13/09/2025
አገልጋዩ በድንገተኛ አደጋ አረፉ!!
በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ቀጠና ቃለ ህይወት ቤ/ክ ሰብሳቢ፤ የጌዴኦ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ሥራ አስፈፃሚና አባል፤ የይርጋ ጨፌ ቃለ ህይወት አጥቢያዎች ህብረት ዋና ፀሐፊና በተለያዩ የወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ የነበሩት አገልጋይ አቶ ዮናስ ቼካ በድንገተኛ አደጋ (ሽንት ቤት ተደርምሶ) ከዚህ ዓለም ድካም ወዳገለገሉት ጌታ ሄደዋል።
ለቤተሰቦቻቸዉ፤ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለመላዉ የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ምመንና ለይርጋ ጨፌ ከተማ ነዋሪዎች መጽናናትን እንመኛለን!!