የዳሞት ፍሬ/Damot's Fruit

የዳሞት ፍሬ/Damot's Fruit ኑ የደጋ ዳሞት ፍሬ ዛሬ በመረጀ አቀባይነት ይሠራል ነገ በበጎ አድራጎት መልክ ይመጣል

08/05/2024

የሊቀ ሊቃውንት ተዋናይ ቅኔ
~~~~~~~~~~~~~~
(ተዋነይ ዘ ጎንጅ)
(ምንጭ፣ሕይወት ታደሰ ወደአማርኛ የተረጎመችው የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ)

ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ
ወፈጠረ ፈጣሪ ኪያው።

የህግ ባለሟል
የፍትህ አባት ሙሴ
ከህግ አንቀፅ በፊት ሊያመልክ የሚሻውን
ፈጣሪን ፈጠረው

ፍትህ የሚባል እግዜር
ህግ የሚባል እግዜር
ሙሴ እሱን ለመውደድ ሲጨነቅ አየና
ፈጣሪ ወደደው ሙሴን ፈጠረና።

ጎንጅ ቅኔ ያጠናበት ደብር ሥም ነው። ደብረ ጥበብ ጎንጅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም። ተዋነይ የባለቅኔው ሥም ነው። (የግዕዝ ትርጉሙ "ዋናተኛ" ማለት ነው።) ሊቁ ተዋነይ የልኅቀቱን ያክል እምብዛም አይወራለትም፤ ነገር ግን በዘመኑ ወደር የሌለው ልኂቅ ስለመሆኑ ሥራው ይናገራል። የሕይወት ተፈራ "Mine to Win" የተሰኘ ድርሰት መቼቱን በዐፄ ዮሓንስ ንግሥና ዘመን፣ በጎጃም/ጎንደር የቅኔ መማሪያ ደብሮች ያደረገ ልብወለድ ነው። ልቦለዱ የቅኔ ትምህርት ስርዓትን ያስተዋውቀናል፤ በበኩሌ የቅኔ ትምህርትን እና የቅኔ ሊቃውንት ታላቅነት ቀድሞ ከነበረኝ ግንዛቤ የበለጠ እንዲሆን አድርጎኛል። በተለይ የተዋነይ ዘ ጎንጅ (በውኑ ዓለም የነበረ ባለቅኔ) ተከታይዋ አምስት መሥመር ቅኔ መጽሐፍ የሚወጣት እንደሆነች ልቦለዱ አሳሰበኝ። ወይም በአጭሩ ብዙ ምዕራባውያን ስንት መጽሐፍ የጻፉለት ፍልስፍናን በአምስት መሥመር ይዟል። የቅኔው ትርጓሜ የመጽሐፍ ቅዱስን እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ፈጣሪ ኅልውና ይሞግታል።

ትርጉሙን በኋላ እመለስበታለሁ። ስለተዋነይ መጀመሪያ የሰማሁት የበውቀቱ መጽሐፍ ላይ ነበር። እሱም በጨረፍታ - “የሌሊት ዜማዎች” የሚለው ግጥሙ ውስጥ። በውቀቱ ተዋነይን በግጥሙ ግርጌ ማስታወሻው አስተዋውቆን ያልፋል፣ “ተዋነይ በቅኔ ቤት አፈ ታሪክ ሞትን በግዝት ለሰባት ዓመታት ያቆመ ጀግና ነው"። ከዚያ በኋላ፣ አዲስ አድማስ ላይ የወጣ አንድ ጽሑፍ ተዋነይ የተላከበትን መልአከ ሞት ደጃፉ ላይ በምትሐት 7 ዓመት አቁሞት በማርያም አማላጅነት ነው ገብቶ ነፍሱን እንዲወስድ የፈቀደለት የሚል አፈ ታሪክ አለ ይለናል። በሌላ በኩል ዕፀ ሕይወት አግኝቶ ነገር ግን በአጠቃቀም ስህተት ግማሽ ሰውነቱ ሞቶ ግማሹ ሲኖር፣ ፈጣሪውን ለምኖ ነው ሙሉ ለሙሉ የወሰደው የሚል ሌላ አፈ ታሪክም አለ። የኋላ ኋላ ቴዲ አፍሮም አንድ ዘፈኑ ላይ ሥሙን ጠቅሶት ያልፋል።

በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የተጻፈው የአለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራ "የኢትዮጵያ ታሪክ" (በሚል በሥርግው ገላው የተሰናዳው መጽሐፍ) ላይም ሥሙን እንዲሁ በአጭሩ ተጠቅሶ አገኘሁት። እንዲህ ይላል፣ “ዐፄ በካፋ በዘመኑ ከክፉ ሥራ በቀር ፩ ቀን በጎነት ሥራ አልሠራም። ያን ግዜ ተዋነይ የሚባል የጎንጅ ደብተራ ጠንቋይ ነበረው። ሙያው ከርሱ ጋራ ነበረ። በካፋም ፱ ዓመት ነግሦ [በ1723] በክፉ ሞት ሞተ።" ተዋነይን የቀድሞ ታሪክ የሚያስታውሰው እንዲህ ነው ማለት ነው? በርግጥም ይህን መሰል ቅኔ እየጻፈ መልካም ሥም ቢኖረው ነበር የሚገርመኝ። የፍቅር እስከመቃብሩ "ጉዱ ካሣ" የእውነተኛ ባለታሪክ ቢሆን ኖሮ (የእውነተኛ ሰው መነሻ ተደርጎ ነው የተጻፈው የሚሉ አሉ) በታሪክ የሚታወሰው እንደቀውስ ነበር። ከዚህ አንፃር የተዋነይ ዘ ጎንጅ እንደ ጠንቋይ መታወስ ላይገርም ይችላል። በነገራችን ላይ፣ ተዋነይ የዐፄ በካፋ አማካሪ ከመሆኑ በፊት የንጉሡን ምግብ ዕፀ መሰውር ለብሶ (እንዳይታይ ሆኖ) ይበላባቸው ነበር የሚባል አፈ ታሪክም አለ።
ከዚያ በኋላ ደግሞ ገጣሚው ኤፍሬም ሥዩም “ተዋነይ" በሚል ርዕስ “ብሉይ የግዕዝ ቅኔያት ፍልስፍና” ትርጉም የያዘ መጽሐፍ አሳትሟል። "ቅድመ መግቢያ"ውን የጻፉለት ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን የተዋነይን ሁለት ቅኔዎች መርቀውልን ያልፋሉ። ከሁለቱ አንዱ የታችኛው ነው።

“ፀሐየ ሰማይ ያውዒ ሀገረ መርቄ ርኁቅ፣
እንዘ ቅርብቶ ደደከ ኢያመውቅ።"

ትርጉሙ እንዲህ ነው፦

አንቺ ፀሐይ - አፍንጫሽ ሥር ያለው - ደጋ ምንም ሳይሞቅ፣
እንደምን ተቻለሽ - ቆላውን ከሩቁ - እንደዚህ ማወበቅ።

[ሳይንስ ለዚህ የተዋነይ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ የአየር ጥቅጥቅነት (ዴንሲቲ) ከፍታ ቦታ ላይ የሚቀንስ መሆኑን ነው። ሙቀት ደግሞ በባዶ ቦታ (ቫኪዩም) ላይ አይቆምም። ዞሮ፣ ዞሮ ሳይንስ የሚመልሰው ጥያቄው ቀድሞ የተገኘ እንደሆነ ነው።] ተዋነይ የነበረው ጭንቅላት እንዲህ ዓይነት ጠያቂ ነበር፤ አጠያየቁ ደግሞ በቅኔ።

ስለተዋነይ ሕይወት ይሄ ነው የሚባል መረጃ አላገኘሁም። ነገር ግን የዛሬ ሰዎች ለተዋነይ ቅኔ ያስተማረው መንፈስ ቅዱስ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ሰምቻለሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በውኃ ላይ እንደተራመደ ሁሉ፣ ተዋነይም በጣና ውኃ ላይ የሚራመድ ምትሐተኛ ነበር የሚሉትም አሉ። በደመና ተጭኖ ዓለምን ጎብኝቷል እስከማለትም ይደርሳሉ።

"ተዋነይ በጣና፣
ይመስላል ደመና" ይባላል።

ኤፍሬም "የቅኔ ፈጣሪዋ" ይባላል ይለናል - ተዋነይን። ነገር ግን በትርጉሙ ላይ በመግቢያዬ የጠቀስኳትን፣ ይሄን ሁሉ ለመዘብዘብ ያበቃችኝን ቅኔውን፣ ከሌሎች ተርጓሚዎች በተለየ ነው የተረጎማት። ሲጀመር፣ የመጨረሻዎቹን ሁለት ስንኞች ብቻ ነው የሚተረጉማቸው። ሲቀጥል፣ የአማርኛ ትርጉሙ ላይ አምስቱንም መሥመሮች ነው የሚተረጉማቸው። "የሚያነቡት አማርኛውን ብቻ ነው" ብሎ ነው ብለን እንዳንገምት ደግሞ መግቢያው ላይ "ምጣኔነቷ ሁለት መሥመር ነው" ይለናል። ትርጉሙን እነሆ፣

“የሕግ ባለሟል
የፍት’ አባት ሙሴ
ከሕግ አንቀፅ በፊት ሊያመልከው ‘ሚሻውን
ፈጣሪን ፈጠረው።
ፍትሕ ‘ሚባል እግዜር
ሕግ የሚባል እግዜር
ሙሴ እርሱን ለመውደድ ሲጨነቅ አይና
ፈጣሪ ወደደው ሙሴን ፈጠረና።”

ይህ የኤፍሬም ትርጉም፣ በኔ እምነት፣ የተዋነይን ፍልስፍና ግልጽ አያደርገውም። የመጨረሻዎቹን ሁለት ስንኝ ትርጉሞች ያየን እንደሆነ፣ ‘ፈጠረ’ የሚለውን ቃል ለሙሴ ሲሆን ‘ወደደ’፣ ለፈጣሪ ሲሆን ደግሞ ‘ፈጠረ’ እያለ ተርጉሞታል። ይህ “ሙሴ ፈጣሪውን ፈጠረ” ብሎ አንድ ክርስቲያን ሊጽፍ አይችልም ከሚል አዕምሮ የፈለቀ ትርጉም ይመስላል። ይህንን ይዤ አንዲት በፒኤችዲ ደረጃ የግዕዝ ተማሪ ወዳጄ የሆነችው ሔዋን ስምኦን ጋር ሔድኩኝ። እሷም [‘አዋቂዎች ጠይቃ’] ‘ፈጠረ’ የሚለው የግዕዝ ቃል ሊኖሩት ከሚችሉት ትርጉሞች መካከል ሁለቱ “ወደደ” እና “ፈጠረ” የሚሉት መሆናቸውን ነገረችኝ። (የሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን ግዕዝ - አማርኛ መዝገበ ቃላት ግን ‘ፈጠረ’ ለሚለው እና ለ11 ብዜቶቹ አንድም ‘ወደደ’ የሚል ወይም ተቀራራቢ ትርጉም አይሰጥም።) የሆነ ሆኖ፣ በእርሷ የስድ ንባብ ትርጓሜ፣ የሙሉ ቅኔው እያንዳንዱ ስንኝ እንዲህ ሊተረጎም ይችላል።

“ያምናል ይገ:ዛል
ዓለም ሁሉ ራሱ ለፈጠረው
ብዙዎች አምነው በፊቱ ሲሰግዱ
ይሄንንም ነገር ለማስተዋል እሥራኤል ይፈሩ ዘንድ
ሙሴ ፈጣሪውን ወደደው
ፈጣሪውም እሱን ወደደው”

ይሁን እንጂ በእሷ ትርጉም ውስጥ ያሉት የመጨረሻዎቹ ሁለት ስንኞች፣ ከላይኞቹ ስንኞች ጋር በዐውድ አይገጥሙም። ትርጉማቸው እንዲያ ከሆነ ቅኔውን ተራ ያደርጉታል። ይህ ትርጉም የሚስማማቸው ሊቃውንት፣ ‘ተዋነይ የተቸው ከእሱ በፊት የነበረውን የጣኦት አምልኮ ነው’ ብለው ያምናሉ ብላኛለች። ነገር ግን እንደብሉይ ኪዳን ከሆነ ሙሴም ቢሆን መሰዊያ አስቀርፆ ነው እንዲያምኑ የሰበካቸው - መጽሐፉም የሚነግረን እንደዛ ነው። በዚህ የቅኔው ትርጉም ሔዋን እንዳለችኝ፣ "ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የተስማሙበት ነው"። እኔ ግን ስምምነቱን አሳምኖኝ አልተቀበልኩትም። የቤተ ክርስትያን ሊቃውንት ሥራ አማኞችን መጨመር እንደሆነ አውቃለሁ። ስለዚህ የሕይወት ተፈራ መጽሐፍ (የአማርኛው ትርጉም) ላይ ያለውን የቅኔውን ትርጉም አማኝ ሊቃውንቱ የሚወዱትም የሚቀበሉትም አይመስለኝም። ሆኖም፣ ይህ የሕይወት ትርጉም፣ የመጨረሻዎቹን አወዛጋቢ ስንኞች ከላይኞቹ ጋር በዐውድ ስምም እንዲሆኑ ያደርግልናል። ከኤፍሬም ሥዩም ትርጉም የተሻለ የሚያሰኘውም ዐውዱ ነው።

“የሰው ልጅ በገዛ’ጁ፥ ላስቀመጠው ፈጥሮ
ይገ:ዛል ባንክሮ
ሰው ፈርቶ እንዲገ:ዛ፥ እንዲሰላ ኑሮ
ለዚኽም ማስረጃው የሙሴ ነገር ነው አምላኩን መፍጠሩ
አምላኩም ፈጠረው በአምሳሉ በግብሩ።”

(ሕይወት ታደሰ/ሕይወት ተፈራ/ኀሠሣ)

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዘፍጥረት” የሚባለው የመጀመሪያው መጽሐፍ የተጻፈው በሙሴ ነው። (የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዝ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ 5 መጽሐፍት በሙሴ እንደተጻፉ ብዙ ጥናቶች ይናገራሉ፤ ራሱ መጽሐፉ ይህንን ይጠቅሳል። ለምሳሌ ዘፀአት 24፥4 "ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ" ይላል፣ ሌሎችም ይህንኑ ያረጋግጣሉ።) የተዋነይ ፍልስፍና እዚህ ላይ ነው የሚገለጠው። ሙሴ እንዲህ ጻፈ፣ “እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ” (ዘፍጥረት 1፥26)። ተዋነይ ሲያነበው፣ የሙሴ ጽሑፍ ውስጥ የሰው ምኞት የታየው ይመስለኛል። የፈጣሪን በራሱ በሰው አምሳል የመሳል ነገር (ቀናተኝነት፣ ቁጡነት፣ መመለክ/መከበር መፈለግን፣ ወዘተ…)፣ የሰው ልጅ የሌሎች ፍጥረታት ገዢ የመሆን ምኞትም እዚሁ የዘፍጥረት ጥቅስ ላይ ተጽፏል። ስለዚህ መጀመሪያ ሰው ሳይሆን ፈጣሪ ነው በሰው አምሳል የተፈጠረው (“ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ”)፣ ከዚያ በሙሴ ቃል ውስጥ ነው፣ ፈጣሪ ሰውን የፈጠረው ( "ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ")።

ተዋነይ ዘ ጎንጅ የሙሴን ድርጊት እንደፍትሓዊ እርምጃ የቆጠረው ይመስላል። እስራኤላውያን ፈርተው የሚታዘዙለት አንድ ሕግ አውጪ መኖር ነበረበት። ለዚያም ነው በአምሳሉ መልሶ የሚፈጥረውን ፈጣሪ ሙሴ ቀድሞ በአምሳሉ የፈጠረው እያለን ይመስላል።

29/04/2024

የሰሙነ ህማማት ሰኞ፡-

መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ-እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

አንጽሆተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተመቅደስ ሄደ፤ ቤተመቅደስ፣ቤተጸሎት፣ ቤተመሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

✟🍀🌸 🌸🍀✟
💐 💐
🌺🍂 🍂🌺
💐 💐
🍂🏜💒🏜🍂

"።።።።።።።።የቀጠለ።።።።።።።።ወንድሞቼ አሁን እናንተ እንዳላችሁት ይህን መከላከያ መስዋትነትነት ከፍለን መያዝ እንችላለን ። ይሁን እንጅ ይህ መከላከያ የመጨረሻው አይደለም ። ሌላ መከላከ...
30/06/2023

"።።።።።።።።የቀጠለ።።።።።።።።
ወንድሞቼ አሁን እናንተ እንዳላችሁት ይህን መከላከያ መስዋትነትነት ከፍለን መያዝ እንችላለን ። ይሁን እንጅ ይህ መከላከያ የመጨረሻው አይደለም ። ሌላ መከላከያ በእጥፍ ጨምሮ ይመጣል ። እናንተን ወንድሞቻችንን ስናጣ ግን ሌላ በእጥፍ የሚጨምር ወንድም የለንም ። ይልቅስ ዛሬ መከላከያ ከመሸገበት ሒዳችሁ አላስፈላጊ መስዋእት ከምትከፍሉ በቂ ስልጠና ስልጥናችሁ እንደፋኖ ወንድሞቻችሁ ብትዋጉ የተሻላ ይሆናል ። ዛሬ ግን የሚደረገው መስዋዕትነት የከፋ ይሆናል ። መከላከያም በከበባ ውስጥ ስለገባ አመልጣለሁ ብሎ ስለማያስብ እስከሚሞት መዋጋቱ አይቀርም ። በሚሊታሪ ሕግ ጦርነት የሚደረገው አዋጭነቱ ከተረጋገጠ በሗላ ነው ።
ብዙ ሠራዊት ሙቶ ትቂት ፋኖዎች መስዋእት ከሚሆኑና ከእናንተ መካከል ብርቅየ ወንድሞቻችን ከምናጣ መከላከያው መጣብን እንጅ አልሄድንበትምና ሽንፈቱን አምኖ ይሂድ ። " አለ ።
ወጣቱ ግን ለመተናነቅ ቢጓጓም የሽማግሌ ምክር ትዛዝን ከካድሪ በቀር የሚጥስ ስሌለ ሽማግሌዎችን አዳመጠ ።
መከላከያው በበኩሉ በጭንቀት ውስጥ ነው ። ጦርነቱ ቢጀመር በከበባ ውስጥ ስለሆነ መውጫ እንደሌለው ተርድቷል ። ስለሆነም የእንሸማገል መልዕክት ላከ ። ሽማግሌዎችም ወደመከላከያ አዛዦች ቀርበው የሕዝቡን የጦርነት ስነልቦነ ከፍተኛነት አስረድተው የመጣችሁበት ፋኖን የእናጠፋለን የመንግሥት የተንሸዋረረ እይታ አስረድተው ይህ ሁሉ የምታዩት ሕዝብ ፋኖ ነው ። ሌላው ከዚህ መምጣት አቅሙ ያልፈቀደለት ሽማግሌና ባልቴት በአሰተሳስብ ፋኖ ነው ። ፋኖን አጠፋለሁ ማለት ሕዝብን ገድየ እጨርሳለሁ ማለት ነው ። ይህ አይሆንም ስለሚሊታሪ ሕግ እኛም አለንበት ። አሁን እየተጨነቀን ያለነው የእናነትን ሕይዎት ለማትረፍ ነው ። ሕዝብም አላስፈላጊ መስዋትነት ከሚከፍል እናንተም ከዚሁ ከምትቀሩ ትዛዝ እናስከብራለን ገለመሌ ማለታችሁን ትታችሁ ወረዳችንን ለቃችሁ ውጡ ። የሚል ምክር መሰል ትዛዝ ተሰጣቸው ። በጭንቀት ውስጥ የነበረው መከላከያም ሽማግሌዎችን አመስግኖ የሚመለስበት አካባቢ እንዲለቀቅለት ተደርጎ ትናንቱን ካለቀው ወጭ ተጨማሪ ሳይልቅ ያለምንም ድል በሽንፈት ተመለሰ ።

ሕዝቡ መሽገው ከነበሩ ፋኖዎች ጋር ተገናኝቶ በደስታ እየሸለለና እየፈከረ ረጅሙን መንገድ ከፍልቅልቅ ጀመሮ ፈንካቲትን ፣ ገንዳውኃን ፣ አቋርጦ በየራ ሚዳ መንግድ ዝቋላ ደብረሲናን አቋርጦ በአመሰራርት ጥንታዊት በልማት እድገቷ ካሮት ከሆነችው ከተማ ገባ ። መላ ከተማው በሕዝብ ተጠለቅልቋል ። የጠጠር መጣያ የለም ። የፍከራው የሆታው የትኩስ ድምፅ ተደማምሮ ከተማው አዲስ ክስተት ሁኗል ።
ደም በመመላለስ የሚታወቀው ሕዝብ ዛሬ ግን ሌላ የገራ በአማራነቱ ሊያጠቃው የመጣ ጨካኝ አረመኔ ጠላት ስላለ ጠላትነቱን ትቶ ወንድማማች ሁኗል ።
በጅግንነት ጥንቱን የሚታወቀው አንድነቱ ግን በመንግሥት ሴራ ክፉኛ ላልቶ የነበረው ዛሬ አንድ ልብ መካሪ አንድ አፍ ተናጋሪ ሁኗል ።

ቀድሞ የነበረው የዳሞት ጀግንነት ሁለተኛ ዳግም ተወልደል ። በግማሽ ሚሊዮን አካባቢ የሚቀጥር ሕዝብ በከተማውዋ ያለምንም ፖሊስ ራሱ በራሱ ብቻ ያውም በበርካታ ተኩስ ደምቆ አንድ ሱቅ ሳይዘረፍ አንድ መሥራያ ቤት ሳይበር የፋኖዎች ደጀን መሆኑን አረጋግጦ በርካታ አትሌቶችን በአስገኘው ለምለሙ ባሕርመስክ ሚዳ ወርዶ በፋኖዎች ንግግር በሰላም ተጠናቆ የሩቁ በቅርብ እንዲያድር ሁኖ በሰላም ተሰናበተ ።

ዳሞትም በፋኖዎቹ ፋናዎጊነት በሕዝቡ አንደንድነት ያለብዙ መስዋዕትነት ማሸነፍ እንደሚቻል ለዓለም አስመሰከረ ።

ምስጋና
© በወረዳው ላለው ሁሉ ሕዝብ በተለይ ወደአረፋ ለተመመው ሁሉ
© ከወረዳው ውጭ የሆናችሁ ተወላጆች በስልክአመራሮችን ለመከራችሁ ለገሰፃችሁ እና መፍትሔ ለመከራችሁ ሁሉ
© ስለዳሞት ለዘገባችሁ ሚዲያዎች ዩቱበሮችና ለጻፋችሁ አክቲቪስቶች ሁሉ
© ያለ ከፍተኛ ደም መፋሰስ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለአደረጋችሁ ሽማግሌዎችና የሽማግሌዎችን ምክር ለሰማችሁ ወጣቶች ሁሉምስጋና ይገባችኋል ።
ሰላም ለአማራ!
ሰላም ለጎጃም!
ሰላም ለዳሞት!
ሰላም ለፈረስቤት!
ደጋ ዳሞት የቀድሞ የጅግንነትና የደግነት የከበረና ገናና ስሙን በጀግንነት እንደትናንቱ ዛሬም አሰጠርቷል!

የሰማሁትን ባልናገር ፣ የአየሁትን ባልመሰክር ነፍሴ ወደገሐነም ስጋዬ ወደመቃብር ይወርወር!

ከብዙ በትቂቱ ፣ ከረጅሙ በአጭሩ ከሰማሁት

የዳሞት ጀግንት ዳግም ልደት/Rebirth hero of the Damot።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ይህ ገፅ ለደጋ ዳሞት ጀግንነትና ደግነት የሰሩና የሚሰ...
30/06/2023

የዳሞት ጀግንት ዳግም ልደት/Rebirth hero of the Damot
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ይህ ገፅ ለደጋ ዳሞት ጀግንነትና ደግነት የሰሩና የሚሰሩ ሰዎች ስማቸው የሚዘከርበት ታሪካቸው የሚተረክበት የእናንተ የBieza Mera Mera ገፅ ነው ።
በBieza Mera Mera

ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ የድሕረ ገፃችን ተከታታዮች ሰሞኑን በአምሳለ ገነት ቅድስት ሐገር ጎጃም በደጋ ዳሞት የተሰራው ገድል ለአርያነት የሚጠቀስ ስለሆነ ከመነሻ እስከመድረሻው የተለያዩ ሰዎችን መጠይቅ አድርጌ ከረጅሙ በአጭሩ ለአስቃኛችሁ ወደድኩ ።
የዳሞት ጀግንነት ከራስ ደጀን የገዘፈ ፣ ከውቅያኖስ የጠለቀ ሁሉም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ዓለም ሲፈጠር ዘመን ሲቆጠር ጀምሮ ለመሆኑ ስሙ ዳሞት ማለት "እዳው ሞት ፣ ምግቡ ዶቄት ሐገሩ ሰቀልት" እየተባለ መተርጎሙ ለአብዛኛው ግልፅ ነው ።
ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደጋዳሞት ጀግኖቹ በተናጠል እንጅ በጋራ መነሳት ባለመቻላቸው በጀግንነት የገዘፈው ስሙ ወደመረሳት እየነጎደ ነበር ።

አሁን ግን ከወያኔ ኢሕአዴግ መንግሥት ጀምሮ አማራን ለማጥፋት በማንፌስቶ አርቅቆ በሕገመንግሥት አፀድቆ መላ አማራን ለበርካታ ግፍና ስቃይ ሞትን ስደት ሲዳርገው መላው አማራ ተንቀሳቅሶ ወያኔ ኢሕአዴግ ገለል እንዲል ሲደረግ ኦነግ ኢሕአዴግ ስሙን "ብልፅግና" ብሎ "ለውጥ አመጣሁ" በማለት ሕዝቡን አታሎ ከልቡ የሌለን "ኢትዮጵያ" እያለ ስለተናገረ የዳሞት ሕዝብም እንደሌላው ሁሉ ሰላም ይሰፍናል ብሎ ቢጠብቅም ለውጡ ግን በእባብ ከመነደፍ ወደ በዘንዶ መዋጥ ሆነ ። በቀላል የአባቶቻችን ንግግር "ከድጡ ወደማጡ" ሆነ ።
ስለሆነም በመላ አማራ በጎንደር ፣ በወሎ ፣ በሽዋና ጎጃም መንቀሳቀስ ጀመረ ።
ሁኖም ግን መንግሥትን አላወከም ፤ ተቋም አልዘረፈም ፤ ሕዝብ አግቶ ገንዘብ አልጠየቀም።

ይሁን እንጅ ኦነግ ኢሕአዴግ/ብልፅግና ቡድን ተቋም ከሚዘርፈው ፣ ሲቢል ከሚያገተው ፣ ከሚገድለው ከሚያፈናቅለው ይልቅ ወደ አማራ መከላከያ ብሎ የሚጠራውን ገዳይ ኃይል አሰማርቶ በ4ቱ ማዕዘን ዘራችን ከምድረገፅ መጥፋት የለበትም ያሉ ፋኖዎችን ማሳደደ ቢጀምርም በእየሔደበት አልሳካ ሲለው ቦታ እየቀየረ አንዱ ላይ ያጣውን ከሌላው ላይ የማገኝ መስሎት በሁሉም የአማራ አካባቢዎች ሙከራ እያደረገ ነው ።

እንደሌሎች ሁሉ በደጋዳሞት ፋኖ ላይም እንደ ውጭ ጠላት በከባድ መሳሪያ ታጅቦ መከላከያ እየተባለ የሚጠራው የኦነግ ኢሕአዴግ/ብልፅግና መንበርን አስቀጥላለሁ ብሎ የሚንቀሳቀሰው ገዳይ ቡድን ዘመተ ።
ዘመቻው ገና ብዙ ነገር የሚቀረው ቢሆንም እንዴት እንደነበር ቃለ መጠይቅ ያደረግሁትን አስቃኛችሗለሑ ።

ቤዛ መራ መራ ፦ ጤናይስጥልኝ ለቃለ መጠይቁ ፈቃደኛ ስለሆኑ አመሰግናለሁ ።

ክቡር አቶ ዳሞት ፦ እኔም የዳሞትን ገድል ተዚህ ቀደም ታሪካቸውን ጽፈሕ ለአንባቢ እንዳበቃሀቸው አርበኞች ሁሉ ይኽን የዳሞት ጀግንነት ዳግም መወለድ ለአንባቢ ለማሳወቅ ስለጠየቅኸኝ አመሰግናለሁ ።

ቤዛ ፦ ሰሞኑን ስለደጋ ዳሞት ብዙ ይነገራል ። የተከሰተውን ክስተት ፣ የተደረገውን ድርጊት በአጭሩ ቢነግሩኝ ?

ክቡር አቶ ዳሞት ፦ ታሪኩ በጣም ብዙ ነው ከየት ልጀመር?

ቤዛ ፦ ስለ ሰሞኑ ብቻ ከልሆነማ እውነት ነው ። ኧረ እንዲያውም የሰሞኑም ብዙ ነው ። ሁኖም ግን በአጭሩቢሆንም እንሞክረው ።

ክቡር አቶ ዳሞት ፦ መልካም አንተም እንደምታውቀው አማራ በሚባል ምድር በሁሉም አካባቢ ፋኖን ለማጥፋት መንግሥት ደፋ ቀና እያለ ነው ። የአማራ ሕዝብ ደግሞ ራሱን ከጥፋት ለመታደግ አልሞት ባይ ተጋዳይ ራሱን እየተከላከለ ነው። የዳሞት ፋኖዎች ሙሉ ትጥቃቸውን ታጥቀው አንድ ቀን ከአዲስ አበባ ጋር እኩል የተቆቆረች ነገር ግን በእደገት መንደር ትሁን ከተማ ለመለየት የምታስቸግር በደርግ መንግሥት እነ አቶ ውብሸት ፣ የአስር ዓለቃ ጥሩነህ ፣ መቶ ዓለቃ አዲስ አታላይ ፣ መቶ ዓለቃ አርጋው መንግሥቱ ፣ አምሳ ዓለቃ ታደሰ ፣ አያሌው ወንድም ፣ ተመስገን እምሩና ሌሎች የዘመኑ ተሿሚዎች ከጀመሩት ጅምር በስተቀር ይኽ ነው የሚባል ልማት ባላሳየች ከተማ ፣ አቶ አበባው ደስታና ወ/ሮ ትልቅሰው ገዳሙ ትንሽ ለማነቃቃት ከመጣራቸው በቀር የእየ ቀበሌ ከተሞች ኮብል ተነጥፎባቸው ፈረስቤት ግን ኮብል በማታውቅ እድገቷ እንደካሮት በሆነችው ከተማ በመሀል መንገድ ወደላይና ወደታች ተንጎራደዱባት መከላከያ ደግሞ ወደ ፋኖ ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ ፈረስቤት ከተማ ወድማ ዛሬ ታሪክ በሆነች ነበር ። እንደአመራሩ እንዘኽላልነት ፈጣሪ ታድጎናል ።
የፋኖዎችን መኖር የሚያውቀው ነበልባል
የፈረስቤት ሕዝብ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ የደርስንላችሁ መልክት ከያለበት እየተኮስ ፋኖዎች ወደአረፉበት ሆቴል ሲጎርፍ አመራሩ ያልጠበቀው ነገር ገጠመው ። ፋኖዎችም የታቀደላቸው ግድያ ቀርቶ ከእነ ክብራቸው ወጥተው በኩራት እና በጀግንነት መከላከያ ይመጣል ሲባል ስለሰሙ ጦርነቱ ከተማ እንዳይሆን ከተማውን ለቀው ወደ ደረቄ በኩል ራቅ ብለው ከመከላከያ ጋር የሚደረግን ፍልሚያ ሌማት ጠብቆ ለመብላት እንደተዘጋጀ እንግዳ ይጠባበቁ ጀመር ።
ይሁን እንጅ አስተዋይ የሆነው ጭዋ የከተማዋ ሕዝብ ስለሆነው አዝኖ አሁንም መከላከያ ቢመጣ የበለጠ እልቂት እንደሚከሰት አመራሮችን ማስጠንቀቂያ መሰል ምክር መክሮ መከላከያ እንዳይ ገባ አሰደረገ ።
ፋኖዎችም መከላከያው እንደቀረ ካረጋገጡ በሗላ አረፋ ተብሎ ወደሚጠራው ክፍለ ዳሞት ሔዱ ። ይህ በሆነ በሳምንቱ መከላከያ በሞጣ በኩል አድርጎ ወይንዉኃን አቋርጦ አረፋ ደብተራ/ ፍልቅልቅ አካባቢ ከበባ ፈፀመ ።
በዚህ ጊዜ ከባድ ውጊያ ተደርጎ ቀድሞ የመጣውን ኃይል ሲያሸንፍ ሌላ ተጨማሪ ኃይል ሲጨመር ለረጅም ሰዓት ስልጡኑ የአረፋ መንደር የጦርነት ማዕከል ሆነ ።
ጦርነቱ የተጀመረበት ሰዓት ምሸት ስለነበር ጨለማው ሽማግሌ ሁኖ ላልተወሰነ ጊዜ ገላገላቸው ። በነጋታው ጧት ሁሉም የዳሞት ሕዝብ በነቂስ የጠሊም ቀጠና ፣ የበርቀኝ ቀጠና እና የእናሞራ ቀጠና ወደ አረፋ እንደጉንዳን ባለመሳሪያ መሳሪያውን ይዞ መሳሪያ የሌለው አንካሴና ሌሎች መሳሪያዎችን ይዞ ተመመ ።
በተለይ የፈረስቤት ከተማ ሕዝብ የመንግሥት ሰራተኛ ቢሮ ስራውን ትቶ ሴት ወንድ ሳይል ጉዞውን ወደ ፋኖ አደረገ ።

ስልጡኑ የአረፋ ሕዝብ ፣ ስራ ወዳዱ የአረፋ ሕዝብ ጦርነት ተከፍቶበት ስራ አቁሟል ። የፈረስቤት ከተማ ጭር ብሏል ። አልፎ አልፎ ከሚነፍሰው ዝናባማ ነፍስ በስተቀር የሚንቀሳቀስ የለም ።
አረፋ ደብተራ/ፍልቅልቅ ትናንቱን በተደረገው ጦርነት አንድ አርሶ አደር ሲገድል ሌሎችም የቆሰሉ መኖራቸው ታውቋል ። አንዷ ሕፃን ሴት ስትሆን ጥይቱን በቀዶ ጥግና ያወጣላት ሐኪም ዓለሙ አዲሱ ለቤዛ መራ ስለሁኔታው አሰረድቷል ።

ሕዝቡ እንደሰናክሬም ሰራዊት አረፋ ላይ ከትሟል ። ፋኖ በአንድ በኩል መሽጓል መከላከያ በምሸቱ ውጊያ የሞተው ሙቶ የቆሰለው ቆስሎ ሌላ ኃይል ተትክቶ በአንድ በኩል መሽጓል ።
ይሄን ዜና የሰሙት የቢቡኛና የእነሴ እንደንብ ተናዳፊ ፋኖዎች ለዳሞት ፋኖ የሆላ ደጀን ለመሆን ገስግሰው መከላከያን ከበዋል ። የቋሪት ተርቦች ለራሳቸውና ለዳሞት ፋኖዎች ጥይት በኃይለኛው ጭነው ደርሰዋል ።
የዳሞት ግዝት የሆነችው አረፋ የዓለምን ቀልብ ስባ በተለያዩ የዓለማት ክፍል ያሉ አክቲቪስቶች ብዕራቸውን አንስተው ስለደጋዳሞት ፈረስቤት አረፋ የሚሰሙን የፋኖ አሸናፊነት እየጦመሩ ያስነብባሉ ። ዩቱቨሮች የንግግራቸው መክፈቻ በሰባር ዜናቸው አረፋን ያስቀድማሉ ሚዲያዎች የኦነግ ኢሕአዴግ/ብልፅግና ከሚቆጣጠራቸው ውጭ ያሉ ሁሉ ስለታላቁ ደጋዳሞት ሕዝብ አይበገሬነት ይተነትናሉ ። ስለአረፈዋ ፍልቅልቅ ውሎ ዜና ያሰራጫሉ ። አረፋ የዓለም የትኩረት ማዕከል ሁና ውጤቷን ለማወቅ የዓለም ሕዝብ ይጠብቃል ። በሩቁ የሚኖረው የዳሞት ተወላጅ በአፍሪካ ፣ በአሜሪካ ፣ በአውሮፓ እና በአረብ ሐገር ያሉ እውነተኛ መረጃ ይገኝበታል ያሉትን ሚዲያ ና ዩቱዩብ ያዳምጣሉ ። እውነተኛ ያሉትን አክቲቪስት ጽሑፍ እያነበቡ ውስጣቸው ይጨነቃል ።

በሐገር ውስጥ በተለያዩ ከተሞች ያሉ የወረዳው ተወላጆች ከዩቱዩቡና ሚዲያ ዜና ከአክቲቪስቱ ጽሁፍ በተጨማሪ በስልክ መረጃ በእየስዓቱ ይሰማሉ ። ውጤቱ በሕዝቡ አሸነፊነት እንደሚደመደም ቢታወቅም ስለሚከፈለው መስዋዕተነት ይጨነቃሉ ።
ሕዝቡን ሞትን ተጠይፎ ከመከላከያ ጋር አንገት ላንገት ሊተናነቅ ተዛግጅቶ ከፋኖ የተኩስ ፊሽካ ይጠብቃል ። መከላከያው መውጫ እንደሌለው ስላወቀ ውስጡ ተጨንቋል ።

አሰተዋዩ የዳሞት ሕዝብ የበርካታ ሕዝብ ደም ሳይፈስ በሰላም ስለሚፈታበት ሁኔታ ሽማግሌው መከረ ። አስር ካሕናት አስር ደግሞ ተሰሚነት ያላቸው ሽማግሌዎች ተሰየሙ ። ወጣቱ ግን ሽምግልናን አንቀበልም እንዋደቃለን አለ ።
በዚህ ጊዜ ከሽማግሌዎች መካከል ስለጦርነት ልምድ ያላቸው የቀድሞ ሠራዊቶች ስለነበሩ ለወጣቱ ማስረዳት ጀመሩ ።
ለምሳሌ ያኽን አንድ ሰው ልጥቀስ በደጋ ዳሞት ታሪክ አዋቂነት የሚታወቀው ምኒሻ አንተነህ መንግሥቱ ወደወጣቱ ቀርቦ እንዲህ ሲል አስረዳ ።

"ወንድሞቼ አሁን እናንተ እንዳላችሁት ይህን መከላከያ መስዋትነትነት ከፍለን መያዝ እንችላለን ። ይሁን እንጅ ይህ መከ

ዳሞት ዳሞት አትበይ በወሬ ሰምተሽው፣ጀግንነቱን ሳታይ በቅረበት ቀርበሽው፣በሩቅ እንደሰማሽ ታሪክ ተቀንጭቦ ፣ዛሬ ነይ ላሳይሽ ጀግንነት በደቦ ።
28/06/2023

ዳሞት ዳሞት አትበይ በወሬ ሰምተሽው፣
ጀግንነቱን ሳታይ በቅረበት ቀርበሽው፣
በሩቅ እንደሰማሽ ታሪክ ተቀንጭቦ ፣
ዛሬ ነይ ላሳይሽ ጀግንነት በደቦ ።

28/06/2023

 ( በብዙአየሁ ደስታ .የተቀነጨበ..)ጀግናው ደጋ ዳሞት አረፋ ደብተራ፣ግርማው የገነነ ሲሄድ የሚያስፈራ፣የጭንቅ ቀን ደራሽ ጠበቃ ለአማራ።
28/06/2023


( በብዙአየሁ ደስታ .የተቀነጨበ..)
ጀግናው ደጋ ዳሞት አረፋ ደብተራ፣
ግርማው የገነነ ሲሄድ የሚያስፈራ፣
የጭንቅ ቀን ደራሽ ጠበቃ ለአማራ።

Address

Dega Damot
Feres Bet

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የዳሞት ፍሬ/Damot's Fruit posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share