11/12/2025
#ዜና | የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ለፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የድሬዳዋ ሁሉአቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት 500 ያህል መፃህፍት ድጋፍ አበረከተ ።
| ታህሳስ 02 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የንባብ ቀን ፣ ስልጠና እና የፓናል ውይይት በድሬዳዋ ሁሉአቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት ተካሂዷል ።
“የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት" በሚል መሪ ቃል በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የድሬዳዋ ሁሉአቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የተዘጋጀ የንባብ ቀን ፣ ስልጠና እና የፓናል ውይይት ተካሂዷል ።
የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የማረም ማነፅና ተሀድሶ ልማት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ሉባባ ጀማል በወቅቱ እንደገለፁት ማረሚያ ቤት ዘርፈ ብዙ ስራዎች የሚሰራበት ማዕከል እንደሆነ ገልፀዉ ታራሚዎች የፅሞና ጊዜ በመዉሰድ መፅሀፍትን ማንበባቸው ያለዉን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ገልፀዋል።
ኮሚሽነር ሉባባ አከሰለውም ታራሚዎች እራሳቸዉን በእዉቀት ማዳበር እንዳለባቸው አፅዕኖት ሰተዋል፤የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎትንም ላደረጉት ድጋፍም አመስግነዋል ።
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የድሬዳዋ ሁሉአቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ማዕከል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ሙላት ጫንያለዉ በበኩላቸው አገልግሎቱ በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ የህግ ታራሚዎችን የንባብ ባህል ለማሳደግና ታርመው ከህብረተሰብ ጋር ሲቀላቀሉ አምራች ዜጎች ይሆኑ ዘንድ የንባብ ልምዳቸውን እንዲያጎለብቱ ላደረገው ድጋፍ በተቋሙ ስም አመስግነዋል።
ኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ አባተ ካሳዉ በበኩላቸው ማረሚያ ቤት ታራሚዎች የሚታነፁበት እና የሚታረሙበት ለቀጣይ ህይወታቸው የሚዘጋጁበት እራሳቸዉን አስተምረዉ አብቅተዉ የሚወጡበት ማዕከል መሆኑን ገልፀዉ መድረኩ የንባብ ባህልን በማዳበር እራሳቸዉን በእዉቀት እንዲያዳብሩ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።
"ማረሚያ ቤትን በመፃህፍት ማደራጀት እና ንባብ" በሚል መሪ ሀሳብ ገለፃ በደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ እንዲሁ ተሞክሯቸዉን ደግሞ ደራሲና ጋዜጠኛ ኢሳያስ ሆርዶፋ ለታራማዎች አጋርተዋል ።
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ለድሬዳዋ ሁሉአቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት 500 ያህል መፅሐፎችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲተመን ከሁለት መቶ ሰላሳ ሺ ብር በላይ እንደሚሆን ተገልጿል።
በተያያዘም በመድረኩ ወጣቱ ደራሲ ሚካኤል ካሳሁንም የታራሚዎችን ስብዕና ይቀይራል በማለት በስነ አእምሮ ዙሪያ የፃፈዉን ሀያ ሁለት መፃህፍት በስጦታ አበርክቷል ።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር " የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ሳቢያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተዘጋጀ የንባብ ክበባት ምስረታ ላይ በመገኘት ለተማሪዎች ለመማር ማስተማር ምቹ የሆኑ ወደ ሁለት መቶ ሀያ ገደማ መፃህፍትችን ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ አድርገዋል ።
አገልግሎቱ በተጨማሪም ለድሬዳዋ አስተዳደር እምርታ ቤተ መፅሀፍት ስድስ መቶ ስልሳ ስምንት መፃህፍትን በስጦታ አበርክተዋል። ድጋፍ የተደረገላቸዉ አካላት ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል ።
ሰላም ይኄይስ
ምስል፦ሀየሎም አለበል
ተጨማሪ ፥ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፦
👉ፌስቡክ፡-
ለአማርኛ ፦https://www.facebook.com/diretvamharic
ለአፋን ኦሮሞ ፦https://www.facebook.com/share/1B8KihEAkt/
ለአፍ-ሶማሊ ፦https://www.facebook.com/share/199s1kp4Sr/
👉ዩትዩብ ፦
https://www.youtube.com/live/rkHE_fWNmkE?si=TElgNpYHVPxpB77L
👉በቲክታክ ፦
https://vm.tiktok.com/ZMSwgmLny/
👉በቴሌግራም ፦
https://t.me/+6C5aVWGZeL4wOWM0
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!