ደራሮ 2016 መረጃ ጌዴኦ ዲላ Dararo News media Gdeo Dilla

  • Home
  • Ethiopia
  • Dilla
  • ደራሮ 2016 መረጃ ጌዴኦ ዲላ Dararo News media Gdeo Dilla

ደራሮ 2016 መረጃ ጌዴኦ ዲላ Dararo News media Gdeo Dilla የደራሮ በዓል 2016 ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ዲላ�

17/05/2025
በጌዴኦ ዞን ቡሌ ወረዳ በተፈጥሮ ሀብት ልማት በCALM ፕሮግራም ድጋፍ የንዑስ ተፋሰስ በማህበር በተደራጅ አርሶአደሮች የተሰራ ስነአካላዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃ የጠረጴዛማ እርከን ጌዴኦ ዞን/ቡ...
05/05/2025

በጌዴኦ ዞን ቡሌ ወረዳ በተፈጥሮ ሀብት ልማት በCALM ፕሮግራም ድጋፍ የንዑስ ተፋሰስ በማህበር በተደራጅ አርሶአደሮች የተሰራ ስነአካላዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃ የጠረጴዛማ እርከን

ጌዴኦ ዞን/ቡሌ ወረዳ ቀበሌ 1ኛ ኦኮሉ
ሚያዝያ 27/2017
#ዲላ

የቋቁቻ መንስኤዎችና መፍትሄዎቹ | Pityriasis Versicolor🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉✅ የቋቁቻ መንስኤ እና መፍትሄዎች🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️...
26/04/2025

የቋቁቻ መንስኤዎችና መፍትሄዎቹ | Pityriasis Versicolor
🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

✅ የቋቁቻ መንስኤ እና መፍትሄዎች
🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️

ቋቁቻ ማላሴዚያ (Malassezia) በሚባል የፈንገስ ዓይነት የሚመጣ ሲሆን፤ አብዛኛውን ጊዜ ወጣቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነው።

ይህ የፈንገስ አይነት በሁላችንም ሰዉነት የሚገኝ ሲሆን፤ ለምን አንዳንድ ሰዎች ላይ ብቻ በሽታዉን እንደሚያመጣ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር የለም።

ይህ በሽታ ገርጣ ገርጣ ወይም ጠቆር ጠቆር በሚሉ የቆዳ ለውጦች ተለይቶ ይታወቃል።

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

አብዛኛውን ጊዜ ደረትና ጀርባን የሚያጠቃ ሲሆን፤ አልፎ አልፎ ፊት፣ እጅና እግርን ሊያጠቃ ይችላል።

ቋቁቻ በአብዛኛው በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ወይም የአየር ንብረት የሚከሠት ሲሆን በይበልጥ ወንዶችን ያጠቃል።

አብዛኛዉን ግዜ ምልክት ባይኖረዉም አንዳንድ ግዜ ግን ልያሳክክ ይችላል፤ ይሁንና ቋቁቻ ከሰዉ ወደ ሰዉ አይተላለፍም።

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

ቋቁቻ በብዛት ሊከሰት የሚችል ከሰዉ ወደ ሰዉ የማይተላለፍ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ
ላይ ችግር ነው።

ፈንገሱ የቆዳ ተፈጥሮዊ መልክን በማሳጣት ትናንሽ፣ ነጣ ወይም ጠቆር ያሉ መልካቸዉን የለወጡ ነገሮች በቆዳ ላይ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

ሞቃታማ እና እርጥበት አዘል የአየር ፀባይ፣ ወዛማ ወይም ቅባታማ ቆዳ ካለዎት፣ የሆርሞን ለውጦች፣ የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም መዳከም ቋቁቻ እንዲከሰት የሚያደርጉ ሁኔታዎች ሲሆኑ፤ ቋቁቻን በሚቀቡ እና በሚዋጡ የተለያዩ መድሃኒቶች ማከም ይቻላል።

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

ሆኖም ግን ሁኔታዎች ሲመቻቹለት ቋቁቻ የመመለስ ወይም የማገርሸት ባህሪ አለው።

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

✅ የቋቁቻ ሕክምና
🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️

ቋቁቻ በፈንገስ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ችግር ስለሆነ የሚከተሉት መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡

የተወሰኑት መድሃኒቶች በቆዳ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ሲሆን ቀሪዎቹ የሚዋጡ ናቸው።

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

1️⃣ የፍሉኮናዞል እንክብል ወይም ፈሳሽ መድሃኒት።
2️⃣ ኢትራኮናዞል (እንክብል፣ ካፕሲዩል ወይም ፈሳሽ)።
3️⃣ ኬቶኮናዞል (ክሬም፣ ጄል ወይም ሻንፖ) ናቸው።

ምንም እንኳን ህክምናዉን በደንብ ቢከታተሉትና ህመሙ ቢሻልዎትም ለሳምንታት ወይም ለወራት የቆዳዎ ቀለምዎ ሳይለወጥና እንደሻከረ ሊቀጥል ይችላል፡፡

አንዳንዴ ደግሞ ህመሙ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል (በተለይ በሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ወቅት)፡፡

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

ስለሆነም ኢንፌክሽኑ ተመልሶ እንዳይመጣ መድሃኒት በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ መውሰድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

➖〰️➖〰️➖〰️
መልካም ጤንነት!!
➖〰️➖〰️➖〰️

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

🟪 ጠቃሚ መረጃ ነውና ለወዳጆችዎ ያካፍሉ 🟪

👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉

➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️
ምንጮች | Sources
➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️
Health line, NIH &

26/04/2025

የ2017 ተጠባቂ አፈፃፀሞች

በያዝነው አመት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በታቀደው መሠረት በ8.4% የሚያድግ መሆኑን የሥራ አስፈጻሚው ገምግሟል፡፡ በዘርፍ ደረጃ ደግሞ ግብርና በ6.1%፣ ኢንዱስትሪ በ12.8%፣ ማኑፋክቸሪንግ በ12.0%፣ ኮንስትራክሽን በ12.3%፣ አገልግሎት ደግሞ በ7.1% የሚያድጉ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡ ያለፉት 9 ወራት ጠቅላላ የመንግሥት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ134% ብልጫ አሳይቷል፡፡ የውጭ ብድር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 13.7% ወርዷል፡፡ ወደ ውጭ ገበያ የሚቀርቡት ስድስት ዋና ዋና ምርቶች፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ ከ82%-386% ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ በስንዴ፣ በሩዝ፣ በቡና፣ በሻሂ ቅጠል እና በፍራፍሬ ምርቶች በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ለመውጣት እየተደረገ ያለው ትግል ፍሬ እያፈራ መሆኑን አይተናል፡፡

26/04/2025

ፕሮጀክቶች እና ስኬቶቻችን

ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን በጊዜና በተገቢ ደረጃ ለማጠናቀቅ የተሰጠው አቅጣጫ ብዙዎችን ለፍጻሜ እያበቃቸው ነው፡፡ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 98.66 ደርሷል፡፡ የኮይሻ፣ አይሻና አሰላ የኃይል ማመንጫዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሠረት እየተጓዙ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታም የኢትዮጵያን ነገ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የቅድመ ዝግጅት ምእራፉ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የኮሪደር ልማት በአዲስ አበባ በ8 ኮሪደሮች እና በመላው ኢትዮጵያ በ65 ከተሞች እየተከናወነ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ ብዙዎቹ የመስኖ ግድቦች ወደ ፍጻሜያቸው እየደረሱ ናቸው፡፡ ከዘጠኙ የመስኖ ግድቦች ውስጥ ስድስቱ አፈጻጸማቸው ከ75 በላይ ደርሷል፡፡

የ 10 አገራት የመገበያያ ገንዘብ በአሜሪካ ዶላር የዛሬ ሽያጭ (ምንዛሬ) ዋጋ ከዚህ እንደሚከተለው ነው፦ ⩩1| ኢትዮጵያ ➔  1 dollar = 133.45 Birr (ብር¹)2| ቬትናም ➔ 1 ...
26/04/2025

የ 10 አገራት የመገበያያ ገንዘብ በአሜሪካ ዶላር የዛሬ ሽያጭ (ምንዛሬ) ዋጋ ከዚህ እንደሚከተለው ነው፦



1| ኢትዮጵያ ➔ 1 dollar = 133.45 Birr (ብር¹)

2| ቬትናም ➔ 1 dollar = 26,021.47 d**g

3| ኢንዶኔዥያ ➔ 1 dollar = 16,828.56 Rupiah

4| ማሌዥያ ➔ 1 dollar = 3,841.79 Rupiah

5| ኡጋንዳ ➔ 1 dollar = 3,665.60 Shilling

6| ታንዛኒያ ➔ 1 dollar = 2,686.67 Shilling

7| ናይጀሪያ ➔ 1 dollar = 1,608.72 Naira

8'| ደቡብ ኮሪያ ➔ 1 dollar = 1,440.83 won

9| ፓኪስታን ➔ 1 dollar = 280.95 Rupee

10| ኬንያ ➔ 1 dollar = 129.50 Shilling

[ወዳጄ ልቤ!...]

➊ የኢትዮጵያ ብር የወደቀ ነው የሚሉህ የወደቁ ናቸው። የኢትዮጵያ ብር ከወደቀ የቬትናም፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ፣... ብር ምን ሊባል ነው? አስቀድሜ የጠቀስኳቸውን ሃገራት ጠቅል ሃገራዊ ምርት፣ የኢኮኖሚ ደረጃ፣ የገቢ መጠን፣... ወዘተ ትንሽ Browse አድርገህ አንብብ...

➋ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምርታማ አይደለም። 85% ህዝባችን በግብርና ላይ ተሰማርቷል ብለን ስናበቃ ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ስንዴ ስንገዛ ነበር። በአፍሪካ በቀንድ ከብት አንደኛ ነን ብለን ስናበቃ ስጋ ከኬንያ እንገዛለን። ሸራተን ሆቴል እና Sky light hote ስጋ የሚገዙት ከኬንያ ነው 🤔 መንግስት ምርት እናምርት፣ የከተማ ግብርና፣ የበጋ ስንዴ፣ የሌማት ትሩፋት፣... ወዘተረፈ የሚለው ምርትና ምርታማነታችንን ለማሳደግ የዳቦ ቅርጫታችንን ለመሙላት ነው።

ዛሬም ዘይት ከውጭ ገዝተን እናስገባለን። ጫማ፣ ልብስ፣ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጸጉር ቅባት፣ መድሃኒት፣ የቤት ቁሳቁስ፣ ነዳጅ፣ አትክልትና ፍራፍሬ (ሽንኩርት ሳይቀር 😂)፣ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ ከእነመለዋወጫው፣ ማሽነሪ፣ ወዘተረፈ በውጭ ምንዛሬ ገዝተን የምናስገባ ጉዶ'ች ነን።

[መፍትሄው]

[ሀ] ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ ማምረት፣

[ለ] የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ብዙ ምርት ወደውጭ መሸጥ፣

[ሐ] ማምረት! ማምረት ! አሁንም በጥራትና በብዛት ማምረት !

💰

¹ - የዛሬ ዓመት 1 dollar እስከ 250 ብር ሊደርስ ይችላል።

ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሣዔ በዓልን በአብሮነትና በመረዳዳት ማሳለፍ ይገባዋል - የኃይማኖት አባቶችሚያዝያ 11፣ 2017   ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሣዔ በዓልን በአብሮነትና በመረዳዳት በጋራ ማሳ...
19/04/2025

ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሣዔ በዓልን በአብሮነትና በመረዳዳት ማሳለፍ ይገባዋል - የኃይማኖት አባቶች

ሚያዝያ 11፣ 2017

ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሣዔ በዓልን በአብሮነትና በመረዳዳት በጋራ ማሳለፍ እንደሚገባው የኃይማኖት አባቶች ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል፣ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሀፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ እና የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፖስተር ጻድቁ አብዶ የትንሳኤ በዓልን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በመግለጫቸው፤ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር በድንበር ለተሰማሩ ወታደሮች፣ በተለያዩ የዓለማት ክፍል ለሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮችና ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የትንሣዔ በዓል እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ፍቅሩን የገለጸበት ትህትናን ያስተማረበት መሆኑን ገልጸው፤ በዓሉን ሲከበር ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና አንድነት በመጸለይ እንዲሁም የተቸገሩትን በመርዳት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በዓሉ ለተቸገሩት ካለን የምናካፍልበት እና አብሮነታችንን የምናሳይበት ሊሆን ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል የትንሣዔ በዓል የትህትናና የመከባበር እሴታችንን የምናሳይበት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ትንሣዔ ጥላቻ በፍቅር፤ መለያየት በአንድነት፤ ሐዘን በደስታ የተቀየረበት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍቅር የተገለጠበት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሀፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ የትንሣዔን በዓል ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በማሳለፍ የክርስቶስን ፍቅር ማሳየት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ትንሣዔ የተጣሉ የሚታረቁበት፤ የተራራቁ የሚቀራረቡበት እንዲሆን ታርቆ በማስታረቅ መልካም ምሳሌ መሆን እንደሚገባ ገልጸው፤ የኢትዮጵያን ሰላም እና የህዝቦቿን አንድነት በጽኑ ዓለት ላይ ለማቆም በመከባበርና መደማመጥ ላይ የተመሰረተ ውይይትና እርቅ የግድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፖስተር ጻዲቁ አብዶ፤ የትንሣዔን በዓል በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሣዔ ድረስ ያደረጋቸው ተግባራት ለእኛ ለሰው ልጆች ትህትናና ፍቅርን የሚያስተምሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ክርስቶስ ለእኛ የከፈለውን መስዋዕትነት በማሰብ ምዕመናን የተራቡትን በማብላት የተጠሙትን በማጠጣት የታረዙትን በማልበስና የተቸገሩትን በመርዳት ማሳላፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ምዕምናን የትንሣዔ በዓልን ለኢትዮጵያውያን አንድነትና ዘላቂ ሰላም በመጸለይ እንዲያከብሩ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

19/04/2025

#ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱሰ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

#መልካም በዓል!

#ሰላማችሁ ይብዛ!

😁የማስታወስ ችሎታን በ75% የሚጨምረው ሮዝሜሪ ወይም የጥብስ ቅጠል!!=========================በሀገራችን በተለይ በገጠራማው ክፍል የስጋ መጥበሻ ወይም ሮዝሜሪ በመባል የሚጠራው...
19/04/2025

😁የማስታወስ ችሎታን በ75% የሚጨምረው ሮዝሜሪ ወይም የጥብስ ቅጠል!!
=========================
በሀገራችን በተለይ በገጠራማው ክፍል የስጋ መጥበሻ ወይም ሮዝሜሪ በመባል የሚጠራው ቅጠል በየጓሮው እናስተውላለን፤ ነገር ግን ጠቀሜታው ጊቢ ከማሳመርና አልፎ አልፎ ስጋ ሲጠበስ እንደማጣፈጫነት ከመጠቀም በዘለለ እንብዛም አይታወቅም፡፡

ሮዝሜሪ ወይም የጥብስ ቅጠል ምንድን ነው?
ሮዝሜሪ ለጤና ብዙ ጠቀሜታ አለው፡፡

ጥናታቸውን ሮዝሜሪ ላይ ያደረጉ ባለሙያዎች በቅርቡ ባወጡት መረጃ የማስታወስ ችሎታን 75 ከመቶ ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ይህ ተክል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችም አሉት፡፡
ሮዝሜሪ ለምግብ ማጣፈጫነትም በስፋት ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡

በአብዛኛዉም ለስጋ ጥብስ ጥሩ መአዛ እና ጠአምን ስለሚሰጥ ለስጋ መጥበሻነት ያገለግላል።

የጥብስ ቅጠል የሚለዉን ስያሜም ያገኘዉ ከዚሁ አገልግሎቱ የተነሳ ነዉ።

የሮዝሜሪን የዘይት ፋብሪካዎችም ዘይት ለማምረት በጥሬ እቃነት ይጠቀሙታል፡፡

የሮዝሜሪ ተክል የማስታወስ ችሎታን የማሳደግ ሚስጥር አዲስ ግኝት አይደለም።
የዚህን ተክል የማስታወስ ችሎታን ማሰደግ በጥንት ዘመን ስነጽሁፎች ዉስጥ ሳይቀር ተገልጾ ይገኛል፡፡

ስለዚህ ተክል በዊልያም ሼክስፔር ሀምሌት መጽሀፍ ላይ ተጽፎ እናነባለን፡፡

በጥንት ጊዜ በጋብቻ ስነስርአት ላይ እንደ መታሰቢያ መልክት ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡

በተጨማሪም በአውሮፓ እና በአውስትራሊያ የጦርነት መታሰቢያ ምልከት አድርገው ይጠቀሙበት ነበር፡፡

ሀዘንተኞችም ባለቁልፍ ልብስ በመልበስ፤ እጣን በማጨስ እና ሮዝሜሪ ወደ ᎂች መቃብር በመወርወር መታሰቢያ ስርአት ያደርጉ ነበር፡፡
ይህ የሮዝሜሪ ተክል በርግጥ የቆየ እና የጥንት ባህል ቢሆንም መነሻው ግን በመካከለኛው ዘመን ከአረቡ አለም ወደ ሳይንሳዊ እሳቤነት እንዳደገ ይገመታል፡፡

የተለያዩ ሳይንቲስቶች ባጠኑት ጥናት ሮዝሜሪ የማስታወስ ችሎታን ለማሳደግ ጠቃሚ እንደሆነ ነው፡፡

በ2012 ዓ.ም በአማካኝ 75 አመት እድሜ ያስቆጠሩ ሰዎች ላይ በተደረገ ጥናት የደረቀ የሮዝሜሪ ቅጠል ዱቄት እንዲጠቀሙ በማድረግ የሚያስደንቅ ውጤት ተገኝታል፡፡

በዚሁ ጥናት ላይ የሮዝሜሪ ዘይት የማስታወስ አቅምን በሚያስደንቅ ሁኔታ እስከ 75 በመቶ የማሳደግ አቅም እንዳለው ተረጋግጧል፡፡

ሌሎች የጥብስ ቅጠል የጤና ጥቅሞች የአፍ ጠረንን ለማስወገድ የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል
ካንሰርን ይከላከላል የማይግሬን ህመምን ያስታግሳል
የፀረ ባክቴሪያነት ጥቅም በሽታን የመከላከል አቅምን ያዳብራል::

19/04/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሀንታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ! ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ የትንሳኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደምከተለው አስተላልፏል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን በመስቀል ተሰቅሎ፣ ሞቶ መነሣቱ የሚታሰብበት ይህ በዓል፣ የጌታን ለሰው ልጅ ያለውን ጥልቅ ፍቅር የተገለጠበት በመሆኑ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ“እኔ እንደወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህቺ ናት”ዮሐ 15፡12 የሚለውን ቅዱስ ቃል በማሰብ እርስበርስ በመዋደድና በመተሳሰብ በድምቀት ይከበራል።

የእምነቱ ተከታዮች ኃይማኖታዊ አስተምሮውን በመከተል በሀገራችን ያለው የመከባበር፣ የአብሮነትና የመረዳዳት መልካም እሴት እንዲጎለብት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ እያሳሰብኩ ለመላው ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ! አመሰግናለሁ!

11/04/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል።

Address

Dilla

Telephone

+251910206600

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደራሮ 2016 መረጃ ጌዴኦ ዲላ Dararo News media Gdeo Dilla posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ደራሮ 2016 መረጃ ጌዴኦ ዲላ Dararo News media Gdeo Dilla:

Share