27/09/2025
ኦዴጋርድ ለኒውካስትል ጨዋታ እንደሚደርስ አርቴታ ተናገረ
************
ማርቲን ኦዴጋርድ አርሰናል ዕሁድ ከሜዳው ውጭ ከኒውካስትል ዩናይትድ ለሚያደርገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ እንደሚደረስ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ተናግሯል፡፡
በትከሻ ጉዳት የተወሰኑ ጨዋታዎች ያለፉት አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ ልምምድ መስራቱን የገለጸው አርቴታ ለወሳኙ ጨዋታ ዝግጁ መሆኑንም አሳውቋል፡፡
አሰልጣኙ ከዕሁድ ጨዋታ በፊት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከጉዳት የተመለሰው ቡካዮ ሳካም በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልቷል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ