
08/09/2022
ሼህ ሁሴን ጅብሪል ከ100 አመት በፊት ስለራያ የተናገሩት
"በስምንተኛው ሺህ በስተመጨረሻ
ከሰሜን የመጣ ነገረኛ ውሻ
ነጥቆ ይወስደዋል ፤ የመሆኒን መሬት ፤ የራዮችን እርሻ።
ጠጉራቸው ጨበሬ ቋንቋቸው የግራ
አፋቸው ሙጎጎ ፤ ቀልባቸው ወንጋራ
ጋግረው ያበሉናል ፤ የተንኮል እንጀራ።
አጥንትና ወገን ጎጥ እየቆጠሩ
በደረቅ ቀልባቸው እየተማከሩ
በድፍድፍ እጃቸው ቂጣ እያነኮሩ
መቼም ላንድ ሰሞን ፤ ይጠፋል ሃገሩ።
ወሎ ቡን ይወዳል አቦል እስከ ቶና
ዛሬም ዱኣ ያውቃል እንደትላንትና
እነዚያ ጨበሬዎች ቀኑ ሲከዳቸው
አርከባስ እያለ ወሎ ነቀላቸው።
በሁለት ሺህ አመት ደግሞ በሃስራ ሃንድ
እንዲያው ላንድ ሰሞን ፤ ደፍረስረስ ይልና የጦቢያ መንገድ
ዱኣው በጦሳ ላይ መልሶ ሲወርድ
መለይካ ሚመስል ፤ ዘሩ ከነአህመድ
ከጅማ ይዘልቃል ፤ ሊያረገን ዘመድ።
መልኩ እንደ ኢያሱ ነው ንግግረ ሸጋ
ምላሱ መድሃኒት ፤ ነገሩ የረጋ
በሱነው ጨለማው ቶሎ የሚነጋ።
እሱ በነገሰ በሶስተኛ አመት
የጎበዞቹ ሃገር ራያ ሚሉት
መሬቴን መልሱ እያለ ይነሳል
እምቢ ያሉት እንደሁ ፤ ና ውረድ እያለ ጎራውን ያፈርሳል።
ያኔ ያች ተሃት ቀልቧን ታዞራለች
መርዝ እንደቀመሰ አይጥ ትውለበለባለች
ራያ መሬቱን አለቅም ትላለች።
ያኔ ነው እድሜዋ ቶሎ የሚያበቃ
አልመልስም ስትል የሰው መሬት ሰርቃ።
ያኔ ነው የተሃት የሚያልቀው ነገሯ
ራያ ሜዳ ላይ ይቆፈራል ቀብሯ."
#ሸህሁሴንጅብሪል
#ኢትዮጵያ