላዎቹ ጋር ተያይዞ በጎረምሶቹ መካከል አልፎ አልፎ በዱላ መናከት እልፍ ሲልም በጩቤ መዘናጠል መኖሩ የክዋኔው አስፈሪ ገፅታ መሆኑ ይታወሰኛል!😔

ታዲያ! በዚያ በልጅ እድሜአችን ጥምቀትና ሚካኤል እንዲሁም አስተሪዮ ማሪያም እስከሚደርስ በከፍተኛ ጉጉት እንጠብቅ ነበር፡፡ ሀይቅ ከሚገኘው ፓሶሚሌ ሚካኤል ፣ አምባሰል ወረዳ ከምትገኘው ሶከኬ ማሪያም ብዙ አይረሴ የልጅነት ትዝታዎች አሉኝ፡፡ ያኔ በርግጥ ለአቅመ ሎሚም ሆነ አደስ መጣል ባንደርስም አስደሳች ትእይንቱን ከመታደም ባሻገር "እጢአችንን ጥለን" እንመለሳለን!😜

ይህን ትዕይንት አመት ጠብቆ የሚታደመው የእምነቱ ተከታይ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ነበር፡፡ እኛም ለአቅመ "ያኔ...!" ለማለት አብቅቶን ፥ ሁኔታውን የኃሊት የሽምጥ ጋልቤ ፥ ፍቅሩን ፣ መተሳሰቡን ፣ አብሮነቱን ፣ ቅንነቱን ፣ ደስታውን ፣ ...ወዘተ ሳስበው ፣ የማይሆነው እንደገና መፈጠር አለያም ወደዚያ የልጅነት ጊዜ መመለስ ሁሉ ያምረኛል!😢

አይ! ልጅነት!!!❤️❤️❤️

ጥቁሩን ናዚ፥ ዛሬ ለቆመበት ስፍራና አስቻይ ሁኔታ ምቹ መደላድል የፈጠሩት ያኔ ከጎንህ ነን አይዞህ ሲሉ የነበሩት ብአዴናዊያኑ ናቸው። ያኔ ትራምፕ በቴድሮስ ላይ ሲዘምትበት ጥቂት አማራዊያን ...
20/01/2022

ጥቁሩን ናዚ፥ ዛሬ ለቆመበት ስፍራና አስቻይ ሁኔታ ምቹ መደላድል የፈጠሩት ያኔ ከጎንህ ነን አይዞህ ሲሉ የነበሩት ብአዴናዊያኑ ናቸው። ያኔ ትራምፕ በቴድሮስ ላይ ሲዘምትበት ጥቂት አማራዊያን የትራምፕን አቋም ደግፈን የቴድሮስ የዘመናት ወንጀልን እየገለጥን ስንጮህ፥ ከአማራ ህዝብ ጥቅም በተቃራኒ ቆመው የቴድሮስ ጠበቃ ሆነው የቆሙት የብአዴን አህዮች ነበሩ።

ዛሬ በስልጣናቸው ሲመጣ፥ ለአማራ ህዝብ የተቆረቆሩ በመምሰል "ጥቁሩ ናዚ" ሲሉት ይውላሉ።

በነገራችን ላይ በውጭ ሀገር የሚገኘው የአማራ ሐኪሞች ማህበር የቴድሮስን ወንጀል የሚያጋልጥ ዝርዝር ሰነድ አዘጋጅቶ ቴድሮስ እንዳይመረጥ ሲሟገት፥ ብአዴን ማንኛውንም ትብብር ለማህበሩ በመንፈግ የቴድሮስን ወደስልጣን መምጣት ያፋጠነ ድርጅት ነው።

እነዚህ የብአዴን ሰዎች፥ "ኢትዮጵያ" ሲሉ እንደግለሰብ ራሳቸውን ማለታቸው መሆኑን ፈፅሞ መዘንጋት የለብንም።
የአማራ ህዝብ ሰቆቃ ቢገድዳችሁ ኖሮ፥ ይህ ፋሽስት ገና ወደስልጣን ሳይመጣ የማጨናገፍ ዕድሉ ነበራችሁ። ሲቀጥል ዶናልድ ትራምፕ ሁለተኛ ዕድል ሲያመቻች፥ የቀድሞ አለቃችሁ ተላላኪና ደጋፊ ሆናችሁ ነው የቀረባችሁት። የአሁኑ ጩኸታችሁ ለህዝባችን ከመቆርቆር ሳይሆን፥ ቴድሮስ በወንበራችሁ ስለመጣ ብቻ ነው።

አዎ እኛ አማራዊያን ግን ትናንትም ዛሬም ነገም ቴድሮስ ከናዚም የከፋ አረመኔ መሆኑን እናምናለን!!!

14/12/2021

➔ወራሪው መንጋ ፋብሪካችንን ነቅሎ ወስዶታል፡፡ እኛ ግን በፒንሳና ካቻቪቴ እየተጨቃጨቅን ነው፡፡

➔አሸባሪው ቡድን እንደ ወልድያ ያሉ ትልልቅ ከተሞቻችንን ነጥቆናል፡፡ እኛ ግን በማንቆርቆሪያ እየተካሰስን ነው፡፡

➔ርሐብ*ተኛው መንጋ በእኛው ተሸከርካሪ ጭኖ ዱቄታችንን እና እህላችንን ወስዶታል፡፡ እኛ ግን ‹‹ጆንያውንና ጎማውን ማን ወሰደው›› በሚል ርዕስ ሌባና ፖሊስ እየተጫወትን ነው፡፡

➔ወራራው ሃይል መደብሮቻችንን እና ተቋማቶቻችንን ዘርፎ ባዷቸውን አስቀርቷቸዋል፡፡ እኛ ግን የቤት ችግራችንን በውስጥ መፍታት አቅቶን ክልሉን ለመዝረፍ በተዘጋጀው ሃይል ፈንታ "ካርቶኑን የወሰደው ማን ነው›› በሚል አጀንዳ እኝኝኝኝኝ እያልን ነው፡፡

እናስ....
እንደ እኛ አይነት ሐሞት የለሽ ውዳቂ ልጅ ያፈራ ሕዝብ ተዋርዶ ከመኖር ውጭ ምን አማራጭ አለው?

(አሳየ ደርቤ)

13/12/2021

ውጫሌ
===
እንደሚታወቀው ባለፈው የውጫሌ ከተማ እና በዙሪያዋ ያሉ ተራሮች በወገን ጦር ገቢ ተደርጎ ነበር። የመንግስት መገናኛ ብዙሀንም ይሄንኑ ዜና በሰበር አሰምተውን ነበር።

ዛሬ ወደ ስፉራው ተጉዘን ያጣራነው መረጃ ግን ከዚህ የተለየ ነው። ውጫሌ በሁለቱም ሀይሎች ተይዛለች። የህወሓት ታጣቂዎች አበት አቦን፣ ነጎል ስላሴን፣ ውልቆን ይዘዋል።

ደንካ ሚካኤልን እና አካባቢውን ምሽግ አድርገዋል። የከተማውን ህዝብ እንደ ከለላ አድርጎ ሲሸነፍ ይደበቅበታል። ማጥቃት ሲፈልግ ከከተማው በመውጣት ተኩስ ይከፍታል።

የወገን ጦር ሮቢትን፣ ጭሳን፣ ቂንአምባጊወርጊስን፣ አጀዋ ወንዝን ከላይ እስከ ታች እና ደደሆራን ይዟል። በነዋሪዎቹ ላይ እስከአሁን ጉዳት እንዳልደረሰ ጃንጥራር አረጋግጧል።

ዛሬ በደሴ ከተማ የአምባሠል ወረዳ አስተዳደር ጸጥታ፣ አስተዳደር ጽ/ቤት እና ፓሊስ ስብሰባ አድርገዋል።

መረጃው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ያለው መረጃ ይሄው ነው።

ዛሬ ከከለላ ተቆርጦ የቀረ ኃይል በኩታ በር አድርጎ ደሴ ለመግባት ሞክሮ በጀግናው የወገን ጦር ተደምስሷል። ቀሪው የጁንታ ርዝራዥ ወደ ማርዬ በኩል እንደሸሸ

በሌላ በኩል ሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ
ፋጂ ፣መነዮ፣መንጠራ፣አረዳ ባሬ እና የሞለክሲ ከፍተኛ ተራራዎች በወገን ጦር ገብተዋል።

12/12/2021

#ፋኖ የ አማራ ኩራት

12/12/2021

«ጥይት ጨርሰናል ፤ ሽፋን ስጡንና አስወጡን።» ‼😂
—————————————————————
በጀነራል ዘነበ የሚመራው የህወሓት የተቆረጠው ታጣቂና ጀሌ በሲቃ ድምጽ ያስተላለፈው የሬዲዮ መልክት ነው።

Breaking newsየአሜሪካ ና እስራኤል ሴራ በኢትዮጵያየአሜሪካ ና እስራኤል ወታደራዊ የስለላ ተቋማት ለሕወሓት በሱዳን በኩል የድሮን መከላከያ ሚሳኤል ሊሰጡ አስበው መጨንገፉ ተሰማ። የድሮ...
10/12/2021

Breaking news

የአሜሪካ ና እስራኤል ሴራ በኢትዮጵያ

የአሜሪካ ና እስራኤል ወታደራዊ የስለላ ተቋማት ለሕወሓት በሱዳን በኩል የድሮን መከላከያ ሚሳኤል ሊሰጡ አስበው መጨንገፉ ተሰማ። የድሮን መከላከያው በቀላሉ ሰው ሊሸከመው የሚችል እና ከትከሻ ሊተኮስ የሚችል ሆኖ እስከ ሱዳን ድረስ ተልኮ ነበር። ሆኖም እቅዱ የመከነው ድሮኑ ኢትዮጵያ ከምትጠቀማቸው የተራቀቁ የቱርክ የተሻሻሉት የቻይና እና የኢራን ድሮኖች ጋር Compatible(ተናባቢ ሆኖ ሚመክት) ሊሆን አለመቻሉ ዋናው ምክንያት ሲሆን ሱዳንን ከትግራይ የሚያገናኙ ዋና ዋና መስመሮች በኢትዮጵያ ና ኤርትራ ወታደሮች በከፍተኛ ትኩረት ክፍተት ሳይፈጠር መጠበቁና ሰርጎ ለመግባትም አስቸጋሪ መሆኑ ሁለተኛ ምክንያት ነው።

በሌላ ዜና የኢትዮጵያ ድሮኖች የሚጠቀሟቸው ውድ የሆኑ ተተኳሾች እያለቁ ስለሆነ ሕወሓት ድጋሚ ያንሰራራል ተብሎ በሕወሓት ዋነኛ አክቲቪስቶች እየተገለፀ ያለው ነገር ከወታደራዊ ሳይንስ አንፃር አስቂኝ ነገር ነው ሲል አንድ ከፍተኛ የቻይና መካላከያ የቀድሞ ጄኔራል ገልፆዋል😎

ምንጭ_ African intelligence, xinua

08/12/2021

ዛሬ ረፋድ መቀሌ ላይ አየር ሃይል በተመረጡ የህወሀት ወታደራዊ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል።

06/12/2021

ፀረ ሰላም ኃይሎች በሱዳን ድንበር ሰርገው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ
==============
ከኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ተልዕኮ ተቀብለው በድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት በሞከሩ የአሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ እንዲሁም የቤሕነን ታጣቂዎች በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና በክልሉ ፀጥታ ኃይሎች የጋራ ጥምረት ርምጃ እንደተወሰደባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የታጣቂዎቹ ተልዕኮ የኅዳሴ ግድብ ተገንብቶ ስራ ላይ እንዳይውል እና መንግስት የያዘው የብልፅግና ጉዞ እንዳይሳካ ለማደናቀፍ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሀመድ ገልፀዋል።
በተወሰደው ርምጃም ፀረ ሰላም ኃይሎቹ ይጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ ጥይቶች እና ፈንጂዎች እንዲሁም አርፒጂ፣ ሞርታር እና ሌሎች ልዩ ልዩ ከባድ መሳሪያዎች መማረካቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የክልሉን ሰላምን በዘላቂነት ለማስቀጠል በተከናወነው ኦፕሬሽን ኅብረተሰቡም ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የጠቀሱት ኮሚሽነሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስተግበር የፀጥታ ስራው ከአጎራባች ክልሎች ጋር የጋራ ጥምረት በመፍጠር በእቅድ እየተመራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል፡፡
በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል አሸባሪው ሕወሓት እና ተላላኪው ሸኔ ሀገርን ለማፈራረስ የወጠኑት ሴራ መክሸፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ ገገልጸዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ ጠላት ሀገር ለማፈራረስ ጥረት አድርጓል፣ ብዙ ጥፋቶችን አጥፍቷል ያሉት ኮሚሽነሩ ይህንን ለመቀልበስ መላው ኅብረተሰብ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የክልሉ የፀጥታ ኃይል ከሌሎች የፀጥታ አካላት እና ከማኅበረሰቡ ጋር ባደረገው ቅንጅት በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የሸኔ ቡድን ላይ አስፈላጊውን ርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነሩ አክለውም ለአሸባሪው ሸኔ አገልግሎት ሊውሉ የነበሩ በርካታ የጦር መስሪያዎች ከመያዝ እና ቡድኑ የጦር ግብዓቶችን እንዳያገኝ የግንኙነት መረቡን ከመበጣጠስ አኳያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለፀጥታ ኃይሉ ተጨማሪ አቅም እና ጉልበት እንደሆነው መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

05/12/2021

እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይል ከህወሓት ነፃ የሆኑ አካባቢዎች ዝርዝር ፦

- ጋሸና
- ላሊበላ
- አርቢት
- አቀት
- ዳቦ
- ጃማ ደጎሎ
- ወረኢሉ
- ገነቴ
- ፍንጮፍቱ
- አቀስታ
- መዘዞ
- ሞላሌ
- ሸዋሮቢት
-ደብረ ሲና
- ራሳና
- ለምለም አምባ
- ጀውሐ
- ሰንበቴ
- አጣየ
- ካራ ቆሬ
- ኮን
- ዳውንት
- ልጓማ
- መሐል ሜዳ
- ጨፋ ሮቢት
- ሐርቡ
- መኮይ
- ቀውዝባ
- ጭላ
- አጅባር
- ተንታ
- ዶባ
- ማጀቴ
- ጭረቲ
- ከሚሴ
- ርቄ
- ወለዲ
- አልቡኮ
- የቃሉ ወረዳ አብዛኛውን ክፍል ሲሆኑ፣

የአካባቢው አስተዳዳሪዎች የተመለሱባቸው ቦታዋች ደግሞ፣
- ካሳጊታ
- ቡርቃ
- ዋኢማ
- ጭፍራ
- ጪፍቱ
- ድሬሮቃ
- አለሌ ሱሉላ ናቸው።

05/12/2021

ደሴ‼️
===
ጠቅላይ ሚኒስተሩ ገብተው ሰበር ዜና ሊነግሩን ከአልሆነ በስተቀር የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ ትላንት ደሴ ከተማን ተቆጣጥረዋል። ያለምንም ተኩስ ደሴ በጀግኖቹ እጅ ገብታለች።

ኮምቦልቻ‼️
===
ኮምቦልቻ ዛሬ ከዘገዬ ነገ ነጻ መሆኗን እንሰማለን። የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋ ውስጥ ገብቷል። ነገር ግን በከተማዋ ከአሸባሪው ጋር የተኩስ ልውውጥ አለ። ሸዋ ሮቢት፣ ከሚሴ፣ ሰንበቴ እና አጣዬ ህብረተሰቡ ወደ ቤቱ እየተመለሰ ሲሆን አጣዬ ላይ አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ አለ።

የመከላከያ ሰራዊት እና የአፋር ልዩ ኃይል ጀውሀ ላይ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የኦነግ ሰራዊት በቁጥጥር ስር አውለዋል። የአሸባሪው ትህነግ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ ብሎ መሸሹን ተከትሎ ወደየት መሸሽ እንዳለበት የተደናበረው ኦነግ አሞራ እንደሳታት የዶሮ ጫጩት በየጥሻው ከተደበቀበት እየተመነጠረ እጁን ረጥቷል።

ከጋሸና፣ ድብኮ፣ ሹምሸሃ እና አሙሲት የተመታው የጁንታ ኃይል ቁራጭ በሚባለው በጋዞ ወረዳ ቦያ ሚካኤል አካባቢ ቁጥሩ 2000 የሚሆን ወራሪ በአካባቢው ህዝብ መንገድ ተዘግቶበት ታግቷል። መሳሪያውን ጥሎ በአቋራጭ ወደ ሙጃ እና ቆቦ የሚያስወጣ መንገድ አሳዩን እያለ መሪ አልባ ሆኖ ሲደናበር መንገድ ተዘግቶበት ዛሬ 3ኛ ቀኑን ይዟል።

05/12/2021

ሸዋ ሮቢት
===
በሸዋ ሮቢት ከተማ የወራሪውን ቡድን ሲመሩ የነበሩ እና የውስጥ ባንዳ ሆነው ከተማዋን ሲያዘርፍ የነበሩ ተላላኪዎችን ፋኖ ርምጃ ወስዶባቸዋል።

በየስርቻው ከተደበቁበት በህብረተሰቡ ጥቅማ እየተለቀሙ ነው። በተጨማሪም በደብረ-ብረሃን ተከናቅለው የሚኖሩ የሸዋ ሮቢት እና የደብረ ሲና ነዋሪዎች እየተመለሱ ሲሆን ጤና ጣቢያዎች፣ ባንኮች እና የመንግስት መስሪያቤቶች ጥገና ተደርጎላቸው በቅርብ ስራ እንድጀምሩ ዛሬ በደብረ- ብረሃን የዞኑ አመራሮች ተሰብስቀው ውሳኔ አስተላልፈዋል።

ደብረ ሲና እና ሌሎች የአካባቢው ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ *******************************የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአሸባሪው ወራሪው ቡድን ነፃ የሆ...
04/12/2021

ደብረ ሲና እና ሌሎች የአካባቢው ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ
*******************************

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአሸባሪው ወራሪው ቡድን ነፃ የሆኑ ከተሞችንና የገጠር አካባቢዎችን እንደገና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት ደብረ ሲና፣ ጣርማ በር፣ የለን፣ ተሬ፣ ራሳ፣ ኩማሜ እና በሸዋ ሮቢት ዙሪያ ያሉ ሌሎች የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አግኝተዋል፡፡

ወራሪው የትህነግ ቡድን ሰሜን ሸዋ ዞን በገባበት ወቅት የወደሙና የተጎዱ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመጠገንና መልሶ በመገንባት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ሰራኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ነው፡፡

በዚህም የመካከለኛ እና የዝቅተኛ መስመር ፍተሻና ጥገና ተጠናቆ የተጠቀሱት አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ማግኘታቸውን የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በወራሪው ቡድን ምክንያት ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው ከቆዩ ከተሞች መካከል ሸዋሮቢት ከተማና በደብረ ሲና አካባቢ ያሉ አርማንያ፣ አስፋቸውና ጭራ ሜዳ የተባሉ የገጠር ከተሞች ህዳር በትናንትናው ዕለት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘታቸውን መግለፃችን ይታወሳል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን ሰጥቶ የነበረው የክብር ዶክትሬት ሰረዘ።የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ለዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን የኢትዮጵያ ምርት ገበያን...
30/11/2021

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን ሰጥቶ የነበረው የክብር ዶክትሬት ሰረዘ።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ለዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በማቋቋምና በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt)) የሰጣቸው መሆኑን አስታውሷል።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በወቅቱ የክብር ዶክትሬቱን የሰጣቸው የህብረተሰቡ አኗኗር እና የሀገሪቱን የውጭ ንግድ ስርዓት እንዲሻሻል ባበረከቱት መልካም አስተዋጽኦ እና ለወደፊቱም በተሰጣቸው የክብር ዶክትሬት ልክ ሀገራቸውን ያለአድሎና በእኩልነት እንዲያገለግሉ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ ነበር ብሏል።

ይሁን እንጅ ዶ/ር እሌኒ ሰሞኑን የዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል ተብሎ ይጠራ በነበረው ድርጅት አማካኝነት በድብቅ በተዘጋጀ የበይነመረብ ስብሰባ ላይ ሙያዊነትን ያልጠበቀ፣ አድሏዊ፣ የአንድን ቡድን ፍላጎት ብቻ ያንጸባረቀ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ዋና ዋና እሴቶች የሚፃረር ሀሳብን በማራመዳቸው ዩኒቨርሲቲው ለዶ/ር እሌኒ የሰጠውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በድጋሚ ሲያጤንና ሲመረምር መቆየቱን ገልጿል።

በዚህም መሠረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ለዶ/ር እሌኒ ገብረመድኅን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt)) እንዲሰረዝ መወሰኑን አሳውቋል።

25/11/2021

ሽዋ ያለው ሁኔታ # ግርማካሳ
————————————
ፋኖና የራሳ ገበሬዎች የሸዋ ሮቢት ከተማን ሙሉ ለሙሉ አስለቅቀዋል:: በርካታ
የወያኔኖ ኦነግ ታጣቂዎች ሞተዋል::
በደብረሲና በመከላከያ ጦር የተከበቡ አሸባሪዎች የሚማረኩት እየተማረኩ
የሚሞቱት እየሞቱ ነው::የቀሩት ጥቂቶች መሄጃ የላቸውም::
የመሃል ሜዳና የመዘዞ ከተሞች በወገን ጦር ስር ሆነዋል::
በሞላሌ አየር ሃይል በቅሪት የኦነግና ህወሃት ታጣቂዎች ላይ ትልቅ ጉዳት
አድርሷል::
ቀደም ሲል ከሳምንት በፊት ማጀቴ በህዝባዊ ሚሊሺያዎች ነፃ መውጣቷ
ይታወቃል:: አጣዬ ካራቆሬም ይከተላሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው::
ልክ በደቡብ ጎንደር እንደሆነው ነው በሸዋ እየሆነ ያለው:: በየቦትው እምስት
አስር እየሆኑ በየቦታው የሚሸሹት የመልቀም ስራ እየተሰራ ነው::

Address

No
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wello times/ ወሎ ታይምስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share