Guna Broadcast Media ጉና ብሮድካስት ሚዲያ

Guna Broadcast Media ጉና ብሮድካስት ሚዲያ Guna Broadcast Media is news company on social media.

እንኳን በድል ተመለሳችሁ🏅🏅🏅🏅🏅🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹💪💪💪
28/07/2022

እንኳን በድል ተመለሳችሁ🏅🏅🏅🏅🏅
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹💪💪💪

Another Gold 🏅 medal for Ethiopia  Tsegay
24/07/2022

Another Gold 🏅 medal for Ethiopia
Tsegay

19/07/2022
የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴርና የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በሚያዚያ ወር  በጎንደር በወራቤና በጂንካ አካባቢ በተፈፀሙ የተለያዩ ጥቃቶች ላይ በተካሄደ ምርመራ ተረጋገጠ ያሉትን በህይወትና ...
15/07/2022

የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴርና የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በሚያዚያ ወር በጎንደር በወራቤና በጂንካ አካባቢ በተፈፀሙ የተለያዩ ጥቃቶች ላይ በተካሄደ ምርመራ ተረጋገጠ ያሉትን በህይወትና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት መጠን ይፋ አደረጉ። የምርመራ ግኝቱ ይፋ የተደረገው በኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋና የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኦፕሬሽን መምሪያ ሃላፊ ሙሊሳ አብዲሳ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። አቶ ሙሊሳ በጎንደር ከተማ አንድ የእስልምና ሃይማኖት አባት ስርዓተ ቀብር ላይ ለቀብር የሚሆን ድንጋይን ሰበብ በማድረግ በተፈጠረው ግጭት የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉና ከ100 ባላይ ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። በወቅቱ በንብረት ላይ የደረሰው ውድመት መጠን ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ፣ 11 የሚሆኑ መስጊዶች ላይ ጉዳት እንደደረሰና አንድ መስጊድ ደግሞ ሙሉ በሙሉ መውደሙን አስረድተዋል። በጎንደሩ ግጭት ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 509 ሰዎች ስር ቢውሉም አቶ ፈቃዱ እንዳሉት ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ከ300 የሚበልጡት ወዲያው ተለቀው የቀሩት 199ኙና ሌሎች 17 ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች በአጠቃላይ ከ216 ሰዎች 121ዱ ማስረጃ ስላልተገኘባቸው መለቀቃቸውን ገልጸዋል።በመጨረሻም ከሁለቱም እምነት ተከታዮች 103 ሰዎች ተለይተው ክስ ተመስርቶባቸዋል ብለዋል። ወራቤ ሳንቁራ ወረዳ በአለም ገበያ ከተማና መንዝር ጦር በርበሪ ወረዳ በተባሉ አካባቢዎች ተካሄዱ በተባሉ ቅስቀሳዎች ሰበብ በተነሱ ግጭቶች 2 ሰዎች መገደላቸውን ፣79 ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አቶ ሙሊሳ ተናግረዋል። እንደ በቀል ተወሰደ በተባለ እርምጃም አራት የኦርቶዶክስ እንዲሁም 3 የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት መውደማቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። በምርመራ መዝገቡ መሠረት 97 ሰዎች ላይ ክስ ተመስርቷል። ጉዳት እንደደረሰባቸው ተረጋግጧልም ተብሏል። በስልጤ ወራቤ የደረሰው የንብረት ውድመት 46 ሚሊዮን ብር እንደሚገመትም ተገልጿል።
ከማንነት ጥያቄ ጋር በተገናኘ በኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ አራት የአሪ ወረዳዎችን በመያዝ ዞን እንሆናለን የሚል ጥያቄ በማቅረብ ሂደት የከተማዋን ከንቲባ ጨምሮ ሻንካ የሚል ቡድን በማደራጀት ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት በአማራ ተወላጆች ላይ ፈጽመዋል ያሉት አቶ ሙሊሳ በጥቃቱ 247 ሚሊዮን ብር የሚገመት የተለያዩ ሰዎች ንብረት መውደሙን ተናግረዋል። አቶ ሙሊሳ በዚሁ ወቅትም 144 የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች ቤት ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል 46 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል። ።1150 ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል። በጥፋቱ ከተጠረጠሩ 732 ተጠርጣሪዎች ውስጥ በፌደራል መንግሥቱ ስልጣን ስር ይወድቃሉ የተባሉ 142 ተከሳሾች ሰዎች በፍርህ ሚኒስቴር በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዘርፍ ክስ እንደተመሰረተባቸው አቶ ፈቃዱ አብራርተዋል።

‹‹ግደሉ›› የሚሉትን ታቅፎ ‹‹አትግደሉ›› የሚሉትን አፋኙ መንግሥት---በአሳዬ ደርቤ---ሰኔ 23/2014 ዓ.ምበአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚያደርጉ የመንግሥት አመራሮች፣ አክ...
30/06/2022

‹‹ግደሉ›› የሚሉትን ታቅፎ ‹‹አትግደሉ›› የሚሉትን አፋኙ መንግሥት

---በአሳዬ ደርቤ---

ሰኔ 23/2014 ዓ.ም

በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚያደርጉ የመንግሥት አመራሮች፣ አክቲቪስቶች፣ ፓስተር ተብዬዎችና በሐይማኖት ውስጥ የተደበቁ ተኩላዎች... እኩይ አላማቸው በመንግሥት የሚደገፍ በመሆኑ በፍጹም ነጻነት በየሚዲያው እየወጡ ወለጋ ላይ በፈሰሰው የንጹሐን ደም ፈንታ ለተገደሉት ዜጎች የሚፈስሰውን እንባ እያወገዙ የጭፍጨፋውን ምክንያትና ተገቢነት ማስረዳታቸውን ቀጥለዋል፡፡ እኒህ ጸረ አማራ ኃይሎች ከ1600 በላይ ንጹሐንን ካስጨፈጨፉ በኋላም የተለመደ ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም የሚያበረታታቸው እንጂ የሚቆጣጠራቸው መንግሥት አገሪቷ ላይ የለም፡፡

በሌላ መልኩ ግን አሳፋሪው የአማራ ክልል መንግሥት ኦነጎች ወለጋ ላይ በፈጸሙት አረመኔያዊ ድርጊት የአማራ ፋኖዎችን እያፈነ ወደ ማጎሪያ ካምፕ ማስገባቱን አጠናክሯል፡፡ በአዲስ አበባም፣ በግፍ ለተጨፈጨፉ አማራዎች ኀዘናቸውን የሚገልጹትንና የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙትን እየመረጡ የማሰር ዘመቻው በበላይ በቀለ ወያ ተጀምሯል፡፡

ከባድ መሣሪያ ታጥቀው፣ ግዙፍ ሠራዊት አደራጅተው የሥልጣን ትግል ከለኮሱትና ንጹሐንን ከሚጨፈጭፉት የትሕ-ኦነግ ኃይሎች ይልቅ ‹‹ዜጎችን አታስገድል›› የሚል ሰላማዊ ትግል የሚያሳስበው የብልጽግና መንግሥት ወንጀለኞችን ታቅፎ የሚቃወሙትን እያሳደደ ነው፡፡ ከዩኒቨርስቲ ተማሪ መሀከልም አሸባሪ እያፈላለገ ነው፡፡

በንጹሐን ላይ የሚፈጸመው እልቂት ሦስተኛውን ዙር የአባይ ግድብ ሙሊት ማደናቀፍ በሚፈልጉ የግብጽና የሱዳን ተላላኪዎች የሚፈጸም ነው›› በሚል መግለጫ ተላላኪዎቹንና ጨፍጫፊዎቹን አዝሎ፣ ግድቡን በአማራዎች ደም ሊሞላው ያሰበ ይመስል ‹‹ጭፍጨፋው ይቁም›› የሚሉ ድምጾችን ለማፈን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡

እንዲያም ሆኖ ግን ከእኛ የሚጠበቀው ሦስት ነገር ነው፡፡

1. ወንጀል አለመሥራትና ሕግን አለመተላለፍ

2. ወንጀልን እና ወንጀለኛን በመቃወም የሚመጣን የትኛውንም እርምጃ ንቆ ማለፍ

እና ደግሞ….
ተገቢነት በሌለው የአምባገነኖች ቅጣት አለመሸነፍ




#በቃን

#እምቢ

እውቁ አሜሪካዊ  ድምጻዊ አር ኬሊ በጾታዊ ጥቃት ወንጀል የ30 ዓመት እስር ተፈረደበትታዋቂው የአሜረካዊ የአር ኤንድ ቢ አቀንቃኝ አር ኬሊ በአሜሪካ ፍርድ ቤት የ30 ዓመት እስር እንደተፈረደ...
30/06/2022

እውቁ አሜሪካዊ ድምጻዊ አር ኬሊ በጾታዊ ጥቃት ወንጀል የ30 ዓመት እስር ተፈረደበት

ታዋቂው የአሜረካዊ የአር ኤንድ ቢ አቀንቃኝ አር ኬሊ በአሜሪካ ፍርድ ቤት የ30 ዓመት እስር እንደተፈረደበት ተነግሯል።

የ55 ዓመቱ ሙዚቀኛ ባሳለፍነው መስከረም ወር ላይ ነበር በወሲብ ንግድ፣ በህፃናት ላይ ጾታዊ ጥቃት፣ በአፈና እና ሌሎች ከወሲብ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ተከሶ ፍርድ ቤት የቀረበው።

በዚህም ፍርድ ቤቱ ትክክለኛ ስሙ ሮበርት ሲልቪስተር ኬሊ በተባለው ድምጻ ላይ የ30 ዓመት እስር የፈረ ሲሆን፤ ይግባኝ ማለት መብት እንዳለውም አስታውቋል።

''መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን በአግባቡ ያክብር'':-  #ኢሰመጉየኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ:-  ሰኔ 23/ 2014///////////////////////////////////...
30/06/2022

''መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን በአግባቡ ያክብር'':- #ኢሰመጉ

የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ:-
ሰኔ 23/ 2014
////////////////////////////////////////////
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዥንጋ ወረዳ ሴነ ቀበሌ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በሸኔ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት እጅግ በጣም በርካታ ንጹሀን ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት፣ ዘረፋ እና እገታዎች መፈጸማቸውን እንዲሁም ኢሰመጉ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም መግለጫ በማውጣት መንግስት የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ ጥፋት አድራሾችን ለህግ እንዲያቀርብ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

በዚህ ጥቃት ምክንያት በርካታ ሰዎች(በዋናነት ህጻናት) ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች(በተለይም ህጻናት) እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እና ይህ እርዳታ እና ድጋፍ በበቂ ሁኔታ እየደረሰ አለመሆኑን ኢሰመጉ ከአካባቢው ባሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ይህንን ድርጊት በማውገዝ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰላማዊ ሰልፎች የተደረጉ ሲሆን ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዎን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፎችን ያደረጉ ቢሆንም ሰልፎቹ የጸጥታ ሀይሎች አስለቃሽ ጭስንና ሀይልን በመጠቀም እንደበተኑት እና በሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች በነበሩ ሰልፎች ላይ የተደበደቡ እና የታሰሩ ተማሪዎች እንደሚገኙ ኢሰመጉ ከአካባቢው ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ተያያዥ የህግ ግዴታዎች፡
የሲቪል እና ፖለቲካል መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን አንቀጽ 21 ላይ ሰዎች ሰላማዊ ስብሰባ የማድረግ መብት እንዳላቸው እና ለብሔራዊ ጸጥታና የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጥቅም ወይም የህዝብን ጤናና ስነ ምግባር ለመጠበቅ ወይም የሌሎችን መብቶችና ነጻነቶች ለማስከበር ከሚያስፈልገውና በህግ ከተደነገገው በቀር በዚህ መብት ላይ ምንም ገደብ አይደረግም ሲል ይደነግጋል፡፡

በሰዎች እና ህዝቦች መብቶች ላይ የወጣው የአፍሪካ ቻርተር በአንቀጽ 11 ላይ ሁሉም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን የመሰብሰብ መብት እንዳለው እና ይህ መብት ሊገደብ የሚችለው በህግ አግባብ በተደነገገው መሰረት ብቻ ለብሄራዊ ጸጥታ፣ ደህንነት፣ ጤና፣ ስነ ምግባር፣ እና ለሌሎች ነጻነቶች እና መብቶች ብቻ እንደሆን ይደነግጋል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት በአንቀጽ 30 ላይ የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትንና አቤቱታ የማቅረብ መብት በማለት ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡

ከእነዚህ ህጎች እና ከዓለም አቀፍ የህግ ፍልስፍና (jurisprudence) ልንረዳ የምንችለው ማንም ሰው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት እንዳለው እና ይህንንም መብት ለመለማመድ ለመንግስት የማሳወቅ ስራ መስራት ብቻ በቂ እንደሆነ (ፈቃድ የሚለው እሳቤ ትክክለኛ አረዳድ እንዳልሆነ) እንዲሁም ከላይ ከተጠቀሱት የተወሰኑ ሁኔታዎች በስተቀር ይህ መብት እንደማይገደብ ነው፡፡

31/05/2022
የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ መምህራን ወደ ተክለሃይማኖት አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ መምህራን ወደ ተክለሃይማኖት አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን እያሰሙ ነው ...
24/03/2022

የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ መምህራን ወደ ተክለሃይማኖት አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።

የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ መምህራን ወደ ተክለሃይማኖት አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን እያሰሙ ነው ። ከያዟቸው መፈክሮች መካከል
-ፈተናን በደቦ እየሰሩ ብቁ እና ተወዳዳሪ ትውልድን ማፍራት አይቻልም!

-በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ውጤት ላይ ተስፋቸውን ለተነጠቁ ተማሪዎች እና ወላጆች ፍትሕ ይሰጥ!

-ተማሪዎች በእውቀታቸውና በችሎታቸው ብቻ ይመዘኑ

-የፈተና ስርቆት የትምህርት ጥራትን ይጎዳል

-ተማሪዎቻችን የሀገራችን ሀብቶች በመሆናቸው እኩል ሊታዩ ይገባል! ሲሉ መምህራን ድምፃቸውን አሰምተዋል።


በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኙ መምህራንም የአቋም መግለጫ በሰልፋ ላይ ቀርቧል።

የመምህራኑ የአቋም መግለጫ የሚከተለው ነው

1) በ2013/14 ዓ.ም. የ12ተኛ ክፍል የተሰጠው ፈተናና የፈተና አሰጣጥ ፍትሀዊነት የጎደለው ስለሆነ መንግስት ይሄን አውቆ አጠቃላይ ውጤቱ እንዲሰረዝ እንጠይቃለን።

2) የፈተናዎች ኤጆንሲ የሚፈጸሙ ተደጋጋሚ የውጤት መዛነፎች በሙያችን ክብር ላይ አላስፈላጊ ጫና እየፈጠሩብን መሆኑ ታውቆ ማስተካያ እንዲደረግ፡፡

3) የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ፍትሃዊ ምዘናን፤ ብቃትንና የአገርን መጻኢ ዕድልን
ባገናዘበ መልኩ መፈጸም አለበት

4) የተማሪዎችን ውጤት ያለአግባብ ከፍና ዝቅ በማድሪግ እና በኤጀንሲው የህዝብን አመኔታ በማጓደል በትውልዱ ላይ ጥቃት የፈጸሙ እና ሀገርን ላልተገባ የኢኮኖሚ ኪሳራ የዳረገ ስነምግባር የጎደላቸው ባለሙያዎች ይጠየቁ፡

5) እንዲህ አይነትና ተመሳሳይ ችግሮች በህገራችን ላይ መታየት ከጀመሩ ብዙ አመታትን ያስቆጠረ ስለሆነ እና ወደፊትም በመንግስት ላይ እምነት እንዳይኖረን ስለሚያደርጉ መንግስት የተለየ የፈተና አፈታተን ስልት እንዲከተል እንጠይቃለን ብለዋል።

Address

Ras Mekonnen
Dire

Telephone

+251904282531

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guna Broadcast Media ጉና ብሮድካስት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Guna Broadcast Media ጉና ብሮድካስት ሚዲያ:

Share