Visit Dire

Visit Dire ድሬ የፍቅር ሀገር

25/08/2026

መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው የፖሊስ አባላት ስሜትን የሚነካ ንግግር

🚨 ሰበር ዜና (Breaking News) - አርጀንቲናየእግር ኳሱ ንጉሥ የሊዮኔል መሲ አባት ጆርጅ መሲ (Jorge Messi) በ68 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። 💔አባት ጆርጅ መሲ ከዜ...
08/08/2026

🚨 ሰበር ዜና (Breaking News) - አርጀንቲና

የእግር ኳሱ ንጉሥ የሊዮኔል መሲ አባት ጆርጅ መሲ (Jorge Messi) በ68 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። 💔

አባት ጆርጅ መሲ ከዜሮ ቀን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በሊዮ ሕይወት ውስጥ — በሙያውም ሆነ በግል ሕይወቱ — ሁልጊዜ ከጎኑ በመሆን ትልቅ አምድ ነበሩ።

🕊️ በሰላም ዕረፍ፣ ጆርጅ! 🕯️

👏 የጋራ ጥረትና የቅንጅት ውጤት!የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከአጎራባች የፀጥታ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ላስመዘገበው የላቀ ስኬትና ላገኘው እውቅና እንኳን ደስ አላችሁ!...
29/07/2026

👏 የጋራ ጥረትና የቅንጅት ውጤት!

የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከአጎራባች የፀጥታ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ላስመዘገበው የላቀ ስኬትና ላገኘው እውቅና እንኳን ደስ አላችሁ! የተቀናጀ አሰራር ለቀጠናችን ሰላም ዋስትና ነው!

"ለሕዝባችን ሰላም ሲሉ ቀንም ማታም ለደከሙት የጸጥታ ኃይሎቻችን እና ለተባባራችሁ የከተማችን ነዋሪዎች ሁሉ ልባዊ ምስጋና ይገባል። ሰላማችን ዘላለም ይጸና! 🙏"
26/07/2026

"ለሕዝባችን ሰላም ሲሉ ቀንም ማታም ለደከሙት የጸጥታ ኃይሎቻችን እና ለተባባራችሁ የከተማችን ነዋሪዎች ሁሉ ልባዊ ምስጋና ይገባል። ሰላማችን ዘላለም ይጸና! 🙏"

የተላለፈ የምስጋና መልዕክት

ለተከበራችሁ የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ መላው ሕዝበ ምዕመናንና እንግዶች፣ የባጃጅ አሽከርካሪዎች፣ የፀጥታ ኃይሎች እና አጋዥ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ፤

በዕለተ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት የተከበረው የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግሥ ምንም ዓይነት የወንጀል ተግባር ሳይከሰት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁት ሁለተናዊ ትብብር የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ከበዓሉ ቀናት በፊት ጀምሮ እስከ መጠናቀቁ ድረስ የፀጥታ እቅዳችንን በመቀበል፣ ከጎናችን በመቆም ላሳያችሁት ከፍተኛ ኃላፊነት ምስጋና ይገባችኋል።

በዓሉ ሕዝባችን ሰላም ወዳድ መሆኑን፣ አንድነቱን፣ ወንድማዊ ፍቅሩን እና በአብሮነት የመኖር የቆየ እሴቱን በድጋሚ ያረጋገጠበት፤ ድሬዳዋ የሰላምና የፍቅር ከተማ መሆኗ ይበልጥ የታየበት ታላቅ ክስተት ሆኗል።

የፀጥታ ግብረ-ኃይሉ፣ የአስተዳደሩ ምክር ቤት፣ መላው ሠራዊት፣ የሌሊት የባጃጅ አሽከርካሪዎች እንዲሁም ተባባሪ ተቋማት በጋራ በመሥራታችን ያስመዘገብነው ይህ ውጤት ለቀጣይ ሥራዎቻችን ትልቅ ምዕራፍ ነው።

ለዚህ ሁሉ ሰላም መረጋገጥ በግልና በተቋማ ደረጃ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ!

ሰላማችን የጸና፣ ፍቅራችን የዘላለም ይሁን!


የድሬዳዋፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ

09/07/2026
09/07/2026

ወዳጅህን ለማስደሰት አታርፍድ...

22/06/2026

Abela🙏🙏

10/05/2026

Waaaw...

የአመራር ጥበብ በሰብዓዊነት ሲመዘን!! ኮሚሽነር አለሙ መግራ እና የሠራዊት ፍቅር!​"መሪ ማለት በሹመት ከፊት የሚቀደም ሳይሆን፣ በመከራ ቀን ለሠራዊቱ ጋሻ፣ በደስታው ቀን ደግሞ አጋዥ የሚሆ...
10/05/2026

የአመራር ጥበብ በሰብዓዊነት ሲመዘን!!

ኮሚሽነር አለሙ መግራ እና የሠራዊት ፍቅር!
​"መሪ ማለት በሹመት ከፊት የሚቀደም ሳይሆን፣ በመከራ ቀን ለሠራዊቱ ጋሻ፣ በደስታው ቀን ደግሞ አጋዥ የሚሆን ደግ አባት ነው!"

​የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ፣ ተቋማቸውን ወደ ላቀ ከፍታ እያሻገሩ የሚገኙት በዕዝ ሰንሰለት ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፣ በልዩ የአመራር ጥበባቸውና ለበታች አባሎቻቸው ባላቸው ጥልቅ ፍቅር ጭምር መሆኑን በተግባር እያስመሰከሩ ይገኛሉ።

​ዛሬ ለሰማዕቱ ኢንስፔክተር እስክንድር ለማ ቤተሰቦች የተረከበው ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ የኮሚሽነሩን "ሰው ተኮር" አመራር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አብነት ነው። ለሀገር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን የሰጡ ጀግኖችን ዝክረ-ነገር በታሪክ ማኅደር ብቻ ሳይሆን፣ በቤተሰቦቻቸው ኑሮ ላይ ተስፋን በመዝራት ማክበር መቻል የታላቅ መሪ መገለጫ ነው።

​ለሀገር መስዋዕት መሆን የክብር መደምደሚያ ነው" ብለው ሲናገሩ፣ መስዋዕት ለከፈሉ አባላት ቤተሰብ መጠለያ በማዘጋጀት ቃላቸውን በተግባር ያፀናሉ።

ለከፍተኛ አመራሩ ብቻ ሳይሆን፣ እስከ ታችኛው የፀጥታ አባል ድረስ ያለውን ሞራል በመገንባት፣ ተቋሙ እንደ አንድ ቤተሰብ እንዲተሳሰር አድርገዋል።

ይህ ቤት በአፈቴ ፖሊስ ጣቢያና በማህበረሰቡ ትብብር እንዲገነባ በማድረግ፣ የፖሊስንና የህዝብን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ አሳድገዋል።

​የኢንስፔክተር እስክንድር ለማ ቤተሰቦች የፈሰሰው እንባ ታብሶ ዛሬ በደስታ ሲሳቁ ማየት፣ ከጀርባው ጠንካራና ሩህሩህ አመራር መኖሩን ያረጋግጣል። ኮሚሽነር አለሙ መግራ "ድሬዳዋ ፖሊስ በጀግንነት ይጠብቃል፤ በሰብዓዊነት ያገለግላል" የሚለውን መርህ በራሳቸው ስብዕና የገነቡ መሪ ናቸው።

​ክብር ለሀገር መስዋዕት ለሆኑ ጀግኖች!
ምስጋና ለሰብዓዊው መሪያችን ኮሚሽነር አለሙ መግራ!

በጎሮ ጉቱ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ‎ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አልፏል።አደጋው ከአዲስ አበባ ወ...
13/04/2026

በጎሮ ጉቱ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ

‎ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ሲጓዝ በነበረ ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በተከሰተው አደጋም እስካሁን የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ነው የተገለጸው፡፡

FBC

Address

Lagaharree
Dire Dawa

Telephone

+252113334

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Dire posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share