16/08/2026
የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የላቀ ውጤትና ሽልማት
የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበይነ መረብ ኦንላይን የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በተሳካና በተቀናጀ መልኩ በመተግበር የላቀ ውጤት በማምጣቱ ተሸልሟል።
ይህ ውጤት ቢሮው የዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለነጋዴዎችና ለማህበረሰቡ ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተደራሽ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
በኦንላይን የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሂደት የተሻሻለ በመሆኑ፣ የደንበኞችን ጊዜና ወጪ ለመቀነስ፣ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እና የሥራ ሂደቶችን ለማቀላጠፍ አስተዋፅኦ አድርጓል።
የተገኘው ሽልማትም የቢሮው አመራርና ሠራተኞች በጋራ በመስራት ያሳዩትን ትጋት፣ ተነሳሽነትና የላቀ አፈፃፀም የሚያመላክት ነው። በቀጣይም ቢሮው የዲጂታል አገልግሎቱን በማጠናከር የነጋዴዎችንና የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ በቁርጠኝነት ይሰራል።
ይህ ሽልማት የዛሬ ስኬት ብቻ ሳይሆን የተሻለ አገልግሎት፣ የተሻለ አሰራርና የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያበረታታ ትልቅ ማበረታቻ ነው።