Lagaharree Social Media

Lagaharree Social Media Dirree Dhawaa badhaate Arguuf

11/08/2026
10/08/2026

ሣምንታዊ መልዕክት!

ዛሬ የተከልነዉ ችግኝ ነገ ጥላ እንደሚሆን ሁሉ፤ ዛሬ የምንገነባው የጋራ እሳቤም ነገ የሀገር ጽናት ይሆናል!

እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት ስንቆም የሚያስቆመን ምድራዊ ሀይል አለመኖሩን የቀደመዉ ታሪካችን ይመሰክራል፡፡

አድዋ ላይ በልዩነቶቻችን ሳንከፋፈል፣ በአንድ ልብና በአንድ ዓላማ ተሰልፈን የቅኝ ግዛት ሥርዓት ካባ ሊያላብሰን ድንበር ተሻግሮ የመጣዉን ወራሪ ድል ነስተናል። ይህ ታሪካችን ትልቅ ትምህርት ነው፤ የጋራ ዓላማችንን ከግለሰባዊና ከቡድናዊ ልዩነቶቻችን በላይ ስናደርግ ትላልቅ ድሎችን እንደምናስመዘግብ ህያዉ ምስክር ነዉ፡፡

የዛሬውም ትውልድ ይህንኑ የቀደምቶቹን ታሪካዊ መንፈስ በአዲስ መልክ መድገሙን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኅብረትና የሀገራዊ ቁርጠኝነት ምልክት ሆኖ በመቆም አረጋግጧል፡፡

የአረንጓዴ አሻራም በተመሳሳይ መንፈስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በአንድ ዓላማ አሰባስቦ ሀገራዊ ለውጥን በተግባር እያሳየ ይገኛል። በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) የተጀመረዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በስምንት ዓመት ጉዞዉ 48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እንዲተከሉ አድርጓል፡፡

በዚህም ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የመተው ኃላፊነት፣ የምግብ ዋስትናን የማጠናከር ጥረት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
በዚህ ዓመት “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን መትከላችን በኅብረት ስንንቀሳቀስ ምን ያህል ታላቅ ግብ ማሳካት እንደምንችል ያሳየን የአንድነት ድል ነው።

በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ባህል እየሆነ የመጣዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የደን ሽፋን ወደ 23.4 በመቶ እንዲያድግ ምክንያት ሆኗል፡፡ የጋራ ዓላማን ለማሳካት ከሚደረግ ጥረት ጎን ለጎን አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን በማጎልበት ለሀገራዊ አንድነት መጠናከር የአንበሳዉን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ የመደመር መንግሥት አረንጓዴ ኢኮኖሚን፣ የአካባቢ ጥበቃንና የተፈጥሮ ኃብት መንከባከብን ትልቅ ትኩረት በመስጠት ከ2011 የክረምት ወቅት ጀምሮ በየዓመቱ ‘አረንጓዴ አሻራ’ ገቢራዊ እያደረገ ይገኛል። በመላ አገሪቱ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እያሳተፈ መርሃ-ግብሩ እንደቀጠለ ነው።

ይህ መርሀግብር ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት ያደረገ ተግባር ነው። አሁን ላይ ደግሞ የችግኝ መትከል ባህል ከመንግሥት ቅስቀሳና ከግለሰቦች ጥረት ባለፈ ሀገራዊ ቅርፅ የያዘ ሲሆን ባለፉት ስምንት ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ትልቁ ማሳያ ነው።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን አለም አቀፍ ገፅታና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማጠናከሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ የCOP32 አስተናጋጅ እንድትሆን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በመሆኑም በተፈጥሮ እንክብካቤ መሪ መሆኗን አሻራዋን በማኖር እያረጋገጠች ከፊት ወደሚጠብቃት የCOP32 አስተናጋጅነት ታሪካዊ ኃላፊነት ታቀናለች፡፡

በአንድ ጀምበር የተከልናቸዉ ሚሊዮን ችግኞች ተከታታይ ክትትልና እንክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡ በመሆኑም የተከልነውን ማሳደግ፣ ያስጀመርነውን ማስቀጠል እና የጋራ ጉዳዮቻችንን በኅብረት ማሳካት ይጠበቅብናል። እንዲሁም ዘላቂ ልማትና ሰላም፣ የኢኮኖሚ እድገት፣ ሀገራዊ አንድነትና ሌሎች የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ በህብረት መረባረብ ይገባናል፡፡

ዛሬ የተከልነዉ ችግኝ ነገ ጥላ ይሆናል፤ ዛሬ የምንገነባው የጋራ እሳቤም ነገ የሀገር ጽናት ይሆናል። ስለዚህ ችግኝ መትከል ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ የሚደረግ ተግባር አይደለም፤ ለልጆቻችንና ለልጅ ልጆቻችን የምናስረክበውን ሀገር ዛሬ የመገንባት ሀገራዊ ኃላፊነትም ጭምር ነው።

10/08/2026
Oromoon fedhii dhunfaaf hin qasooynee fedhii walooma biyyaatiif malee!!Abiy Ahmed Ali
10/08/2026

Oromoon fedhii dhunfaaf hin qasooynee fedhii walooma biyyaatiif malee!!
Abiy Ahmed Ali

Address

Dire Dawa
Dire Dawa
0923328778

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lagaharree Social Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share