ESAT WORLD

ESAT WORLD World News Production Company.

07/01/2026

‎እንጀራው ወልድያ እየተጋገረ፤
‎ወጡ ጉባላፍቶ ሲሸተኝ አደረ።

‎የማሽላው አገር አላገዶ ነው፤
‎ጥንቅሹን ወልድያ ምን አበሸለው።

‎እየተባለ ይዜምላታል!

‎የወሎዋ ሁለተኛ መድናም ይሏታል።

‎የመሰረቷት ታላቁ እራስ አሊ ናቸው። ከተመሰረተች ደግሞ ከ200 አመት እድሜ በላይ አስቆጥራለች። ይህች ጥንታዊት ከተማ ማን ትባላለች?

‎ለመሆኑ ታላቁ ራስ አሊ ማን ናቸው?

‎ቀዳማዊ አሊ /አሊ ጓንጉል/ እየተባሉ ይጠሩ የነበሩት ታላቁ እራስ አሊ የየጁ ስርወ - መንግስት መስራች ናቸው!

‎ከአባ ሴሩ ጓንጉል እና ከላስታዋ ባላባት ከወ/ሮ ገለቡ ፋሪስ የተወለዱት ታላቁ ራስ አሊ ከየጁ ወረሸህ መነሻ ከሆኑት ሸህ ዑመር 7ኛ ትውልድ ናቸው።

‎ራስ አሊ (ቀዳማዊ አሊ) ወይም በጊዜው ይጠሩበት የነበረው ታላቁ ራስ አሊ አባታቸው ከመሞቱ ቀደም ብሎ በ1766 የበጌምድር እንደራሴ ሆነው በመሾም ለአስር አመታት በጌምድርን ሲያስተዳድሩ ከቆዩ በኋላ ከሴሩ ጓንጉል ቤተሰብ የመጀመሪያው ሰው በመሆን የመጀመሪያው የየጁ ስርወ መንግስትን ስልጣን ይዘዋል።

‎ታላቁ ራስ አሊ ከ1777- 1782 በጎንደር ቤተ መንግሥት የመጀመሪያውን የየጁ መሳፍንት የበላይነት ይዘው ያስተዳደሩ ታላቅ ንጉስ ናቸው።

‎የታላቁ ራስ አሊ ቤተ-መንግሥት መርጦ ከተማ በምዕራብ በኩል ልዩ ውበት ና ዕይታ ባላት አምባ ላይ ተሰርቶ የነበረ ሲሆን በአካባቢው የድንጋይ ካብ መሰረት ፣ የፍሪዳና የጠጅ መጣያ የነበሩ ምልክቶች አሁንም ይገኛሉ፡፡

‎በመጨረሻም ታላቁ ራስ አሊ (ቀዳማዊ አሊ) በ1782 በመሞታቸው ወንድማቸው ራስ አሊጋዝ እሳቸውን በመተካት የጎንደር እንደራሴነት(የየጁ ስርወ መንግስት ሁለተኛው ራስ በመሆን) ስልጣንን ጨበጠ።

ወሎ ደሴ

10/12/2025
29/06/2023

ረባዳው ዥጣ ዋድላ ደላንታ ወሎ

@ አማራ ቱሪዝም

24/01/2023

አይጠይፍ ሆኖ ይታያል ከሚሴ
ፍቅር ያልገባው ሰው ምን ያረጋል ደሴ!!!
ደሴ: ወሎ: ኢትዮጵያ

22/10/2022

`` መ ሰ ጠ ት . . .''

መርሳ ነሽ ' ውጫሌ ' ላስታ 'ወረባቦ
ሐይቅ ነሽ ' ውርጌሳ ' ዋጃ ' ራያ ቆቦ
ኮምቦልቻ ነሽ ' ባቲ ' ቦረና ' መቅደላ
አላማጣ ' ዞብል ' ጥሙጋ ' ከለላ
አርጎባ ነሽ ' መቄት ' መካነ ሰላም
ዋድላ ነሽ ' ሰቆጣ ' እስታይሽ ' ኮረም
ወልዲያ ነሽ ' ተንታ ' ሳይንት ' ከሚሴ
ሳንቃ ነሽ ' ሲሪንቃ ' ወረኢሉ ' ደሴ !!

መጣሁ ተቀበይኝ ' በሙሓባሽ በቅሎ
ምድረ ገነቷ አፈር ' አብሽር በይኝ ወሎ !!
✍️ Abdi T Yesuf

12/10/2022

ደሴም ገበያ ነው እግር ላደረሰው
ባቲም ገበያ ነው እግር ላደረሰው
ባንቺአሮ ባንቺአሮ
እንዴት ይሞታል ሰው?
ወሎ: ኢትዮጵያ

ሰበርየህወሃት ጦር መሪዎች የሚሸሹ ወታደሮቻቸው እንዲረሸኑ የሰጡት ትዕዛዝIntercepted phone communication 🔊 77 ----79 አለህ 79-79-97-97🔊 አለሁ አለሁ 79 አጠ...
25/09/2022

ሰበር

የህወሃት ጦር መሪዎች የሚሸሹ ወታደሮቻቸው እንዲረሸኑ የሰጡት ትዕዛዝ
Intercepted phone communication

🔊 77 ----79 አለህ 79-79-97-97
🔊 አለሁ አለሁ 79 አጠገብህ አለ-
🔊 አዎ ከኔጋ አለ
🔊 እንደዚህ ተጠቀሙና 98 እየፈለጋቹሁ ነው
🔊እሺ 64 አለህ
89 አለህ
65 አለህ
እሺ 77ስ አለህ

🔊አለሁ
🔊79 አለህ
🔊አለሁ
🔊ለ99 እነግረዋለሁ ስሙኝ ትላንት የተደረገ መጥፎ ነገር ሁላቹሁም እንድታውቁት ነው::
🔊እሺ
🔊ከአንድ ቤት 4 ዶሮዎችን አርደው በልተው -
ሁለት ሞባይል
ጨውና በርበሬ
ልብሶች ዘርፈው ሂደዋል ::እሄ የምነግራቹሁ ከአንድ ቤት ብቻ ነው ::

ሸለቆው አከባቢ ያሉ ቤቶችን በሙሉ እየበረበሩ ነው::ስለዚህ እየመራን አይደለንም አካሄዳችንም በደምብ አድርገን እንፈትሽ ይሄ አደጋ ነው በጣም አደገኛ ነው ::

በጣም የሚያስገርም ነው ከአንድ ቤት ትላንት ከእግሩ ላይ ጫማውን አስወልቀው የወሰዱ ታጋዮችም ጭምር አሉ ::
ትላንት ሙሉ ቀን ነው ቤቶቹ ሁሉ እየበረበሩ የዋሉት::
የሰው ሃይላችሁን ዙራቹሁ አረጋግጡ አለበለዝያ እኔ እያዞርኩ እርምጃ እወስዳለሁ ::

እቺን አሁን ተግብሯት እየዞራቹሁ ::

ይሄ 98 ተረድተሀኛል 89 ተረድተሀኛል 65 ተረድተሀኛል 94 ተረድተሀኛል እሺ 79
- ተረድቸሃሁ
ቤቶቹ ሙሉ በሙሉ በስርአት እዛ ማዶ እንዳደረግነው እዚህም ጀምረዋል ከአንዱ የተዘረፈው ቤት ላይ ፎቶ እና ደብዳቤያቸውን አግኝተናል ::

የማን መሆኑን እናሳያቹሃለን :: በጣም የሚያሳዝን ስራ ነው እየተሰራ ያለው ::

ከራበዉ ቢኮራመትም ቢሞትም ጭምር ከዚህ በላይ ግን ለትግራይ ህዝብ ሓዘን ልተውለት ተገቢ አይደለም ::

አሁንም በመንደሮች እየተበታተነ ነው:: በደምብ እዩት ሌላ ስራ የላቹሁም ከበታቻቹሁ ያለውን አደራጁት ::ከአዛዦች ውጭ ሁሉም ይሰማራ ይሂድ ::

ምክትሎቹ ከናንተጋ ያሉት ከአዛዦች ጋር ከበታቻቸውም እየተረዳዱ እያንዳንዱ በቦታው እንዳለ አረጋጣቹሁ ሪፖርት አድርጉ ::

ሪፖርት እፈልጋለሁ አሁን

ካልሆነ እንደ መጥፎ የሆነ እንሰሳ በየቦታው እየተዞረ መጥፎ የሆነ ስራ ነው እየተሰራ ያለው ይሄንን በፍጥነት አውርዱት አሁን::
79 ወስጃታለሁ።

የ #ወሎ መዝናኛ ማዕከል ( ) ሲሆን ቆየት ያሉ የወሎ #ሙዚቃዎችን፣ ታሪካዊ #ቪድዮዎችን፣ #ግጥሞችን፣ የወሎ ከተማ እና ገጠር #ምስሎችን ከነ ገለፃቸው ባጠቃ....

ክብር በታላቅ ተጋድሎ በከፍተኛ መስዋዕትነት ከዓመት በላይ በጁንታው ቁጥጥር ስር የቆየችውን ማይጠብሪን ለተቆጣጠሩ የእናት ኢትዮጵያ ጀግኖች!!የኢትዮጵያን ጦር ከድል በስተቀር ወደፊት በድል ከ...
06/09/2022

ክብር በታላቅ ተጋድሎ በከፍተኛ መስዋዕትነት ከዓመት በላይ በጁንታው ቁጥጥር ስር የቆየችውን ማይጠብሪን ለተቆጣጠሩ የእናት ኢትዮጵያ ጀግኖች!!

የኢትዮጵያን ጦር ከድል በስተቀር ወደፊት በድል ከመገስገስ የሚያስቆመው ሃይል አይኖርም!

An Ethiopian soldier carried his wounded colleague on his back 1935.
31/08/2022

An Ethiopian soldier carried his wounded colleague on his back 1935.

30/08/2022

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተማዎች፣ ወረዳዎች እና ዞኖች በተንቀሳቃሾችና በአገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሰዓት ገደብ ወስነዋል። በዚህም መሠረት መንቀሳቀስና አገልግሎት መስጠት የተከለከለው፦

1. ወልዲያ ከተማ
ሰው- ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 1፡00 ድረስ
ተሽከርካሪ- እስከ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ

2. ሰቆጣ ከተማ
ሰው- ከምሽቱ 1፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ድረስ
ተሽከርካሪ - ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ድረስ
ተፈናቃይ - ከካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ ሙሉ በሙሉ ክልክል ነው።

3. ሐይቅ ከተማ
ተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡00 በኋላ
መጠጥ ቤቶች - ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ

4. ኩታበር
ተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡00 በኋላ
መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ

5. ደሴ
ምግብና መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ
ማንኛውም እንግዳ- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ
የከተማው ነዋሪ- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ታክሲ- ከምሽቱ 2፡ዐዐ በኋላ
ባጃጅ- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ

6. ኮምቦልቻ
ሰውም፣ታክሲዎችም- ከቀኑ 11፡00 በኋላ

7. መቅደላ
ተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡ዐዐ እስከ ጧቱ 12፡ዐዐ ድረስ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 እስከ ጧቱ 12፡00 ድረስ
ምግብና መጠጥ ቤቶች -ከምሽቱ 2፡00 በኋላ

8. ደብረ ብርሃን
ተሽከርካሪ - ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ምግብና መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ተፈናቃይ- ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ ወደ ከተማዋም ወደ ጣቢያም መግባት ክልክል ነው።

9. ደባርቅ ከተማ
ባጃጅ- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ
ተፈናቃይ- ከምሽቱ 12፡00 በኋላ ወደ ከተማውም ወደ ጣቢያም መግባት ክልክል ነው።

28/08/2022

እኔ ለጥምር ሰራዊታችን ደጀን ነኝ፤ ያለ እነሱ መስዋእትነት ነገ እንደሌለ አውቃለሁ፡፡ (በድሉ ዋቅጅራ)

ከህይወት በላይ ታላቅ ነገር የለም፡፡ ወታደርነት ይህንን ታላቅ አንድ ህይወት በፈቃደኝነት ለወገን መስዋእት ማቅረብ ነው፡፡ መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሀይሎች፣ ፋኖዎች በአሁኑዋ ቅጽበት ህይወታቸውን እየከፈሉልን ነው፡፡ የሚሞቱት እኛ እንድንኖር ነው፡፡
ጦርነት በተዋጊው ሰራዊት ሞትና ሽንፈት አያበቃም፡፡ ትህነግ በታሪኩ ለሰላማዊ ውይይት ተቀምጦ የማያውቅ፤ ከመግደል፣ ከማውደምና ከመዘረፍ የዘለለ ግብ የሌለው አሸባሪ ነው፡፡ ለዚህ እማኝ መደርደር ጊዜ ማጥፋት ነው፡፡
በጣም የሚያሳዝነው ግን በሰራዊቱ ሽንፈትም ሆነ ድል መሳለቅ ነው፡፡ ተንታኝና አክቲቪሰት ነኝ ባይ፣ ሰራዊቱ ሲያፈገፍግ፣ ‹‹እኔ እንዲህ ብዬ ነበር! ተመልከቱ›› እየለ የሰራዊቱን መስዋእትነት በፍሬከርስኪ ብሽቅ ትንተና ሲመጻደቅበት መመልከት ልብን ያደማል፡፡ ምንም ያህል መንግስትን ብንቃወም፣ ምንም ያህል ጥላቻ ቢያውረን ነው የመንግስትን መጥፎነት ለማሳየት በሰራዊታችን መስዋእትነት ለማሾፍና ለመመጻደቅ የምንበቃው?
ሰላም በሰላማዊ መንገድ ሊመጣ አልቻለም፡፡ አሁን ምርጫ የለም፡፡ መንገዱ አንድ ነው፤ ለጥምር ሰራዊታችን ደጀን ሆኖ ወያኔን ለግብአተመሬት ማብቃት፡፡ ያ ካልሆነ እጣችን ወቅት እየጠበቅን በደም ጎርፍ መታጠብ፣ የመከራ አዝመራ ማጨድ ነው፡፡ እኔ ከጥምር ሰራዊታችን ጋር ነኝ፤ ያለ እነሱ መስዋእትነት ነገ እንደሌለ አውቃለሁ፡፡

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ESAT WORLD posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share