ሚስጥረ ደሴ

ሚስጥረ ደሴ 💫 🌷ማህበራዊ ሚዲያ ለበጎ አላማ 🌷💫

💫🌷ቅን ትውልድ እንፍጠር 💫🌷

ደቡብ ወሎ ዞን ሦስት የተለያዩ የተፈጥሮ ሀይቆች የሚገኙ ሲሆን በስፋት ትልቁ ሎጎ ሀይቅ ነው። ሌሎቹ ሁለቱ የተፈጥሮ ሀይቆች አርድቦ እና ማይባር ይባላሉ። ሎጎ እና አርድቦ ሀይቆች በተሁለደሬ...
07/12/2025

ደቡብ ወሎ ዞን ሦስት የተለያዩ የተፈጥሮ ሀይቆች የሚገኙ ሲሆን በስፋት ትልቁ ሎጎ ሀይቅ ነው። ሌሎቹ ሁለቱ የተፈጥሮ ሀይቆች አርድቦ እና ማይባር ይባላሉ። ሎጎ እና አርድቦ ሀይቆች በተሁለደሬ ወረዳ የሚገኙ ሲሆን ማይባር ሀይቅ ደግሞ በአልብኮ ወረዳ ይገኛል። አርድቦ ከሀይቅ ከተማ በስተምስራቅ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ማይባር ሀይቅ ከደሴ ከተማ በስተደቡብ 23 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

የወሎው ሎጎ ሀይቅ ገበታ ለሀገር ሪዞርት

28/03/2017
እሁድ

06/12/2025

👉የተሻሻለው መመሪያ
👉የመንግስት ሰራተኞች መመሪያ
👉ሃላፊነታችንን እንዴት እንወጣ pdfከታች ባለው የቴሌግራም ግሩፓችን ያገኛሉ።

የተፈላጊ ችሎታ አያያዝና አጠቃቀም መመሪያ  ጥራዝ   5 # የቀጠለTelegramhttps://t.me/+M4R8fNTK_hMxYzU0
02/12/2025

የተፈላጊ ችሎታ አያያዝና አጠቃቀም መመሪያ ጥራዝ 5
# የቀጠለ

Telegram

https://t.me/+M4R8fNTK_hMxYzU0

29/11/2025

😂🌹🌹 ባለ አንካሳ ልብ ሯጭ 🌹🌹

ቅልጥም ለማደንደን ቅቤ ከምትጠጡ፣
ጋሬጣን ለማምለጥ ጫማ ከምትመርጡ፣

❤ የልብ ወጌሻ አምጡ፤❤

አንካሳ ልብ ያለው ምን በእግሩ ቢሮጥም፣
ቢያብርር አይዝም ቢሮጥ አያመልጥም ።

በውቀቱ ስዩም

ኗሪ አልባ ጎጆዎች !

29/11/2025

ጎሠሳ ሰላም

ማጭድ ይሆነን ዘንድ ምንሽር ቀለጠ ፣
ዳሩ ብረት እንጅ ልብ አልተለወጠ ፣
ለሳር ያልነው ስለት እልፍ አንገት ቆረጠ፤
ለእንጨት ያልነው ስለት እልፍ እጅ ቆረጠ።

👉 በውቀቱ ስዩም የአሳት ዳር ወጎች
ኗሪ አልባ ጎጆዎች።

እንደው የግጥሙ መመሳሰል ገርሞኝ ነው።

18/11/2025

ደሴን መውደድ ማለት ልማቶቿን መቃወም አይደለም።
የደሴ ልጅ ልዩ መገለጫ ባህሪው አገር ወዳድነቱ እና በሳልነቱ ነው በምክንያት ያምናል የማንም ድብቅ ፖለቲካ ማራመጃ አይደለም።

ምንም ነገር ሳይፈርስ የሚለማ ከተማ የለም
የትናንቷን እና የአሁኗን አዲስ አበባ ተመልከት ። ታዲያ ትልልቅ ህንፃዎች ሳይፈረሱ የተመሰረተ መሰለህ።

ደሴ ከተማ ላይ ሰሞኑን ደሴ ላይ የዘመቱት እናማን ናቸው ....?
- ደሴን በደንብ የማያውቃት
- መሬት ተሸጦ አለቀ የሚሉት እነማን ናቸው መሬትን ያላግባብ በዘረፋ ይዘው ወደ ከተማ መሬት ባንክ ገብቶ በሊዝ ስለተሸጠ ታዲያ ከተማ ልማት ከየት ይንጣ ?

ደካማ ፖለቲካኞችና ደካማ ባለሃብቶች ተቀናጅታችሁ መሪን ለማጥላላት ብትሞክሩም አንሰማችሁም።

- የደሴ ከተማ እንቁ ትልልቅ ባለሃብቶች አስመጭና ላኪዎች ኢንቨስተሮች ወንድም እህቶቻችን ከደሴ በተሰደዱ ከ30 አመት በሁዋላ አሁን እየመጡ ደሴ ደሴ እያሉ ነው ።
በድብቅ ወደስልጣን ለመምጣት ሰሞኑን ሶሻል ሚዲያውን የሚንጡትን በጥብቅ እንታገላለን ሜዳው ለሁላችንም እኩል ነው በምክንያት ኑ ጠይቁ የመልማት ጥያቄ መጠየቅ መብታችን ነው።
ተዘረፈ አያልክ የምትጮህም ና አስኪ በመረጃ
ኮሪደር ልማትን ለማጣጣል በፎቶ ሾፕ ለማቆሸሽ መሞከር ግን ከንቱነት ነው።

ልማት በመሪ ብቻ አይመጣም በሁላችንም ትበብር ነው ። እኛ ምን አግዘናል ይቀድማል ።

መልካም ቀን

🌹ኮሊደር ልማት በአማራ ክልል ከተሞች🌹
13/11/2025

🌹ኮሊደር ልማት በአማራ ክልል ከተሞች
🌹

04/11/2025

🌹🌹የኛ ተወዳጅ ደሴ ከተማ 🌹🌹

የቀሚስሽ ጥለት ጥልፉ በዝቶበታል፣
የሰራው ሸማኔ ይጠየቅበታል።

የወሎዋ እምብርትና አድባር ደሴ ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል  አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቷን ጨርሳ በትግበራ ሙከራ ላይ ትገኛለች። በክቡር ጠ/ሚኒስተራችን ዶ/ር አቢይ አህመድ ኢኒቨቲቭ የተጀመ...
28/10/2025

የወሎዋ እምብርትና አድባር ደሴ ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቷን ጨርሳ በትግበራ ሙከራ ላይ ትገኛለች።

በክቡር ጠ/ሚኒስተራችን ዶ/ር አቢይ አህመድ ኢኒቨቲቭ የተጀመመረው የደሴ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ለግንባታ እና ለቴክኖሎጅ አቅርቦት እንዲሁም ለሲስተም ዝርጋታ ስራ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ በነሀሴ ወር/2017 መጨረሻ አካባቢ ተጀምሮ ሌሊት ጭምር በመስራት በአጭር ጌዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በኢትዮ ቴሌኮም አማካኝነት የቴክኖሎጂ የሲስተም ዝርጋታ ስራውም አብሮ ተዘርግቶ ተጠናቋል።
በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ስራዎች ተጠናቀው በዘመናዊ መልኩ የተዘረጋውን ሲስተም ተጠቅመን አገልግሎት የመጀምር የሙከራ ትግበራ ላይ እንገኛለን ።

ከተቋማቶች የስራ ባህሪ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የአገልግሎት መጓተት ይስተዋልባቸዋል ተብለው የተጠኑ 16 ሴክተሮች እና ከ70 በላይ በሚሆኑ የአገልጎግሎት አይነቶች የምንጀምር ሲሆን ወደፊት ተጨማሪ ግንባታዎችን እያካሄድን ተጨማሪ ተቋማቶች እና አገልግሎቶች የሚጨምሩ ይሆናል።

መሶብ አንድ ማዕከል አግልግሎት እንድገቡ የሚደረጉት ተቋማት በአስተዳደር ወሰን የሚገደቡ ሳይሆን ሌሎች መቀመጫቸው ደሴ ከተማ ላይ የሆኑ ከደሴ የከተማ አስተዳደር ውጭ ያሉ እስከ የፌደራል ተቋማት ጭምር ገብተው አገልግሎት እንድሰጡ በተቀመጠው የበላይ አካላት አቅጣጫ መሠረት እንድፈፀም ጥረት የሚደረግ ይሆናል።
ለምሳሌ:-
- ንግድና ገበያ ልማት ላይ ያሉ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- ገቢዎች ተቋም ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- ኢንቭስትመንት ተቋም ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- ወሳኝ ኩነት ተቋም ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- መሬት መምሪያ ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- ጤና ተቋም ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- ህንፃ ሹም ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- ፍትህ ተቋም ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- ደ/ወሎ ዞን ትራንስፖርት ተቋም ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶች
- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮ ቴሌኮም
- ኢሚግሬሽን
- የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት
- መብራት ሀይል
በዚህ መሠረት ተጠንተው ወደ መሶብ አንድ ማዕከል እንድገቡ የተደረጉት ሴክተሮች ካላቸው ጠቅላላ አገልግሎት መካከል የተመረጡና የተጠኑ አገልግሎቶች ብቻ ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ገብተው በቴክኖሎጅ ተደግፈው ፈጣንና ቀልጣፋ እንድሁም ከብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት እንድሰጡ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራችንን ጨርሰን ዋናው ግባችን ወደሆነው ወደ ሙከራ ትግበራ ገብተናል። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ማረጋገጫችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሲስተም ዝርጋታ ስራው የተሳካ ስለመሆኑ ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በተደረገው የሙከራ ትግበራ ማረጋገጥ መቻላችን ነው።

በመሠረቱ ግባችን ግንባታውን እና የቴክኖሎጅ ዝርጋታ ስራውን ማጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን የህዝባችንን ጥያቄቄ የሆነውን አገልግሎታችንን ማሻሻል ነው።

በመሆኑም ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እየተደረገ ያለው ጥረት የትግበራ ሙከራ ተደርጎ የተሳካ በመሆኑ የከተማችን ማህበረሰብ ይህ ዘመናዊ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት አሰጣጥ የግንባታ ስራውም ሆነ የሲስተም ዝርጋታው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል ደረጃ ላይ ለመድረስ በመብቃታችን እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን በቀጣይ ቅርብ ቀናት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የከተማችን ማህበረሰብ በተገኙበት የተሟላ አገልግሎት እየተሰጠ ከሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር ተቀናጅቶ የምረቃ ስነ-ስረአቱ የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በትዕግስት እንድትጠብቁን ለመግለፅ እንወዳለን።
ልማት ወዳዱ ህዝባችን ሁሌም የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ እንድቀጥል ጥሪ እናቀርባለን።

ከደሴ ከተማ አሰተዳደር ክብር ከንቲባ ሳሙዔል ሞላልኝ ገፅ
የየወሰደ ።

12/10/2025

Address

Dessie

Telephone

+251900098502

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሚስጥረ ደሴ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share