Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት

Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት welcome to the OFFICIAL Mesrak Sport | ምስራቅ ስፖርት is one of GSMN
ሀገራዊ ስፖርት በልዩነት!

27/07/2025
27/07/2025
4ኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት በስፖርታዊ ፌስቲቫል
27/07/2025

4ኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት በስፖርታዊ ፌስቲቫል

ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ !በድሬዳዋ ከተማ ቀዳሚ የሴቶች ቡድን መስራች እና ከድሬዳዋ ከነማ ወንዶች ቡድን ጋር አይረሴ ጊዜን ያሳለፈችው እና የድሬዳዋ ከተማ የስፖርት ቤተሰብ ዘንድ አሁን ድ...
27/07/2025

ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ !

በድሬዳዋ ከተማ ቀዳሚ የሴቶች ቡድን መስራች እና ከድሬዳዋ ከነማ ወንዶች ቡድን ጋር አይረሴ ጊዜን ያሳለፈችው እና የድሬዳዋ ከተማ የስፖርት ቤተሰብ ዘንድ አሁን ድረስ ተወዳጅ የሆነችው ከድሬዳዋ እስከ ፈረንሳይ የተሻገረ ስኬትን ያስመዘገበችው ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ ከድሬ ሶከር ጋር ያደረገቸውን ቆይታ እንሁ ።

ድሬ ሶከር - እራስሽን አስተዋውቂን ?

መሰረት - መሰረት ማኔ እባላለው ተወልጄ ያደኩት ድሬዳዋ ልዩ ስሙ አንደኛ መንገድ በሚባል አካባቢ ነው ።

ድሬ ሶከር - እግር ኳስን እንዴት ጀመርሽ ?

መሰረት - እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጨርቅ ኳስ ከወንድ ጓደኞቼ ጋር አሸዋ በመጫወት

ድሬ ሶከር - በተጫዋችነት ህይወትሽ የመጀመሪያ ክለብሽ የት ነበር ?

መሰረት - በኔ ዘመን የእግር ኳስ ክለብ አልነበረም ነገር ግን ለድሬዳዋ ምርጥ ቡድን ተጫውጫለሁ ከእግር ኳስ ውጪ በርካታ ስፖርቶች ላይ ተሳትፌ ውጠታማ ነበርኩ በሩጫ በመረብ ኳስ በእጅ ኳስ ድሬዳዋን ወክዬ ለጨርቃ ጨርቅ ክለብ እንዲሁም ለትምህርት ቤት ተጫውቻለሁ ።

ድሬ ሶከር - በተጫዋችነት የት የት ክለብ ተጫውተሽ አሳልፈሻል ?

መሰረት - ቀደም ብዬ ለማንሳት እንደሞከርኩት እግርኳስን በምጫወትበት ወቅት የሴቶች እግር ኳስ ክለብ አልነበረም በመረብ ኳስ ለድሬዳዋ ጨርቃ ጨርቅ ተጫውቼ አሳልፊያለው ።

ድሬ ሶከር - ወደ አሰልጣኝነት ህይወትሽ እንምጣ ወደ አሰልጣኝነት ሞያው ለመግባት ምን አነሳሳሽ ?

መሰረት - ድሬዳዋ በእግር ኳሱ ኢትዮጵያ ብራዚል ነች እግር ኳስ የሚወደድባት የሚዘወተርባት ነው ሁሉም ይጫወታል ሁሉም ያፈቅራል እኔ ደግሞ እግር ኳስን ከህጻንነቴ ጀምሮ የምወደው የምጫወተው ነው በዚህ ላይ የመምራት ተሰጥኦ ስላለኝ አብሬአቸው የምጫወታቸውን ወንድ ጓደኞቼን በማሰልጠን ጀመርኩ።

ድሬ ሶከር - እስካሁን በአሰልጣኝነት ያሰለጠንኳቸው ክለቦች ?

መሰረት - በአማተር ቡድን ህንጻ ራዳ ባርነን የወንድና ሴት ቡድነ መድን በፕሮፌሽናልነት የድሬዳዋ ምርጥ ሴት ቡድን ድሬዳዋ ከነማ ሴትና ወንድ ቡድን አዲስ አበባ ከነማ ኢትዮ ኤሌትሪክ አሁን ደግሞ መቻል ስፖርት ክለብ በእግር ኳስ
በመረብ ኳስ የድረዳዋ ምርጥ ቡድን አሰልጥኛለሁ ።

ድሬ ሶከር - በድሬዳዋ እንደ ህንፃ ያሉ ቀደምት ክለቦችን በአሰልጣኝነት እንደመራሽ ስላንቺ ያሰባሰብናቸው ደጋፊ ማስረጃዎች ያሳያሉ የድሬዳዋ እግርኳስ በዛን ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ተምሳሌት የሚታይ የእግርኳስ ስርአት ነበራት እስቲ ስለ ወቅቱ የድሬዳዋ እግርኳስ ጥቂት አስታውሺን ?

መሰረት - የድሬዳዋ እግር ኳስ ቀደምት የነበረው እጅግ የሚያስደስት በየሰፈሩ በብዛት የሚካሔድበት ከየሰፈሩ በርካታ ተጨዋቾች የሚፈሩበት በርካታ ውድድሮች የሚከናወኑበት በሁሉም የእድሜ እርከን የመጫወትና የመወዳደር እድል እንዲያገኙ የሚደረግበት እግር ኳስ እግር ኳስ የሚሸትበት ወቅት ነበር

ድሬ ሶከር - ኢንስትራክተር የድሬዳዋ ከነማ ሴቶች ቡድን መስራች እና ቀዳሚ አሰልጣኝ እንደ ነበርሽ ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ ስለ ጊዜው ጥቂት አስታውሺን ?

መሰረት - እውነት ነው 2003 ዓ/ም የድረዳዋ ምርጥ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኜ ዝዋይ ከተማ ይካሔድ በነበረው የክልል ሻምፒዮና ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረውን ቡድን በዋና አሰልጣኝነት እየመራሁ ይዤ ሄጄ በውድድሩ ለዋንጫ ቀርበን 2ተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀን ወደ ድሬዳዋ ስንመለስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሁሉም በፕሪሚየር ሊግ ላይ የሚሳተፍ ቡድን የሴት ቡድን መያዝ አለበት በማለት ውሳኔ ይወስናል ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለድሬዳዋ ከነማ አመራሮች ጥያቄ አቀረብኩ ጥያቄዬን ተቀበሉኝ በ2004 ዓ/ም የድሬዳዋ የሴት ቡድን በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተመዝግቦ መወዳደር ጀመረ በወቅቱ ድሬዳዋ ከነማን ይመሩ የነበሩት አቶ አብዱሰላም አቶ ፉአድ መሐመድ አቶ ዳንኤል የኋላሸትን ማመስገን እወዳለሁ ።

ድሬ ሶከር - የድሬዳዋ ከነማ የወንዶች ዋናውን ቡድን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕርሚየር ሊግ በማሳደግ እና ወደ ፕርሚየር ሊጉ ባደገበትም አመት ተፎካካሪ የሆነ እና ውብ እግርኳስን የሚጫወት ክለብ የሰራሽ ብቸኛ እንስት አሰልጣኝ ነሽ እና የድሬዳዋ ከነማ የወንዶች ቡድንን በሁለት የሊግ እርከኖች ስኬታማ ጊዜን አሳልፈሻል በክለቡ የቆየሽባቸውን ጊዜያት እንዴት ተገልጫቸዋለሽ ?

መሰረት - በጣም ጥሩ ጊዜአት ነበረኝ በተለይ የክለቡ አመራሮች በወቅቱ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበረው የአሁኑ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የክለቡ ስራ አስኪያጅ እንዲሁም ተጨዋቾቼ ለኔ የነበራቸው መልካም ተግባራቸው ለውጤታማነቴ ከፍተኛ ድርሻ ነበረው በዚህ ላይ የድሬዳዋ ህዝብ ድጋፍ ሁልጊዜ በውስጤ የሚኖር ነው ።

ድሬ ሶከር - ከድሬዳዋ ከነማ የወንዶች ቡድን ስለለቀቅሽበት ጊዜ እናንሳ በወቅቱ ከክለቡ ትለቂያለሽ የሚል ሀሳብ በብዙ የስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ አልተጠበቀም ነበር ክለቡን የለቀቅሽበትም መንገድ ግልፅ አልነበረም ምክንያቱም ክለቡ እንደ ክለብ መጥፎ ጊዜን አላሳለፈም ነበር እስቲ በወቅቱ ስለተፈጠረው ነገር ጥቂት አስታውሺን ?

መሰረት - እውነት ነው ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት በመራሁበት ጊዜ መጥፎ ጊዜአትን አላሳለፍኩም ውብ የሆነ እግር ኳስ የሚጫዋት በከፍተኛ ጫናና ፐሬስ እያደረገ የሚጨዋት ፍላጎት ከተጋጣሚ የሚበልጥ በመከላከሉም በማጥቃቱም የተሻለ ደጋፊውን የሚያስደስት ለአስር ሰዓት ጨዋታ ደጋፊው አራት ሰዓት ላይ ሜዳ ለመግባት ስቴዲዮም ተገኝቶ ሰልፍ የያዘበት ጌዜ ነበር ይህ ለኔ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል፡፡ የለቀቅሁት በራሴ ፈቃድ ነው የለቀቅሁት ያልተመቹኝ ነገሮች ስለነበሩ ነው ።

ድሬ ሶከር - ከድሬዳዋ ከነማ ከተላያየሽ ወዲህ በቅርብ አመታት በድጋሜ ጥሪ እንደቀረበልሽ ይነገራል ምን ያህል እውነት ነው ? ጥሪው ከቀረበልሽስ ውድቅ አድርገሽው ነው ?

መሰረት - እውነት ነው ከአንድም ሁለት ጊዜ የተለያዩ አመራሮች በግል አናግረውኝ ነበር ወደ ከነማ እንድመለስ ጥያቄ ቀርቦልኝ ተነጋግረን ፍቃደኛ ነበርኩ ግን በዛው መልስ ሳይሰጡኝ ቀሩ ።

ድሬ ሶከር - ከድሬዳዋ ከነማ ከተለያየሽ በውሀላ ቀጣይ ማረፊያሽ የት ነበር ?

መሰረት - ድሬዳዋን ከለቀኩ ከአንድ ወር በኋላ የኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ እንድሆን ተመረጥኩ።

ድሬ ሶከር - ኢንስትራክተር ከስልጠናው ባሻገር እራስሽን በየጊዜው ለማሻሻል የሚጠበቅብሽን ርቀት ሁሉ ከመጓዝ አልፈሽ ኢትዮጵያ ላሉ አሰልጣኞች የሞያ ማሻሻያዎችን ስትሰጪ እንመለከታለን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ጥቂት ኢንስትራክተሮች መካከልም አንዷ እንደሆንሽ ይታወቃል ከክለብ አሰልጣኝነት ወደ አሰልጣኞች አሰልጣኝ እንዴት ተሸጋገርሽ ?

መሰረት - የአሰልጣኝነት ኮርስ ስንውስድ በካፍ ያለንን አቅም ተምልክተው አምስት ሴት ኢንስትረክተሮችን እነድንሆን እድሉ ተሠጠን በዛ አጋጣሚ እራሳችንን እና የሞያ አጋሮቻችንን የምናሻሽልበት እና እውቀታችንን የምናሳድግበት እድል ተፈጠረ ያን እድል መሬት በማውረድ ለአሰልጣኞች የሞያ ማሻሻያ ስልጠናዎችንም እየሰጠሁ እገኛለው ።

ድሬ ሶከር - በፈረንሳይ ሊዮን ከተማ አንድ ሽልማት አግኝተሽ ነበር ምክንያቱ ምን ይሆን ?

መሰረት - መሲ ድሬ የእግርኳስ አካዳሚ በመመስረቴ ።

ድሬ ሶከር - ባለፉት ጥቂት አመታት በኢትዮ ኤሌትሪክ የሴቶች ቡድን ጥሩ ቆይታ እንዳደረግሽ እና ከሊጉ ሀይል ከሚባለው ክለብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እስከ መጨረሻ ሳምንታት ለሊጉ ዋንጫ የሚፎካከር ቡድን አሳይተሻል በኢትዮ ኤሌትሪክ ስኬታማ ጊዜን እንድታሳላፊ ምክንያት የሆነሽ ነገር ምንድነው ?

መሰረት - እኔ ሁልግዜ ለስራዬ ከፍተኛ ትኩረት እሰጣለሁ በትጋትና በጥንካሬ ነው ስራዬ የምሰራው ተጨዋቼ በአካልም በአእምሮም ጠንካራ እነዲሆኑ በክፍል ውስጥ በተደጋጋሚ አዘጋጃቸዋለሁ በተጨማሪ ለጆቼ ቤውድድሩ ያላቸውን አውጥተው ይጫወታሉ መስዋት ይከፍላሉ የሚነገራቸውንና የሰሩትን በሜዳ ይተገብራሉ ።

ድሬ ሶከር - በኢትዮ ኤሌትሪክ ስኬታማ የውድድር አመታትን ካሳለፍሽ በውሀላ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከመቻል ጋር አዲስ ጉዞ ለማድረግ ፋርማሽን እንዳኖርሽ እኛም በተደጋጋሚ መረጃዎችን አድርሰናል በ218 የውድድር አመት ከመሲ እና ከመቻል ምን እንጠብቅ ?

መሰረት - ተፎካካሪ ጠንካራ ቡድን በማዘጋጀት የተሻሉ ውጤቶችን ለማስመዝገብ በጥንካሬ እሰራለሁ ።

ድሬ ሶከር - ኢንስትራክተር በበርካታ ክለቦች ስኬታማ ቆይታን አድርገሻል እስካሁን የነበሩሽን የስልጠና ወቅቶች እንዴት ትጋሪያቸዋለሽ ።

መሰረት - እውነት ነው እስካሁን ባሰለጠንኩባቸው ክለቦች በአጠቃላይ ጥሩ ሚባል ቆይታን አድርጊያለው ሀልጊዜም አሸናፊ ቡድን መገንባት ነው የኔ ፍላጎት በማሸነፍ ደግሞ ያገኘሁት ደስታ ነው ይሄን ስኬት ለማስቀጠል አሁንም እሰራለው ።

ድሬ ሶከር - በመጨረሻ ማስተላለፍ የምትፍልጊው መልእክት ካለ ወይም ማመስገን የምትፈልጊው መልእክት ካለ ?

መሰረት - ድሬዳዋ በእግር ኳሱ አሁን የተጀመረውን እንቅስቃሴና መነቃቃት ይበልጥ አጠናክሮ ክለቦችነ ከአማተርነት ወደ ፕሮፌሽናለነት በመቀየር ተጨዋቾች በደመወዝ የሚጫወቱበት ሁኔታዎች መፍጠር ያስፈልጋል በተጨማሪ በየእድሜ እርከኑ ውድድሮችን በሁለቱም ጾታ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ፡፡ በመጨረሻ ከሁሉም አስቀድሜ የደንግል ማሪያም ልጅ ልኡል እግዚያብሔርን አመሰግናለሁ፡፡
እኔ የብዙዎች ውጤት ነኝ በአሰልጣኝነትም በተጨዋችነት ባሰለፍኩባቸው ጊዜአት በርካቶች ድጋፍ አድረገውልኛል
ቤተሰቦቼ በተለይ እናቴ የሰፈር ልጆች እና ጓደኖቼ በተለያዩ ጊዜ ያሰለጠንኳቸው ተጨዋቾቼ መላው የድሬዳዋ ህዝብን አመሰግናለው የእሁድ እንግዳ አድርጎ የጋበዘኝን ድሬ ሶከርን ከልብ አመሰግናለው ።

[ በኦርቢ ድሬ ሶከር የተዘጋጀ ]

Mesrak SPORT l ምስራቅ ስፖርት

27/07/2025
27/07/2025

👉ሰበር ዜና....ሰበር ዜና....ሰበር ዜና.....

📌በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና በ2025 የቶኪዮ የአለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ስም ዝርዝር እጃችን ገብቷል

📌44 አትሌቶች በቶኪዮ አለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ

📌ጀግናዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በሁለት ውድድሮች ሀገሯን ትወክላለች

📌ቀደም ሲል ይፋ እንዳደረግነው ታምራት ቶላ ከቶኪዮው አለም ሻምፒዮና ውጪ ሆኗል

📌ከነገ(ሠኞ) ጀምሮ በሆቴል ተሰባስበው ልምምድ ይጀምራሉ

✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ትናንት(ቅዳሜ)ባደረገው ስብስባ እ.ኤ.አ ከSeptember 13 አስከ 21/2025 በጃፓን ቶኪዮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው 20ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሀገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች ስም ዝርዝር እጃችን ገብቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገና ይፋ ያላደረገውና እጃችን እንደገባው የቶኪዮ 2025 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳታፊዎች ዝርዝር መረጃ መሠረት 27 ሴቶችና 17 ወንዶች በድምሩ 44 አትሌቶች መመረጣቸውን ማረጋገጥ ችለናል።

ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ቀደም ሲል በቶኪዮ አለም ሻምፒዮና ሀገራቸውን ሊወክሉ፣100% ሊመረጡ ይችላሉ ብላ ያመነችባቸውን አትሌቶች በመስፈርቱና በባለሙያ ታግዛ ያቀረባች ሲሆን ምርጫዋም ከ95% በላይ እንደ ግምታችን የተሳካ ሆኖ ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ኮሚቴ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ በመስፈርቱ መሠረት ከመረጠ በኃላ በቃለ-ጉባኤ ተፈራርሞ ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ካቀረበ በኃላ ከምሽት 11:30 ጀምሮ ብረርቱ ውይይትና ክርክር ካደረገ በኃላ ውሳኔውን እንዳሳለፈ ነው የተሠማው።በተለይ አትሌት ጉዳፍ ካላት ወቅታዊ ብቃትና ሚኒማ አንፃር በሁለት ርቀት ትሩጥ?አትሩጥ?የሢለው ክርክር ያስነሳ ሲሆን ቀደም ሲል በቃለ-ጉባኤ ጭምር አንድ አትሌት በአንድ ርቀት ብቻ ነው የሚሮጠው ብለን ነበር በሚል የሃሳብ ልዩነቶች እንደነበሩ ከምንጮቻችን ሠምተናል።

እስከአሁን በተገኘውና በተረጋገጠው መረጃ መሠረት ጀግናዋ አትሌት ጉዲፍ ፀጋይ በሁለት ርቀቶች ማለትም የወቅቱ የ10ሺ ሻምፒዮን በመሆንዋ በግብዣ በ10ሺ እንዲሁም በ5ሺ እንድትሮጥ የተወሠነ ሲሆን በቀጣይ ከአትሌቷና ከአሠልጣኟ ጋር በሚደረግ ውይይት 5ሺ ቀርቶ በተጠባባቂነት በተያዘችበት በ1500 ሜትር ልትሳተፍ የምትችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ተብሏል።

በመጨረሻም የመጨረሻ ምዝገባ (Final Conformation) ሲካሄድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ት አትሌቶች ከተመረጡበትና ከሚወዳደሩት የውድድር ምድብ ተጨማሪ ሁለቴ እንዲሮጡ በተጠባባቂነት እንዲመዘገቡና ፌዴሬሽኑ በመጨረሻ ባለው የመወሠን ስልጣን ወይም እንደሚያመጡት ሜዳልያ አይነት በድጋሚ እንዲሮጡ ውሳኔ ላይ ደርሷል ስራ አስፈፃሚው፡-

በዚህም መሠረት
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5000 ሜትር፣ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1500 ሜትር እና አትሌት ቢኒያም መሀሪ በ10,000 ሜትር እሰከዛ በተጠባባቂነት እንዲያዙ ሆኗል።

ፌዴሬሽኑ ገና ይፋ ያላደረገውና እጃችን በገባው መረጃ መሠረት በተለያዩ ርቀቶች በወንድም በሴትም ሀገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መሆናቸው ተረጋግጧል፤

ከነገ ሠኞ ጀምሮ ወደ ሆቴል እንዲገቡና ልምምዳቸውን እንዲያደርጉም ተወስኗል፤እጃችን በገባው የዕጩ አትሌቶቾ ምርጫ መሠረት:

📌በሴቶች 5,000ሜትር

🏃‍♀,1.ጉዳፍ ፀጋይ ⏰ 14:04:41 በሚኒማ

🏃‍♀,2.ፍሬወይኒ ሀይሉ⏰ 14:19:33 በሚኒማ

🏃‍♀3.ጫልቱ ዲዳ ⏰14:27:11 በሚኒማ
-------------------------------------------------
👉🏃‍♀4.(ተጠባባቂ) አለሽኝ ባወቀ ⏰ 14:27:33 በሚኒማ
-----------------------------------------------
📌በወንዶች 5,000ሜ

🏃‍♂1.ቢኒያም መሀሪ⏰ 12:45:93 በሚኒማ

🏃‍♂2.ኩማ ግርማ ⏰ 12:46:41 በሚኒማ

🏃‍♂3.ሐጎስ ገብረህይወት ⏰ 12:46:82 በሚኒማ
-----------------------------------------------
👉ተጠባባቂዎች
-------------------------------------------------
🏃‍♂4.መዝገቡ ስሜ ⏰ 12:49:80 በሚኒማ

👉 ቢኒያም መሀሪና ዮሚፍ ቀጄልቻ አነሱም አሠልጣኞቻቸውም እንዲቀያየሩ ማለትም ዮሚፍ በ5ሺ ቢኒያም መሀሪ በ10ሺ እንዲወዳደሩ ስለሚፈለግ የውድድር ርቀትና የቦታ ልውውጥ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

📌በሴቶች 10,000ሜ

🏃‍♀ጉዳፍ ፀጋይ ⏰ 29:05:92 Wild Card(ቀጥታ ተጋባዥ)

🏃‍♀,1.መዲና ዒሣ ⏰ 29:25:00 በሚኒማ

🏃‍♀,2.ፎቴን ተስፈዬ⏰ 29:47:71 በሚኒማ

🏃‍♀3.ፅጌ ገብረሠላማ ⏰ 29:48:34 በሚኒማ
---------------------------------------------
👉ተጠባባቂ
------------------------------------------------
🏃‍♀ 4.አይንአዲስ መብራቱ ⏰30:09:05 በሚኒማ
---------------------------------------------------------
📌በወንዶች 10,000ሜ

🏃‍♂1.ዬሚፍ ቀጄልቻ⏰ 26:31:01 በሚኒማ

🏃‍♂2.በሪሁ አረጋዊ ⏰26:31:13 በሚኒማ

🏃‍♂3.ሰለሞን ባረጋ ⏰26:34:93 በሚኒማ
-----------------------------------------
👉ተጠባባቂ
-------------------------------------------
🏃‍♂4.ቢንያም መሀሪ ⏰26:37:93 በሚኒማ
----------------------------------------------
ቢሆኑም ቢኒያም መሀሪና ዮሚፍ ቀጄልቻ አነሱም አሠልጣኞቻቸውም እንዲቀያየሩ ዮሚፍ በ5ሺ ቢኒያም በ10ሺ እንዲወዳደሩ ስለሚፈለግ የቦታ ልውውጥ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

📌በወንዶች ማራቶን

🏃‍♂1.አትሌት ደሬሳ ገለታ በሚኒማ

🏃‍♂2.አትሌት ታደሰ ታከለ በሚኒማ

🏃‍♂3.አትሌት ተስፋዬ ድሪባ በሚኒማ
-----------------------------------------
👉ተጠባባቂ
-------------------------------------------
አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ በሚኒማ
---------------------------------------------
📌በሴቶች ማራቶን

🏃‍♀አማኔ በሪሶ በ Wild Card ቀጥታ ተሳታፊ

🏃‍♀1.አትሌት ትዕግስት አሰፋ በሚኒማ

🏃‍♀2.አትሌት ስቱሜ አሰፋ በሚኒማ

🏃‍♀3.አትሌት ያለምዘርፍ የኃላው በሚኒማ
---------------------------------------------------
👉ተጠባባቂ
-----------------------------------------------------
🏃‍♀4.አትሌት ትዕግስት ከተማ በሚኒማ
-------------------------------------------------------
📌በ3ሺ መሠናክል ወንዶች በሚኒማ

🏃‍♂1.ሳሙኤል ፍሬው 8:05:61 በሚኒማ

🏃‍♂2. ለሜቻ ግርማ 8:07:01 በሚኒማ
🏃‍♂3.ጌትነት ዋለ 8:07:57 በሚኒማ
---------------------------------------------
👉ተጠባባቂ
------------------------------------------------
🏃‍♂4.አብርሃም ስሜ 8:07:92 በሚኒማ
-----------------------------------------------
📌በ3ሺ መሠናክል ሴቶችች

🏃‍♀1.ሲምቦ አለማየሁ 8:59:90 በሚኒማ

🏃‍♂2. ሎሚ ሙለታ 9:06:07 በሚኒማ

🏃‍♂3. አለምነት ዋሌ 9:06:88 በሚኒማ
---------------------------------------------
👉ተጠባባቂ
------------------------------------------------
🏃‍♂4. ወሠኔ አሠፋ WR በኮታ
-----------------------------------------------
📌በ1500 ወንዶች

🏃‍♂.1. አትሌት መለሠ ንብረት WR በኮታ

🏃‍♂.2. አትሌት ኤርሚያስ ግርማ WR በኮታ

🏃‍♂.3. አትሌት ወገኔ አዲሱ WR በኮታ
---------------------------------------------
👉ተጠባባቂ
------------------------------------------------
🏃‍♂4. አትሌት አብዲሳ ፈይሳ WR በኮታ
-----------------------------------------------
📌በ1500 ሴቶች

🏃‍♀1.አትሌት ድርቤ ወልተጂ ⏰3:51:44 በሚኒሚ

🏃‍♂2. አትሌት ብርቄ ኃዬሎም⏰ 3:54:79 በሚኒሚ

🏃‍♂3..አትሌት ሳሮን በርሄ ⏰3:57:72 በሚኒሚ
---------------------------------------------
👉ተጠባባቂ
------------------------------------------------
🏃‍♂4. አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ⏰4:00:69
-----------------------------------------------
📌በ800 ሴቶች
🏃‍♂1. አትሌት ፅጌ ዱጉማ⏰1:56:64 በሚኒማ

🏃‍♂2.አትሌት ንግስት ጌታቸው⏰1:57:01 በሚኒማ

🏃‍♀3.አትሌት ወርቅነሽ መሠለ⏰1:58:06 በሚኒማ
---------------------------------------------
👉ተጠባባቂ
------------------------------------------------
🏃‍♂4. አትሌት ሀብታም ዓለሙ⏰12:00:94 በሚኒሚ
-----------------------------------------------
📌በ800 ወንዶች

🏃‍♂1. አትሌት ዮሐንስ ተፈራ⏰1:44:49 በሚኒማ

🏃‍♂2. አትሌት ጄኔራል ብርሃኑ⏰1:44:49 በWR በኮታ

📌በእርምጃ ወንዶች
🏃‍♂1. አትሌት ምስጋና ዋቁማ⏰1:19:20 በWR በኮታ

📌በእርምጃ በሴቶች
🏃‍♂1.አትሌት ስንታየሁ ማስሬ⏰ በ2014 African champion

በመሆን ለጃፓን ቶኪዮ 2025 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መመረጣቸውን ማረጋገጥ ችለናል ፌዴሬሽኑም ዛሬ በይፋ ሊያሳውቅ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

የአሠልጣኞችን ምርጫ በተመለከተ መረጃውን አጠናክረን እንመለስበታለን።

👉እናንተስ በምርጫው ዙሪያ ምን ትላላችሁ? ኮሜንት ላይ ሃሳባችሁን አስቀምጡልን።

ከሁለቱ የመሃል ሜዳ ማስተሮች ሽኝት በኋላ የነጩ ቤት ፌራሪ የመሃል ሜዳ ሞተር ወርዷል ። ሞተሩ ዕንደው በቀላሉም በጥሩ መካኒክ የሚታደስ አይደለም ። ለሞዛርቶቹ ውርስ የካማዎ ሽዋሚኒ ጥምረት...
25/07/2025

ከሁለቱ የመሃል ሜዳ ማስተሮች ሽኝት በኋላ የነጩ ቤት ፌራሪ የመሃል ሜዳ ሞተር ወርዷል ። ሞተሩ ዕንደው በቀላሉም በጥሩ መካኒክ የሚታደስ አይደለም ።
ለሞዛርቶቹ ውርስ የካማዎ ሽዋሚኒ ጥምረት ዕርባነቢስ ሆኗል ። ክፍተቱ ታላቁ ክለብን የሁሉም መፈንጪያ አድርጎት ከርሟል ። ሰውየው ፔሬዝ ለወረደው የማድሪድ ሞተር አዲስ ለማስጫን 100 ሚሊዮን ፓውንድ ይዘው ኢትሃድ ደጅ አሉ ። የቶኒ ክሩስ እና ሉካ ሞድሪች የዓመታት ታላቅ ግልጋሎት ካጣ በኋላ ሚዛን ያጣ ከርታታ የሆነው ሪያል ማድሪድ ሮኬቱ ቫልቨርድን የሚያግዝ የአማካይ ስፍራው ጀነራል ይፈልጋል ።

ሎስ ብላንኮስ ለወቅታዊ ኋያል የፀና ፍላጎታቸው ዓለምን እየዞሩ ቢያስሱ ከሲቲው ሮድሪ የተሻለ ልምድን ከብቃት ያጣመረ ሳተና የትም በዚህ ሰዐት አያገኙም ። በርግጥ ሪያል ማድሪድ ቢሆንለት አጭሩ የፓሬዚያኑ ልብ ምት ቪቲኒያንም ይመኛል ። እናም ንስሩ ቢሊየነር የነጩ ቤት አለቃ ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የተጨነቀው አሎንሶን ሊያረጋጉ ሲቲዝንስን እየዞሩ ነው ። ከተጨዋቹ ጉዳት ጋር በተያያዘ ያለ ሮድሪ አንድ ዓመት ሙሉ ህይወትን የተላመደው ጋርዲዮላ No Rodri No Party የቀመሰው የውጤት ዕውነታ ቢሆንም 30 ሊሞላ ለተጠጋው ድንቅ ስፔናዊ አማካይ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ቀርቦ ዐይኑን አያሽም ተብሎ ይገመታል ።
በዛ ላይ ጠያቂ ፈላጊው ደግሞ ሪያል ማድሪድ መሆኑ መረሳት የለበትም ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲ በአዲሱ ዝግጁ የቡድን መዋቅሩ እየፈጠረ ካለው ለውጥ አንፃር የላፉሪያ ሮሃው ኮኮብን ከኢትሃድ ከባለንዶኦር ክብሩ ጋር ሊሸኝ ይችላል ። ቪኒ እና ሮድሪ ሁለቱ ባለንዶኦሮች በነጩ መለያ በጋራ ሊታዩ እንደሚችሉ የስፔን ጋዜጦችም እየዘገቡ ነው ።

ኮኮቦቹን ሁሉ መሥጦ ለማስፈረም ያልተፃፈ ህግ ያለው የዓለማችን ብቸኛው ሪያል ማድሪድ መሆኑን ለሚታዘቡ ሮድሪ ከሮኬቱ ጌታ ቫልቬርዴ ሊጣመር ቤርናቢዬ ሊደርስ እንደሚችልም ተገምቷል ።[ Tribunesport ]

ዜና | 4ኛው "ናፍቆት" የድሬዳዋ ሳምንትን ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል ተባለ :: የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ አራተ...
25/07/2025

ዜና | 4ኛው "ናፍቆት" የድሬዳዋ ሳምንትን ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል ተባለ ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ አራተኛው "ናፍቆት" የድሬዳዋ ሳምንት መርሃግብርን በማስመልከት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫን ሰጥተዋል።

አራተኛው "ናፍቆት" የድሬዳዋ ሳምንት ለማሳካት ከያዛቸው ግቦች ውስጥ የድሬዳዋ ተወላጆች ፣ ወዳጆች እና ደጋፊዎችን ማህበራዊ ትስስር ማጠናከር ፣ ባለሃብቶች/ባለፀጋዎች በአስተዳደሩ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መስኮች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አማራጮችን መፍጠር ፣ የቱሪስት ፍሰትን እንዲጨምር ምችችት ማድረጓ ጨምሮ በክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ መሆኑን ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ከሃምሌ 21 እስከ ሃምሌ 25 ተከታታይ አምስት ቀናቶች አለም አቀፍ የድሬዳዋ ቀን ፣ የሰላምና የፍቅር ቀን ፣ የባህል ቀን ፣ የቤተሰብ ቀን እንዲሁም የምስጋና እና የእውቅና ቀን የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።

በዚህም መሰረት ሰኞ ሐምሌ 21 መላ ነዋሪዎችንና ዳያስፖራውን ያሳተፈ "ሽርሽር በኮሪደር ልማት ስር" የተሰኘ የእግር ጉዞ መርሀግብር ፣ የአስተዳደሩ ብሔር ብሔረሰቦች የሚገለገሉባቸው የባህልና የወግ እቃዎች ትዕይንትና የምግብ ቅምሻ ፌስቲቫል ፣ በከዚራ ጎዳና ላይ የብስክሌት ውድድርን ጨምሮ የብሔር ብሔረሰቦች የባህል አልባሳት ትዕይንትየሚከናወን ይሆናል።

ማክሰኞ ሐምሌ 22 በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የምድር ባቡር እና ጠርቃጨርቅ የቀድሞ ኳስ ተጫዋቾን ያሳተፈ ፣ የዲያስፖራ ልዑክ ከአስተዳደሩ አመራሮች የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ቴሌኮም ከፍተኛ አባላቶን የያዘ የተለያዩ አዝናኝ ስፖርታዊ ውድድሮች እና የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል።

ረቡዕ ሐምሌ 23 የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ፣ የፋብሪካ ምርቃትና የጉብኝት መርሐ ግብርና ስነ ስርዓትን ጨምሮ ፣ ለእንግዶች የባቡር ሽርሽር ፣ ሀገር አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ በታዋቂ አርቲስቶችና በአስተዳደሩ ባለሙያዎች የሚቀርብ ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት በለገሀር አደባባይ የሚዘጋጅ ይሆናል።

ሐሙስ ሐምሌ 24 ባለፉት ሰባት ዓመታት በአስተዳደሩ የተሰሩ የልማት ስራዎችና በዳያስፖራው የአገልግሎት አሰጣጥና ፓኬጅ ዙርያ በአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር ከዳስፖራዎች ጋር ውይይትና ምክክር መድረክ ይካሄዳል።

በተጨማሪም ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር አሊያም ከአቻ ጓደኞቻቸው በኮሪደር ልማት ስፍራ የሚጫወቱበት ቀን ሀገር አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ በታዋቂ አርቲስቶችና በአስተዳደሩ ባለሙያዎች የሚቀርብ ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት በለገሀር አደባባይ ይዘጋጃል

አርብ ሐምሌ 25 በማጠቃለያው የምስጋናና የእውቅና መድረክ የናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ፍፃሜውን እንደሚያገኝ በመግለጫው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የድሬዳዋ ተወላጆች ፣ወዳጆች እና ደጋፊዎች በጋራ እንዲታደሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። [ Dire tv ]

ሐምሌ 18 ፣ 2017 | ድሬዳዋ

Mesrak Sport l ምስራቅ ስፖርት

ዜና |  ናፍቆት ድሬ ሳምንት በሚካሄዱ የስፖርት መርሃ ግብር  ከ471ሺ ብር በላይ በማውጣት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተሳትፎ ማድረጉን አስታወቀ ። 4ኛው "ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት" ከሐምሌ 2...
25/07/2025

ዜና | ናፍቆት ድሬ ሳምንት በሚካሄዱ የስፖርት መርሃ ግብር ከ471ሺ ብር በላይ በማውጣት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተሳትፎ ማድረጉን አስታወቀ ።

4ኛው "ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት" ከሐምሌ 21 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ይከበራል ፡፡

ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ሲከበር ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በስፖርቱ ያላቸውን አሰተዋጽኦ አሰመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል ።

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ አበበ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ እንደተናገሩት ተቋማቸው ከሚሰጠው ብድርና ቁጠባ አገልግሎት በተጨማሪ በማህበራዊ አገልግሎቶች በንቃት ይሳተፋል ያሉ ሲሆን ከነዚህ መሀል አቅመ ደካሞች ይደግፋል ፣ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ያበረክታል ፣ ለአማተር የእግር ኳስ አሰልጣኞች የተለያዩ ቁሳቁሶችን ይደግፋል፤ ማዕድ ማጋራት ያከናውናል እንዲሁም የጤና መድን ለአቅመ ደካሞች ያደርጋል ብለዋል።

ታላቁ ግብ ጠባቂ ተካበ ዘውዴ በፈጠረባቸው ተፅዕኖ ግብ ጠባቂ በመሆን እግር ኳስን ተጫውተዋል -አቶ ተሾመ አበበ ። ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት አስመልክቶ በሚከናወነው የጨርቃጨርቅ እና የምድር ባቡር ጨዋታ ተቋማቸው ድጋፍ በማድረጉ ደሰታ እንደሚሰማውም ተናግረዋል ።

በወርቃማው የድሬዳዋ እግር ኳሰ ዘመን ምክንያት የነበሩት ከዋክብቶች አሁን ያሉበት ሁኔታ የሚያሳዝን በመሆኑ ተቋማቸው እነዚህን ባለ ውለታዎችን ለማገዝ የተለያዩ ስራዎችን እየስራ ይገኛል ብለዋል ። ዋና ስራ አስፈፃሚው በተጨማሪ እንደተናገሩት ለጨዋታው ብቻ ለሁለቱ ቡድኖች ማሊያ ለ50 ተጨዋቾች ለእያንዳንዳቸው 4ሺ ብር ጨምሮ ከ471ሺ ብር በላይ በማውጣት መደገፋቸውን ገልፀው በዚህም ትልቅ ደሰታ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል። አቶ ተሾመ ተቋማቸው የቀድሞ የሁለቱ ምርጥ ተጨዋቾች ህይወት እንዲሻሻል ሥራ መጀመሩ ተናግረዋል ።

ናፍቆት ድሬ ሳምንት ለ4ኛ ጊዜ ለድሬዳዋ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ስነ ሰረዓቶች ይከበራል ። ከምንም በላይ የድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ እና የድሬደዋ ምድር ባቡር ጨዋታ ይጠበቃል፡፡3ኛውን ናፍቆት ድሬን ጨርቃጨርቅ ማሸነፉ ይታወሳል ። የዘንድሮስ ማን አሸናፊ ይሆን አብረን የምናየው ነው፡፡ [ Dire tv ]

Mesrak Sport l ምስራቅ ስፖርት

23/07/2025

የእርዳታ_ጥሪ..🙏
🙏 በጎ እጆችን እየጠበቀች ያለች ነብስ! 🙏 ህፃን ልዑል የኃላሸት ህይወት_እንታደግ🙏

በድሬዳዋ ወረዳ 03 በልዮ ስሙ ለንበርዋን ከተወለደባት ህፃን ልዑል የኃላሸት በደረሰበት የልብ የጠና ህመም ላለፉት ጊዜያት በአገር ውስጥ የልብ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ሆኖም በአሁኑ ሰአት የልብ ህመሙ ወደ ውጪ ሔዶ ከፍተኛ ህክምና ማድረግ እንዳለበት በሀኪም ተረጋግጧል ፡፡

ስለዚህ # ከሀገር ውጪ ሔዶ ህክምናውን እንዲከታተል የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን በአጠቃላይ*2 ሚሊዮን ብር* # የተጠየቀ በመሆኑ እስካሁን የሚፈለገው ገንዘብ አልሞላም፡፡ በአሰቸኳይ ውጪ መሔድ እንዳለበት ተገልፆዋል::

እናም..የህፃኑ ቤተሰቦች የህክምናው ወጪ መሸፈን ስለማይችሉ መላው የሀገራችን ህዝቦች ፤በተለያየ ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የድሬዳዋ ወዳጆች ፤የዚህን ህፃን ልዑል የኃላሸትን ህይወት ይታደግ ዘንድ እርዳታችሁን ይማፀናል ።

ህፃን ልዑል የኃላሸትን ለመርዳት፣ህይወቱን ለመታደግ ከታች በተጠቀሱት በአራት ሰዎች የተከፈተው የባንክ ሒሳብ ቁጥር መሠረት በቤተሰቦቹ እና በእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴው ስም በአቶ /ወሮ ንግስትና ዩሐንስ እና ተስፋዬና የኃላሸት በተከፈቱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ * 1000699540513 *የቻላችሁትን እንድትረዱን እንማፀናለን፡፡🙏🙏

ለተጨማሪ መረጃ እንጠቁም።
#ለህፃን ልዑል የኃላሸትን ለህክምና ድጋፍ የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ስልክ ቁጥር
+251911801624
+251915436464 ወገኞቻችን ስለምታረጉልን ልገሳ በቅድሚያ እናመሠግናለን::

ሐምሌ 16/2017

የህፃን ልዑል የኃላሸት ህክምና የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ !!

Address

Addis Ababa
6068@2024

Telephone

+251915750424

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mesrak SPORT / ምስራቅ ስፖርት:

Share

Category