ድሬ ቶክ ሾው

ድሬ ቶክ ሾው Welcome to our official page Dire talk show. follow us on TikTok dire_talkshow

to unite Ye dire lejoch from all over the world who want to have fun, show love, and have a better understanding of their culture and where they came from.

04/01/2025

#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሰሞነኛ የመሬት መንቀጥቀጥን (ንዝረትን) አስመልክቶ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል።

የጥንቃቄ እርምጃዎች ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል።

የመሬት ንዝረት/መንቀጥቀጥ/ ክስተት ጋር ተያይዞ ከክስተቱ በፊት፣ በክስተቱ ጊዜና ከክስተቱ በኃላ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች፤

በየትኛውም ወቅት የመሬት ንዝረት ወይም መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ ከሁሉም ነገር በፊት አለመሸበር፣ መረጋጋትና ሊወሰዱ የሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችን በጥንቃቄ ማከናወን፤ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን መከታተልና ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም ትክክለኛ ያልሆነና ከትክክለኛ ምንጭ ያልተገኘ መረጃዎችን አለመቀበልና አለማሰራጨት እጅግ ተፈላጊ ባህሪያት ናቸው፤

ማንኛውም ግለሰብና ቤተሰብ የፀጥታና ደህንነት ችግሮች እንዳያጋጥሙ በየአካባቢው ካሉ የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር የመሥራት ኃላፊነት አለበት፡፡ በተጨማሪም በአደጋ ስጋት ምክንያት በተከለሉ አካባቢዎች አለመንቀሳቀስ ተገቢ ሲሆን ከዚህ በታች የተመለከቱት የጥንቃቄ መልዕክቶችም በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ ተግባራዊ መደረግ አለባቸው፡፡

1. የመሬት ንዝረት ከመከሰቱ በፊት፤

• ከቤቱ ወይም ከህንፃው ውስጥ እንዴት መውጣት እንደሚቻልና የት ላይ መሰብሰብና መቆየት እንዳለብን ማወቅ፤
• በአደጋ ወቅት ከጣራ ወይም ከከፍታ ቦታ ከሚወድቁ ቁሳቁሶች ራስን ለመከላከል የሚያስችሉ መከለያዎችን መጠቀመ (ጠረጴዛ፣ ዴስክ፣ ምሶሶ፣ ወዘተ)፤
• የነዳጅ፣ የጋዝ፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ መስመሮች እንዴት ቶሎ እንደሚዘጉ እና እንደሚቋረጥ አስቀድሞ መለማመድ፤
• በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት የሚወድቁና ጉዳት የሚያደርሱ ትላልቅ ዕቃዎችን መለየት፤ አስቀድሞ ማስወገድ፤
• ሊቀጣጠሉ ወይም አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፈሳሾችና ኬሚካሎች ዝቅ ባሉ ካቢኔቶች/ሼልፎች ውስጥ ማስቀመጥ ወይንም ማስወገድ፤
• በአስቸኳይ ጊዜ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ( መድኃኒት፣ የእጅ ባትሪ ፣ ሬዲዮ፣ አልባሳት) መለየትና ማዘጋጀት፤
• በአደጋው ምክንያት የሚበተነው ቤተሰብ እንዴትና የት ቦታ እንደሚገናኝ አስቀድሞ መወሰን፤ (የስልክ ቁጥሮችን መያዝ)፤
• በቀላሉ ለመፍረስ ተጋላጭ ከሆኑ ህንፃዎችና ቤቶች ራስን ቤተስብ ማራቅና በባለሙያ ምክረ ሀሳብ መሠረት ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ መቆየት፤

2. በመሬት ንዝረት ክስተት ወቅት

2.1 በህንፃ ወይም ቤት ውስጥ ከሆነ፡
o ባሉበት ተገረጋግቶ መቀመጥና ሊያዙ የሚችሉ ነገሮችን መያዝ እንዲሁም ጭንቅላትን ከጉዳት መከላከል፤
o ከአንዱ ክፍል/ህንፃ ወደ ሌላ ክፍል/ህንፃ መሮጥ/መንቀሳቀስ አለመሞከር፤
o ከሚወድቁ ቁሳቁሶች ራስን ለመከላከል በቀላሉ በማይሰበሩ መከለያዎች (በጠረጴዛ፣ በዴስክና በምሶሶዎቸ፣ በአልጋ) ስር ጎንበስ ብሎ ራስን መከላከል፤
o በመስኮት ወይም በሊፍት ለማምለጥ ወይም ለመውረድ አለመሞከር፤
o ፊትን ወደ በር በማዞር ከመስኮት፣ መስታወቶችና ከከባድ ቁሳቁሶች በመራቅ መቆም፤
o የመሬት መንቀጥቀጡ እስከሚቆም ድረስ ባሉበት ቦታ ተረጋግቶ መቀመጥና አለመንቀሳቀስ፤

2.2 ከቤት ውጪ ከሆነ፡

o ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሮጥ/መንቀሳቀስ አለመሞከርና የመሬት መንቀጥቀጡ እስከሚቆም ድረስ አለመንቀሳቀስ፤

o ከህንፃዎች፣ ከዛፎች ከግድግዳዎች፣ ከኃይል ማመንጫ መስመሮችና ምሶሶዎች፣ ወዘት በመራቅ ክፍት ቦታ ወይም ሜዳማ በሆኑ ቦታዎች ዝቅ በማለትና ሚዛንን በመጠበቅ መቀመጥ/መቆም፤

2.3 በማሽከርከር ላይ ከሆነ (የንዝረት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ)

o በማሽከርከር ወቅት ክፍት ቦታ መምረጥ፣ በፍጥነት ማቆም፣ ሞተር ማጥፋትና የደህንነት መጠበቂያ ህጎችን ጠብቆ በተሸከርካሪው ውስጥ መቆየት፣

o ተሸከርካሪውን በመተላለፊያ መንገድ ወይም ድልድይ ላይ ወይም በኃይል ማመንጫ መስመር ስር አለማቆም፤
o አስቸጋሪ ሆኖ የግድ ከተሸከርካሪው መውጣት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከተሸከርካሪው በመውጣት ወደ በሜዳማ ቦታ መቆየት፤

3. ከመሬት ንዝረት ክስተት በኋላ

• የመሬት መንቀጥቀጥን ተከትሎ ሊነሱ ከሚችሉ የእሳት አደጋ፣ የመሬት መንሸራተት፣ የውሃ አደጋዎች እና ሌሎች አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ (የኃይል ማመንጫ ምሶሶዎችና መስመሮች፣ እሳት፣ ኬሚካል፣ መርዛማ ነገሮች፣ ሊወድቁ የሚችሉ ነገሮች) ነገሮች መኖራቸውን ማረጋገጥና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትል ጥንቃቄ ማድረግ፤

• የተጎዱ/የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጠት፣ የተጎዱ/የቆሰሉ ሰዎችን በጥንቀቄ እና በፍጥነት ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፤

• የህንፃ መሠረቶች፣ ግድግዳዎች፣ ጣራዎች፣ የጭስ መውጫዎች፣ መሰነጣጠቃቸውንና መጎዳታቸውን ማረጋገጥና ሌላ ጉዳት እንዳያስከትል ጥንቃቄ ማድረግ፤

• የንዝረቱ ወይም የመሬት መንቀጥቀጡ የሚቀጥል መሆኑ ከታወቀ ወደ ተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ መቆየት አካባቢው አደገኛ መሆኑ ከተረጋገጠ ሌላ ጊዜያዊ መጠለያ በማዘጋጀት ከአካባቢው መራቅ፤
• ለአስቸኳይ ጊዜ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ፍላጎቶች ምግብ፣ ውሃ፣ አልባሳትና መድኃኒት መኖራቸውን ማረጋገጥ፤

• ከዋናው ንዝረት/ መንቀጥቀጥ ተከትሎ ሊከሰት ከሚችል ዳግም የመሬት ንዝረት /መንቀጥቀጥ/ በቂ ዝግጅት ማድረግ፤

16/12/2024

የድሬዳዋ አስተዳደር የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሆኑት ከክብርት ወ/ሮ ሽኩሪ አቡድረህማን ጋር በቶክ ሾ ው ዝግጅት የተደረገ ቆይታወቅታዊ፣....

19/08/2024
17/08/2024
16/08/2024
03/05/2024

ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!
****

09/04/2024

እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል-ፊጥር ረመዳን በዓል፥ በሰላም እና በጤና አደረሰን/አደረሳችሁ።

ያሳለፍነው የረመዳን ጾም ወር ፥ ዋነኛ ሥርዓቶች ከሆኑት የፀሎት እና የስግደት መንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ ፥ በብዙ የበረከት ሥራዎች የታጀበ ወር ነበር። የዘንድሮ ረመዳን እና የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዐቢይ ጾም አንድ ቀን ላይ በመጀመሩ፥ ጥንትም በ'ትንሿ ኢትዮጵያ' ድሬዳዋ ህብረተሰብ ውስጥ የኖረው የፍቅር እና አብሮነት ውብ እሴት፥ በይበልጥ ደምቆ መታየቱ የማይካድ ሀቅ ነው።

የነገዋ የኢድ ዕለት... በረመዳን የጾም ወር የፈፀምናቸውን የአንድነት፥ የእዝነት፥ የመረዳዳት እና ሌሎች በርካታ መልካም እሴቶች አጠንክረን፥ በቀጣይ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ለማስቀጠል ለራሳችን ቃል የምንገባበት ልዩ ቀን መሆኗን ሁላችንም ልብ ልንገነዘብ ይገባል።

'ረመዳን ሙባረክ' ብለን የጀመርነውን የጾም፥ የፀሎት እና የስግደት ወር በሰላም እንድንጨረስ ለረዳን ፈጣሪ ምስጋና እያቀረብኩ፥ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ በዓሉ የፍቅር፥ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። ኢድ ሙባረክ!

Baga Nagayaan ayaana Ramadaanaa Iid al-Fxir kan Bara 1445ffaatiin, Nagayaafii Fayyaadhaan nu gahe isin gahe.

Ji’ini soomana Ramadaanaa kan dabarsine ji’a araaramaa, ji'a kadhannaa fi Salaataa, akkasumaas ji'a hujiilee Rabbi biratti jaalataaman kan gara garaa ittiin hojjachuudhaan dabaalamee ture. Baatiin Ramadaana baranaatiifi baatiin Soomana-Abiy kan kiriistaanaa waliin walqixa guyya tokko jalqabamuu isaaniitiin Jaalaltii fi dudhaan waliin jiraachuu kan hawaasa 'Itiyoophiyaa xiqqoo' Dirree Dhawaa teenyaa keeysa dur irraa jalqabee ture daran ifee kan ittiin mullate ture.

Guyyaan Iida boruu Guyyaa addaa kan nuti dudhaa waliin jiraachuu, kan tokkummaa, kan gara laafinaa, kan wal gargaarsaa daran jabeeysuudhaan hujilee biroo kanneen ji'a Ramadaanaa keeysa hojjanne gaggaarii tana Jireenya keenya kan itti aanuu keeysatti cimsinee akka itti fufnuuf waadaa guyyaa itti seennuudha.

Ji'ni somaanaa kan 'Ramadaan Mubaarek' waliin jenne jalqabne kan somaanaa, kan salaataatiifi kan kadhaa tahee akka xumuramu kan nu godhee Rabbii keenya guddaaf galata galchaa Hordooftoota Amantaa Islaamaa maraaf ayyaanni kun kan jaalalaa, kan wal-gargaarsaa fi tokkummaa akka isiniif tahuun hawwa. Iid Mubaarak!
~~~~~~~~~

Waxaan idiinku hambalyeynayaa munaasabada ciidal fidri ee sannada 1445 ee tirsiga hijriga.

Bishan waxay ahayd bil wadata shaqooyin barako leh kasokow ducada iyo salaada aan oognay. Sannadkan kulanka ay kulmeen labada soon ee islaamka iyo masiixinyiinta waxa ay sii qurxiyeen dhaqanka ay caanka ku tahay magaalada 'Itoobiyada yar ee' Diri dhaba.

Ciida bari ah waa maalin aan ka qaadanayno shidaal aan kusii xoojinayno waxbixinta, isutudhida iyo howlihii kale samafalka si aan dhaqan uga dhigano.

"Ramadan mubarak" anagoo isugu hambalyeynayno ayey bishani noo bilaabatay hadana waan dhamaysanay cibadadeedii Alle ayaana mahadaas leh Waxaanan idiinku hambalyeynaya mar kale munaasabada ciidal fidriga oo aan idiin rajaynayo inay idiin noqoto mid caafimaad iyo farxad aad ku ciidaan. Ciid mubarak!

08/04/2024

Vacancy
=======
Commercial Bank of Ethiopia would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following positions:
1. Senior Psychiatry Nurse
2. Senior Biomedical Engineer
3. Neurologist
4. Radiologist
5. Gynecologist
6. Specialist Physician (Internist)
7. General Practitioner
8. Junior Pharmacy Service Officer
9. Junior Psychiatry Nurse

Interested and qualified job seekers should apply through CBE career website
( https://vacancy.cbe.com.et ) from April 08 - 14, 2024.

For requirements and other detail information, please use the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/External_Vacancy_97b7ef4f03.pdf

በነገው እለት እንደሚከሰት የሚጠበቀው የጸሀይ ግርዶሽ በነገው እለት ከፊል ወይም ሙሉ  የጸሀይ ግርዶሽ ወይም ሶላር ኢክሊፕስ በበርካታ የአለም ሀገራት እንደሚከስት ይጠበቃል።ሙሉ የጸሀይ ግርዶ...
07/04/2024

በነገው እለት እንደሚከሰት የሚጠበቀው የጸሀይ ግርዶሽ

በነገው እለት ከፊል ወይም ሙሉ የጸሀይ ግርዶሽ ወይም ሶላር ኢክሊፕስ በበርካታ የአለም ሀገራት እንደሚከስት ይጠበቃል።

ሙሉ የጸሀይ ግርዶሹ የሚከሰተው በአሜሪካ ውስጥ በጠባብ ኮሪደር ሲሆን የተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራትም ከፊል ግርዶች እንደሚታይባቸው ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።

ጸሀይ በጨረቃ ሙሉ በሙሉ ስትጋረድ የተወሰነው የሰሜን አሜሪካ ክፍል ሙሉ በሙሉ በጨለማ ይዋጣል። ጨረቃ በጸሀይ ስትሸፈን የሚያሳየውን ድንቅ ክስተት በሜክሲኮ ፖስፊክ ጠረፍ ያሉ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይመለከቱታል ተብሏል።

ሙሉ የጸሀይ ግርዶሹ የሚከሰተው በአሜሪካ ውስጥ በጠባብ ኮሪደር ሲሆን የተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራትም ከፊል ግርዶች ይታይባቸዋል ተብሏል

07/04/2024

!
'ትንሿ ኢትዮጵያ' 🇪🇹 ድሬዳዋ

"ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን
ለውጡንም እናፀናለን ! " በሚል መሪ ሀሳብ፥ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተገኙትን አገራዊ ድል እና ስኬቶች ለማስቀጠል፥ የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪ በአንድነት መቆሙን የሚያረጋግጥበት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ፥ ነገ አርብ መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ጀምሮ በለገሀር ምድር ባቡር አደባባይ ይካሄዳል።

Address

Ras Agez
Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ድሬ ቶክ ሾው posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share