ROCK-Realities Of Community Kembata

ROCK-Realities Of Community Kembata Realities of community kembata will be posted ....

   ❤️❤️❤️
10/06/2025

❤️❤️❤️

ሁለተኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ እንደሚካሔድ ተገለፀ።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እግር ኳስ ፌዴ...
10/06/2025

ሁለተኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ እንደሚካሔድ ተገለፀ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሠርካለም ሳሙኤል ሁለተኛውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮናን አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ሁለተኛው የክልሉ ክለቦች ሻምፒዮና ከሰኔ 5 - 19 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በሆሳዕና ከተማ ይካሔዳል።

ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የክልሉ ክለቦች ሻምፒዮና 24 ክለቦች በሦስት ስታዲየሞች ውድድር እንደሚያካሔዱ የገለፁት ፕሬዝዳንቷ ወ/ሮ ሠርካለም ሳሙኤል ውድድሩን ለማካሔድ በክለቦችም ሆነ በፌዴሬሽኑ በኩል በቂ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።

የፌዴራልና የክልል እንግዶችና የእግር ኳስ ስፖርት ቤተሰቦች በተገኙበት ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ደማቅ የመክፈቻ መርሀ ግብር በአብዬ ኤርሳሞ ስታዲየም እንደሚደረግ የገለፁት ወ/ሮ ሠርካለም ሳሙኤል በሻምፒዮናው የተሻለ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ የእግር ኳስ ክለቦች ክልሉን ወክለው በሀገር አቀፉ የእግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና የሚሳተፉ ይሆናል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

10/06/2025

#ያሉንን የተፈጠሮ ፀጋዎች እንወቅ እናስተዋውቅም።

🔵⚪️🔴

የሀምበርቾ 777 ደረጃዎችን ይዘቱንና ታሪካዊ ዳራውን በጠበቀ መልኩ ተጨማሪ ደረጃዎችን ለመስራትና የኢኮ ቱሪዝም ሥራዎችን የበለጠ በማልማት ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የተቋቋመ ኮሚቴ ...
10/06/2025

የሀምበርቾ 777 ደረጃዎችን ይዘቱንና ታሪካዊ ዳራውን በጠበቀ መልኩ ተጨማሪ ደረጃዎችን ለመስራትና የኢኮ ቱሪዝም ሥራዎችን የበለጠ በማልማት ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የተቋቋመ ኮሚቴ በተዘጋጀው እቅድ ላይ ተወያይቶ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለፀ።

ኮሚቴዎቹ ሀምበርቾን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለማልማት እንዲያስችል በተዘጋጀው እቅድ ላይ ተወያይቶ የጋራ አቋም በመያዝ ከሰኔ 2/2017 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲገቡ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አረጋ እሸቱ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በመድረኩ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አረጋ እሸቱ በሀምበርቾ ላይ የተሰራውን ዘመን ተሻጋሪ ሥራ የበለጠ በማላቅ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ በቅንጅት መሥራት ይገባል ብለዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀምበርቾን ከጎበኙ ወዲህ የተፈጠረውን ተጨማሪ እድል በመጠቀም በተራራ ላይ የ777 ይዘቱንና ታሪካዊ ዳራውን በጠበቀ መልኩ ደረጃዎችን፣ ማረፊያዎችን፣ መፀዳጃ ቦታዎች፣ መታሰቢያ ቦታዎችን፣ የእግረኛ መንገዶችና አረንጓዴ መዝናኛ ቦታዎችን ውበት እንዲኖረው ተደርጎ በአጭር ጊዜ ለመሥራት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ነው የገለፁት ክቡር ዋና አስተዳዳሪው።

🌄 Thank You for Visiting Mount Hambaricho! 🌿We are truly honored to welcome the international delegation that visited Ha...
08/06/2025

🌄 Thank You for Visiting Mount Hambaricho! 🌿

We are truly honored to welcome the international delegation that visited Hambaricho and is planning a Community-Based Tourism (CBT) development project for the next two years! 🙌

✨ Special Thanks to: 🇳🇱 – CBI Programme Manager from the Netherlands.
🌍 – Renowned international CBT expert with extensive experience in countries like Thailand, The Gambia, and Myanmar.
🌱 – Dutch-Ethiopian expert from Impact for Sustainability, with a strong background in project management.
🌍 – Also from Impact for Sustainability, bringing expertise in tourism and other development sectors.
🧭 – An experienced tour operator and strong figure in the Ethiopian tourism sector network.

🛖 Hambaricho is now officially included in the project activities! Trainings and capacity-building sessions will be conducted to empower local communities. The experts have already visited communities around Arba Minch and Hambaricho to explore training ideas and support mechanisms. 🤝

🙏 Thank you for believing in the potential of our heritage, people, and breathtaking landscapes of hambaricho.

Visit Kambata ሀምበርቾ ኢኮቱሪዝም ሥፍራ ጽ/ቤት Hambaricho Eco-Tourism Site Office

© Abinet tadege (Hambaricho Eco-Toursim Site Office Manager )

ፈጣን ይቅርታ ጠይቃችሁ ቶሎ አስተካክሉ!¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯*የቱሪዝም ሚኒስቴር ወዴት ነህ?-የዛሬ ሳምንት ነበር ዱራሜ የሄድነው-ጠቅላይ ሚንስትራችን ለመቀበል።...
08/06/2025

ፈጣን ይቅርታ ጠይቃችሁ ቶሎ አስተካክሉ!
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
*የቱሪዝም ሚኒስቴር ወዴት ነህ?

-የዛሬ ሳምንት ነበር ዱራሜ የሄድነው-ጠቅላይ ሚንስትራችን ለመቀበል።ከተማውና ሐምበሪቾ ተራራ በmain steram media crew ተጥለቅልቀዋል።የድሮን ቀረፃ ተጀምሯል።
አየሩም ድባቡም ደስ ይላል።ሰኞ ጠቅላዮ መጡ(ነገ ሳምንት ይሆናል)ምርጥጉብኝትና የሐምበሪቾ ማስተዋወቅ ስራ ሠሩ።በራሳቸውም በቢሯቸውም ስለሐምበሪቾ ተራራ 777 መወጣጫ ደረጃዎች በርካታ ዘገባ ለጥፈዋል/አስለጥፈዋል።ሁላችን አመስግነናቸዋል!
*የመጣው የጠቅላይ ሚኒስተሩ ቡድንም በጣም የተቀናጀ Friendly,የሚሠሩትን የሚያውቁ VERY FIT PEOPLE!OVERALL,እንከን የለሽ ጉብኝት ነበር።መስከረም ላይ ይደገማል።እናንተም ቶሎ ተንቀሳቀሱ።Do something!

*እሄ ብቻ አይደለም! በርካታ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ ያሉ ዋና ዋናም መለስተኛም የግልም ድረ-ገፃች የዚህን ድንቅ ተራራ ECHOTOURISM ስራ መጎብኘት ተቀባብለውታል።
እኔ በግርድፉ ካየኋቸው ፦
-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ
-የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት
-የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት
-ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
-ትራንስፖርት ሚኒስቴር
-ግብርና ሚኒስቴር
-መላው የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤቶች
-በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ
https://www.facebook.com/share/p/1AZMSQQDg2/

-ክብርት ሚ/ር ወ/ሮ ሙፈሪያት,አምባሳደር ፍፁም አረጋ......ወዘተ....ዜናውን አጋርተዋል።

ግራ የገባኝ ጉዳይ....!

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር የት ነው?
የዚህ ECHO-TOURISM SITE ቀጥታ ተዋናይ ባለቤትና ፕሮሞተር መሆን የለበትም እንዴ?

*ሪፓርቶች እንደሚያሳዮት የሐምበሪቾ 777 ደረጃ ዘንድሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በብዛት ከተጎበኙ የቱሪስት መዳረሻዎች ዋናው ቀዳሚና አንደኛ ነው።(በርካታ የውጭ ሀገራት ዜጎች)

*መፃፍና መዘገብ ቢያቅተው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወይም የጽ/ቤቱን SHARE አያደርግም እንዴ?አያጋራም እንዴ? ከናንተ ገፃች Promotion አይቶ መዓት ቱሪስት ለተራራ hiking አይመጣም እንዴ?የምን passivity ነው?
-የትኛውም ገፃቻችሁ ላይ ስለሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትራችን ወደ ከምባታ መሄድና ሐምበሪቾ ተራራን በ777 ደረጃ በአንድ ትንፋሽ በፍጥነት ወጥተው ተራራው አናት(3,058ሜትር ላይ) በርካታ ፑሽአፕ ሰርተው "ዓለም ይጎብኘው"ብለው ሲጋብዙ ግብዣቸውን SHARE እንኳን አታደርጉትም?

*የቀዳማይ እመቤት ፑሸአፕ በአንድ ቀን ሚሊየኖች View ያደረጉትን እንዴት ባላየ አለፋችሁት?እንዴት አስቻላችሁ?
ጀግና አይደለችም? Share አታደርጉትም?

*ሐምበሪቾ ያከበሩትን ያስከብራል!
*PROMOTING HAMBARICHO IS PROMOTING YOURSELF!....የትራንስፖርት ሚ/ር ድረ-ገፅ ከተፈጠረ ጀምሮ በሐምበሪቾ ልጥፉ ያገኘውን ያህል "like"አግኝቶ አያውቅም!
https://www.facebook.com/share/v/1GMpBBEZ4X/

https://www.facebook.com/share/p/16Qgqo6BbH/

በአንድ ቀን ሚሊየኖች የተመለከቱት!

https://vm.tiktok.com/ZMSSd56nA/
*ወደናንተ ድረ-ገፆች ስመጣ....ምነው?

*ሳምንቱን ሙሉ የትኛውም ከናንተ የስራ Scope ጋር ተያያዥ የሆኑ ገፆች ላይ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ተግተው በተደጋጋሚ Promote ያደረጉትን በአይነቱ አዲስና ተጨማሪ ውብ የቱሪዝም መዳረሻ አለማስተዋወቃችሁ አለመለጠፋችሁ ትልቅ ጥያቄ ፈጥሮብናል! አስተካክሉ(የወዳጃችሁ ምክር ነው)
ጓደኞቼም በተደጋጋሚ ስለዚህ ጉዳይ ጠይቀውኛል!

*Where is Ministry of Tourism?



*እንደ ሕዝብ ተወካይ I need explanation!
ቢሯችሁም እንመጣለን።ፓርላማ ሪፓርት ስታደርጉም እንገናኛለን።Seriously ተከታትለን እንጠይቃለን!

*በምን አግባብ ነው ዋናው የቱሪዝም ጉዳዮች ባለድርሻ መስሪያ ቤት ሳምንቱን ሙሉ ስለሐምበሪቾ ምንም ትንፍሽ የማይለው?

*As Ministry of Tourism of Ethiopia,what plans do you have to further develop Mount Hambarcho echo-tourism site?በዘንድሮውስ በጀት ምን ይዛችሁለታል?
(BTW 777 በሕዝብ መዋጮ በእጅ ነው የተሰራው)
*ሐምበሪቾ የናንተ PROMOTION ከይበዛበትም! ሲሆን ሲሆን በጀትም ትመድቡለታላችሁ እንጂ።
It is now well promoted.ቶሎ Actively ተሳተፉ።ንቁ!
እድሜ ለጠቅላዮና ለቀዳማዊት! አብንስ ገለጢናንሳ

እናንተም አ ስ ተ ካ ክ ሉ!!!

Via Biruk Lambisso Wamisho

08/06/2025
Highlight! HAMBARICHO eco tourism site in Ethiopia.Climb the 777 steps up Hambaricho mountain. Beautiful blend of cultur...
08/06/2025

Highlight! HAMBARICHO eco tourism site in Ethiopia.
Climb the 777 steps up Hambaricho mountain. Beautiful blend of culture, history and nature:
7 peaks
7 local clans
7 water streams.
Joining together into unity.

We were resting for more than an hour on top of Hambaricho sacred mountain, enjoying the incredible views. Taking time to pray for my loved ones lost and found.

Via Jeanette Scherpenzeel

የዱራሜ ከተማ ማዘጋጀ ቤት የኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለሙያዎች በጋራ  አሁን በዝህ ሰዓት በግንባታ ሳይት በሥራ ላይ እንገኛለን ።የሥራ ባህላችን ተቀይሯል !የኬብሮን እንቴርናሽናል ህንፃ G+5 ...
07/06/2025

የዱራሜ ከተማ ማዘጋጀ ቤት የኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለሙያዎች በጋራ አሁን በዝህ ሰዓት በግንባታ ሳይት በሥራ ላይ እንገኛለን ።

የሥራ ባህላችን ተቀይሯል !

የኬብሮን እንቴርናሽናል ህንፃ G+5 ግንባታ ሥራ እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ በፍጥነት እየተሰራ ያለ ስሆን ባለሀብቱ በታቀደለት ግዜ ለመጨረስ በከተማችን ለመጀመሪያ ግዜ የማታ ግንባታ ፋቀድ ወስዶ አሁን ከምሽቱ 3 ስዓት ላይ ግንባታ ሥራ ለይ ነው።

ይህ ተሞክሮ ለሌሎችም አስተማሪ ነው።በሳይቱ ቀን 65 የቀን ሰራተኛ የነበረ ስሆን ለማታ ሥራ 26 ሳራተኛ በሥራ ላይ ይገኛል።
ከተማችን በዕድገት ጉዳና ላይ ነት ። የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ቀንናማታ የሥራ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን እናሳስባለን ።

Via ዱራሜ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ኮንስትራክሽን ዘርፍ !

28/09/2017 ዓ/ም

Tama 💍 Redi     እንኳን አደረሳችው!! አደረሰን!!          መቅረት አይቻልም!!"ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው...
07/06/2025

Tama 💍 Redi
እንኳን አደረሳችው!! አደረሰን!!
መቅረት አይቻልም!!

"ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።" የማቴዎስ ወንጌል 19:6

የወንድማችን ታምራት ታደሰ እና የእህታችን ረድኤት ጥላሁን የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት ሰኔ 1 2017 ዓ/ም ቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ጉዋደኞቻቸው በተገኙበት ይሞሸራሉ።

የጥሪ ወረቀት ያልደረሳችሁ በሰው እጅ ቀርቶ ይሆናል እንጂ እኔ ሳልጋብዛችሁ እንዳልቀረሁ አስባችሁ እሁድ በሰርጋችን ዕለት እግ/ርን አብራችሁን እንድታመልኩ ሲሉ ሙሽሮቹ በፍቅር ጋብዘዋል!!!!

ባለ 777 ደረጃው ተራራ "ሀምበሪቾ"         #ኢቲቪ  #ሀምበሪቾ
07/06/2025

ባለ 777 ደረጃው ተራራ "ሀምበሪቾ"

#ኢቲቪ #ሀምበሪቾ

07/06/2025

የሀምበሪቾ ተራሮች የኢትዮጵያን የተፈጥሮ እና የባሕል ቅርስን የሚያሳዩ ተምሳሌቶች ናቸው። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኙት እነዚህ አስደናቂ የተራራ ሰንሰለቶች የብዝኃ ሕይወት ሀብት እና የታሪክ ዋጋን የተሸከሙ ናቸው። ሀምበሪቾ ተራራ እና ከባቢው ከ16ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን የተከታታይ የከምባታ ነገስታት መቀመጫ በመሆንም አገልግለዋል።ዜጎች እና ከአለም ዙሪያ የሚመጡ ጎብኝዎች አስደማሚውን የሀምበሪቾ ውበት እንዲጎበኙ እና በአካባቢው ሕዝብ እውቀት እና ጉልበት የተሰራውን እኔም የወጣሁትን አስደናቂ 777 ደረጃ በመውጣት ራሳቸውን እንዲፈትኑበት አበረታታለሁ።

The Hambaricho Mountains represent a remarkable facet of Ethiopia’s rich natural and cultural heritage. Situated in the Central Ethiopia region, this mountain range offers stunning landscapes, diverse ecosystems, and significant historical value. Hambaricho Mountain and its surrounding ranges served as the administrative centre and seat of successive Kambata kings from the 16th century until the late 19th century.I encourage citizens and visitors from around the world to experience the breathtaking beauty of Hambaricho and to take on the challenge of climbing its iconic 777 hand-carved stairs which I accomplished last week!

ጠቅላይ ሚንስቴር ክቡር Abiy Ahmed Ali (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ካጋሩት የተወሰደ።

Visit Kambata Ethiopia Land of Origins Central Ethiopia Region Culture and tourism Bureau Hambaricho Eco-Tourism Site

Address

Durame

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ROCK-Realities Of Community Kembata posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share