08/10/2025
#በመንግሥት ሠራተኞች የሚፈጸሙ #ከባድ #የዲስፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች👇
የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ መሠረት የሚከተሉት ጥፋቶች ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች ናቸው፤
👉ሕጋዊ ትእዛዝን ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣ በመለገም፣ ወይም ሆነ ብሎ የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ወይም የመንግስትን ፖሊሲ ባለመከተል በሥራ ላይ በደል ማድረስ፤
👉ጉዳዮችን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም ባለጉዳዮችን ማጉላላት፤
👉ሥራ እንዳይሠራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፤
👉በቀላል የዲስፕሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረት ወይም የሥራ ሰዓት አለማክበር፤
👉በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነት መደባደብ፤
👉በልማዳዊ ስካር ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፤
👉ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ፤
👉በሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈጸም፤
👉የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም፤
👉የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም፤
👉በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤
👉በሥልጣን አለአግባብ መጠቀም፤
👉በሥራ ቦታ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት መፈፀም፤ እንዲሁም ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈጸም፡፡