
25/09/2025
የሃይማኖት መቻቻል እና የህግ ማስከበር ጥሪ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅሬታ የፈጠረ አንድ ክስተት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ነው።
ይህ ክስተት አንድ ግለሰብ የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል ሲያወድም እና ሲሳለቅበት የሚያሳይ ቪዲዮ ነው።
ብዙ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት በሀገሪቱ የነበረውን የሃይማኖት መቻቻል የሚፃረር እና አሳዛኝ ድርጊት መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም፣ የሕግ አካላት ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ግለሰቡ ለፍርድ እንዲቀርብ ጥያቄ አቅርበዋል።
"ሕግ ይከበር፤ የሰውን ሃይማኖት ማክበር ግድ ይላል" የሚለው ጥሪም በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት እየተስተጋባ ሲሆን።
ይህን መረጃ ለብዙሃኑ ለማድረስ ሼር በማድረግ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴