
08/09/2025
በዱራሜ ከተማ እና አካባቢው ባለፉት 7 ሳመንታት #1047 ሰዎች ከሲዖል አመለጡ።
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
"ወንጌል ለሁሉም፣ ሁሉም ለወንጌል!!" በሚል መሪ ቃል በዱራሜ ቁ.1 ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ከሐምሌ 14/2017 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም በዱራሜ ከተማና አከባቢው ሲከናወን በነበረው የወንጌል ስርጭት መርሀ ግብር ከ12000 በላይ ሰዎች የምስራቹን ቃል የሰሙ ሲሆን 1047 ሰዎች ጌታን የግል አዳኛቸው አድርገው ተቀብለዋል በንስሃም ተመልሰዋል፡፡
900 ሰዎች ተስፋ ሰጥተዋል።
ሥርጭቱን ያካሄዱት:-የቤተ ክርስቲያኒቱ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች፣መሪ ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ኬብሮን፣መዘምራን፣እናቶች፣የወንጌል ዘርፎች፣የምድብ ሰፈሮች እና ምዕመናን ናቸው።
የሥርጭቱ ሥፍራ:- ዱራሜ ከተማ፣ሀምቦ፣ዲዴ፣ዲማዩ፣ወታ፣ኦዶሪቾ፣ሄጎ፣ዳንቦያ፣አቦንሳ፣ጆሬ፣አዲሎ፣ሀምዲ ጎፎሮ(እዚያው ማረፊያ በማድረግ)፣ሾኔ፣ሺንሽቾ እና ሀደሮ ናቸው።
በተጨማሪም ለአቅመ ደካሞች የተለያዩ ድጋፎች ተደርገዋል፡፡
ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን።