
29/09/2025
የወረኢሉ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኛ ህብረት የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።
ወረኢሉ፦የወረኢሉ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኛ ህብረት የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት ኮንፈረንስ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረኢሉ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባህሩ በፓርቲያችን ቆራጥ አመራር ሰጭነት እንድሁም በአባላችን ተጋግዞ መስራት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችለናል በማለት በክልላችን ብሎም በወረዳችን የተፈጠረውን የሰላም እጦት በሰላማዊ ሁኔታ እንድቋጭ ፓርቲው የተለያዩ የሰላም አማራጮችን እያቀረበ ይገኛል ብለዋል።