Dessie City

Dessie City Easy way to get latest info.

02/08/2022

በሽዋ ላይ ደሴ… ……ታቹን በቦረና‼

…………… ★★★……………

ወሎ እንደገና ከመከራው ጭጋግ ወጥቶ ታሪኩን ያድሳል‼
★★★

ከኢትዮጵያዊነት ዝቅ የማትለዋ ወሎ…… ውህዷ ወሎ‼ የነወርቂት አገሯ ወሎ…… የነ አባ ቡላ አገሯ ወሎ! የኢየሱስ ሞዓዋ ወሎ! …… የይኩኖ አምላኳ ወሎ! … የተድባበ ማርያሟ ወሎ…… የግሸኗ ወሎ… የሾንክየዋ ወሎ!……የዳንይ የአንየዋ ወሎ!……የይምርሃነ ክርስቶሷ ወሎ!……የሸኽ ደባት የጫሌዋ ወሎ!… የወረ ሸዃ ወሎ!… የንጉሥ ሚካኤሏ ወሎ!… የንግሥት መስታየቷ ወሎ!…… የንግሥት ዮዲቷ ወሎ!……የነ ወሌና የነ ጣይቱ ብጡሏ ወሎ!…… የነብርሃነ መስቀል የነዋለልኝ መኮንኗ ወሎ!…… የበላይ ዘለቀዋ ወሎ!… የጋስጫዋ ወሎ!… የጀማ ንጉሷ ወሎ!…የልጅ ኢያሱዋ ወሎ!……የአመዴ ለማዋ ወሎ!…… እንደገና ታብባለች‼
……………

ዛሬ ወሎ በጭጋግ ውስጥ ሆና እናቶቻችን ቢያለቅሱም ነገ ግን ብሩህ ጊዜን ለወሎየዎች ፈጥረን ልጆቻችን ፈገግታቸው ይፈካል‼
……………………

ገምናው ወሎ ናልኝ እንደገና‼

23/07/2022
አፌ ቁርጥ ይበልለዎት ከንቲባው !!" ወሎ የአንድነት፡የአብሮነት እና የፍቅር ተምሳሌት ናት "  ( ወሎየው የደሴ ከተማ ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ )ስለ ወሎ ህዝብ ደግነት እና ጀግንነት ሲነገር...
23/07/2022

አፌ ቁርጥ ይበልለዎት ከንቲባው !!

" ወሎ የአንድነት፡የአብሮነት እና የፍቅር ተምሳሌት ናት "
( ወሎየው የደሴ ከተማ ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ )

ስለ ወሎ ህዝብ ደግነት እና ጀግንነት ሲነገር ሆድ ቁርጠቱ
ለሚነሳበት መንጋ ከንቲባው እንዲህ ባማረ ቃላት ወሎን
ገልፀውታል! በነገራችሁ ላይ ምስራቅ አማራ፡ምንትስ አማራ
ምናምን እሚል ስያሜ ከአባይ ማዶ ውክልና ተሰጥቷቸው ወሎን እንጨፈልቃል ብለው ሲጋጋጡ ለነበሩ ዘውጌዎች አቶ
ሳሙኤል ሆድ ቁርጠታቸውን ጨምሮላቸዋል! ወሎ ላይ በሁሉም ዞኖች፡በሁሉም ከተማ አስተዳደሮች እንደ ሳሙኤል ሞላልኝ አይነት ህዝቡን በእኩልነት እሚያስተዳድር እና የተሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ እሚወጣ ጠንካራ መሪ
ያስፈልጋል ።

ወሎን የመሰለ ጠንካራ መሪ !!

እሁድ የካቲት 13 ደሴ አይቀርም ወሎ ባህል አምባ ከጧት 2:30
16/02/2022

እሁድ የካቲት 13 ደሴ አይቀርም ወሎ ባህል አምባ ከጧት 2:30

25/01/2022

የአፋር ህዝብ ብቻውን እንዲታገል ተፈርዶበታል የሰለጠነ መከላከያ ባለበት ሀገር እንዴት ገበሬ ይዋጋ ተብሎ ይተዋል ያስተዛዝባል። የፌደራል መንግስት አሁንም አረፈደም ሊግዝና ጥቃቱን ሊመክት ይገባል።

13/11/2021

ስለ ደሴ ወቅታዊ መረጃ፦
========================
ሊንኩን ሲጫኑ ዝርዝሩን ያገኙታል!!https://t.me/joinchat/XM60pFp-5BE5MDRk
ስለ ደሴና ቤተሰቦቻቸው ብዙወች በውስጥ ይጠይቃሉ።ጦርነቱ ከትግራይ ወጥቶ የወሎ ዞኖችና ወረዳወች በትግራይ ወራሪ ከተያዙ ጀምሮ የመብራትና የስልክ አገልግሎት ተቋርጧል።አጠቃላይ የወሎ ተወላጅ የሆኑ በውጭም በሀገርም ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ወንእምና እህቶች ስለ ቤተሰባቸው በመጨነቅና በማሰብ ቀኑ መሽቶ ሌሊቱ ይነጋል።ባለፉት 4 ወራት የወሎ ህዝብ ያየው መከራ አይነተ ብዙና ውስብስብ ነው።የገፈቱ ቀማሽ የሆኑት ደግሞ ቦታው ላይ ያሉት ብቻ ሳይሆኑ በውጭ ሀገር የሚኖሩትም ጭምር ናቸው!!

ይህን ስሜት ችግሩ ለደረሰበት ብቻ ካልሆነ ብታወራው አይገባውም።በዛ ላይ የመንግስት የውሸት ፕሮፓጋንዳና የፌስቡኩ የመሰለኝና ደሳለኝ ልቅቃሚ ወሬ ተጨምሮበት ሊያሳብድ ሁሉ ይችላል።በዚህ ጦርነት የተዋጋው ወታደሩ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገርም የሚኖረው ተወላጅ በሀሳብ ተራራውን እየወጣ፣ሸለቆውን እየተሻገረ ትልቅ ዋገ ከፍሏል።ቤተሰቤ ተራበ ተቸገረ ብለው ያጠራቀሙትን ሀብት እየላኩ ባዶ የሆኑትን ቆጥረን አንዘልቃቸውም!!

ታድያ መንግሰወትና የማዶ ሀገር ሰወች በወሎ ህዝብ ለማቾፍና ለማላገጥም ሞክረዋል።የወሉን ህዝብ ምንም ዋጋ እንዳልከፈለ ትግሉን ለወሎ ህዝብ ጥሎ መሞላቀቅ ያማራቸውንም አይተናል!!!

ወደ ዋናው ጉዳይ ልገባና ያገኘሁትን መረጃ ላጋራችሁ።

ዛሬ ከወሎ ዋና ከተማ ደሴ የቅርብ ጓዶች ደውለውልናል።የደወሉት ስልካቸውን በሶላር ቻርጅ አድርገው ጦሳ ተራራ ላይ ወጥተው ነው።

ደሴ ከተማ ላይ በአሁኑ ሰዐት አንፃራዊ የሆነ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።ከተማውን እንደ ባለቤት ሆነው የሚያስተዳድሩት ጁንታወቹ ሲሆኑ ዋና መቀመጫቸውን ያደረጉት ደግሞ አይጠየፍ ቤተመንግስት ላይ ነው።በደሴ ሁሉም መውጫና መግቢያ መንገዶች ላይ ዘበኛ ያስቀመጡ ሲሆን የደሴ መታወቂያ እያዩ ነው የሚያሳልፉት።

ከተማው ላይ ትልቅ ችግር የሆነው መብራትና ውሀ ነው።ሁሉም አይነት የመንግስት ተቋማት አገልግሎታቸው ስለተቋረጠ በዋናበትም ውሃ ትልቅ ችግር ሆኗል።
በከተማው ላይ ሱቆች የተከፈቱ ሲሆን ብዙ ሰው ካሽ ብር እጁ ላይ ስለሌለ ባንኮች ስለተዘጉ ትልቅ ችግር አለ።በጥቅሉ ይህ ችግር ቢበዛ አንድ ወር ያክል ከቀጠለና መንግስት የተለየ መፍትሄ ካልፈጠረ በከተማው ላይ ከፍተኛ ችግርና ርሃብ ሊከሰት እንደሚችል አስቀምጠዋል ነወሪወቹ።

ኮምቦልቻም ሆነ ሌሎች ከተሞች ላይ ያለው ሁኔታ ከደሴ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን በአሁኑ ሰዐት የጁንታው ወታደር ከተሞቹን ለቆ ወደ ግንባር ስለሄደ ከተሞቹ ላይ ያለው ህዝብ ያለ ስጋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ገልፀዋል።

ስለሆነም፦
መንግስት ትግራይ ክልል ሲያደርገው እንደነበረው አለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶችን በማስገባት ለህዝቡ እንድደርስለት እንጠይቃለን‼
በአስቸኳይም ችግሩ መፈታት አለበት።ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር ወረራወረም ውድመቱም እየተራዘመ ይሄዳል‼

የወሎ ድምፅ Voice Of Wollo ድምፅ
https://t.me/joinchat/XM60pFp-5BE5MDRk

ታማኝ የሆኑ ተጨማሪና አዳድስ መረጃወቻችን ይደርሷችሁ ዘንድ የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ!!

Address

Dessie
GERADO

Telephone

+251914159287

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie City posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dessie City:

Share