10/09/2022
ብሶት የወለደው አበባየሁሽ
(በላይ በቀለ ወያ)
ሀ" ብለን መጣን ፣ "ሀ" ብለን
እስከመቼ እህ "ሆ" እንላለን
"ሀ" ብለን መጣን "ሀ" ብለን
።።።
አበባ አየሁሽ ለምለም ምሩን በተራ
ስልጣን አግኝተን ለምለም እኛ እስንመራ
እንኳንስ ስልጣን ለምለም የለኝም እጣ
እደጅ አድራለሁ ለምለም ኦቨር ስጠጣ
ምጠጣው ደግሞ ፣ አይደለም ጠጅ
ደጅ ያፈራውን ለምለም ብርድ ነው እንጅ😂
።።
አደይ
የኛስ ጉዳይ
ውይ ስቃይ
እቴ አበሳ እቴ አበሳዬ
አዬ እቴ አበሳዬ
ለውጥ ለውጥ ስትለኝ ከርማ
አዬ እቴ አበሳዬ
መብራት ሀይል ሁሌ ጨለማ
አዬ እቴ አበሳዬ
ውሃ ልማት ውሃ ሚያስጠማ
አዬ እቴ አበሳዬ
ይሁን ኑሮ ከተባለማ
አዬ እቴ አበሳዬ
።።።
እዬዬ
እህ
ሁሌ እዬዬ
ሲዘርፉኝ ሲቀሙኝ ፣ ጊዜ ይፍረድ ብዬ
ሀገር ያህል ነገር ፣ ከመንደር ላይ ጥዬ
በገዛ ፍርሃቴ ፣ ቀረሁ ተቃጥዬ
።
ከብረው ይቆዩን ከብረው
የሚሰብሩንን ሰብረው
የሚያፍኑንን አስረው
ከብረው ይቆዩን ከብረው