02/11/2025
የባህር በር ጉዳይ በዋናነት የሚነሳው እንደ ሀገር መውጫ መግቢያ ስላጣን እና ስለታፈንን አይደለም፤ የወደብ ኪራይ ክፍያ ስለበዛብንም አይደለም፤ የህዝብ ቁጥራችን ብዙ በመሆኑም አይደለም፤ አስር ድስት ስለተጣደ ወይንም ስላልተጣደም አይደለም። መውጫ መግቢያ አጣን ብለን የላሙ-ኬንያ ወደብ ወይንም ፖርትሱዳን ይገባናል አላልንም፣ ኒውዮርክ ወይንም ኬፕታውን ወይንም ሌላ ይገባናልም አላልንም።
ይልቁንም አሰብን ጠቅሰን የባህር በር ይገባናል የምንለው አሰብ የኢትዮጵያ አካል ስለሆነ ብቻ ነው። አላግባብ ከኢትዮጵያ የተወሰደ ስለሆነ፣ ሉአላዊነትን ያላረጋገጠ የሽግግር መንግስት በተናጥል ውሳኔ አሳልፎ የሰጠው ስለሆነ፣ ተገንጣይና አስገንጣይ ተባብረው በአንድነት የፈጸሙት ታሪካዊ በደል ስለሆነ ነው የአሰብን የኢትዮጵያ አካል አለመሆንን የማንቀበለውና አሰብ ተፈጥሯዊ የኢትዮጵያ የባህር በርነቱ ዳግም ሊረጋግጥ ይገባል የምንለው።
ይህንን ጥያቄ ለማንሳትም ይሁን እንደ ሀገር በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ለመታገልና ጥያቄውን ለማስመለስ ከዚህ የተሻለ ግዜስ ከአሁንቀደም ነበር ወይ? አይመስለኝም! (ለዚህም ብዙ ምክንያትና ሰፋ ያለ ትንታኔ ሊቀርብለት ይችላል)።
Yes, as a country, we might have taken a long way in the wrong direction, but it is time now that we got to turn around as we do.
Remember also, Vitamin Sea is a vital necessity. It helps heal wounds, maintain good health. So, we need it !
ይሄው ነው!