18/10/2025
የዚህ ሳምንት መጨረሻ ሽንፈት የሚያስከትለው መዘዝ የኖቲንግሃም ፎረስት ዋና አሰልጣኝ አንጌ ፖስቶኮግሎ ላይ የሚጠፋ አይሆንም።
ስለ እግር ኳስ አሰልጣኝነት ያለውን የጨከነ ባህሪ የሚያውቅ ካለ፣ አውስትራሊያዊው ነው።
ከአምስት ወራት ባነሰ ጊዜ በፊት፣ ፖስቶኮግሎ ቶተንሃም በዩሮፓ ሊግ እንዲያሸንፍ ትልቅ ስራ መስራቱ የሚዘነጋ አይደለም ፤ በዚህም የክለቡን የ17 ዓመታት የዋንጫ ድርቅ እንድያበቃ አድርጓል።
ከዚያ ከሁለት ሳምንት በኋላ ግን፣ የ60 ዓመቱ አሰልጣኝ ከሥራው ተባረሩ።
አሁን፣ በአዲሱ የፎረስት ሥራቸው፣ ፖስቶኮግሎ እንደገና በአስቸኳይ ምርመራ ውስጥ ናቸው። ሆኖም በዚህ ጊዜ ያለው የሥራ ውጤት ብዙም አያስደንቅም።
ፖስቶኮግሎ ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶን ከተኩ ጀምሮ ባሉት 38 ቀናት ውስጥ ሰባት ጨዋታዎችን መርተዋል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ አንድም ድል ማስመዝገብ አልቻሉም።
ስለዚህ፣ በኃላፊነት ከተሾሙ ወዲህ ባሉት አምስት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ - ቅዳሜ ከቼልሲ ጋር በሚደረገው ጨዋታ - አራተኛውን ሽንፈት ካስተናገዱ ከሥራቸው የመነሳት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑ እየተነገረ ነው።