Fidoriያ

Fidoriያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fidoriያ, Media, Ethiopia~Bale Goba, Goba.

17/02/2026
05/02/2026

Join us on tiktok 👉" "

05/02/2026

ይድረስ ደብዳዬ ለምወድሽ እና ዘዉትር ለምትናፍቂኝ ለዉዷ እናቴ....... 😕🪖
Letter from soldier to his mother
👇መታየት ያለበት ቪዲዮ 👇

32 likes, 2 comments. “🪖🫡”

"እንጋባ" ሲል ጠየቃት አሳምነው ። አልተቀበለችውም አስማሩ "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው። ተስማሙ ቤት እየመጣ ይጠይቃታል። ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ ካላት ታቀርባለች ይበላሉ። አወግ...
30/12/2025

"እንጋባ" ሲል ጠየቃት አሳምነው ። አልተቀበለችውም አስማሩ "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው። ተስማሙ

ቤት እየመጣ ይጠይቃታል። ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ ካላት ታቀርባለች ይበላሉ። አወግተው ይለያያሉ። የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም። አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ መጣ። እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ። ስለ ሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ።
አስምሩ አሰምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት። ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም ጃኬቱን አውልቆ ሄደ። አስምሩ እሱንም አጥባ አኖረችው
ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ!" አወለቀው።

አስማሩ አጥባ አኖረችው ካፕርቱን ጥሎ ሄደ ፣አጥባ አኖረችው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ ፣አስማሩ "ምነው?" አለችው በጠራራ ፀሀይ ብርድ ሆዴ ገባ አላት ። "ምች ይሆናል" አለችው ። የምች መድኀኒት ብታሽለት ተሻለው ። ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎት ሄደ። አስማሩ አጥባ አኖረችው።

ትንሽ ቆይቶ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ ።
"ምነው?" አለችው ።
"ላሳድሰው መሄዴ ነው ። አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው"አላት
አመነችው
ጨዋታው ደራ ፣ ፍራሹን ረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ቢመጣ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ፍራሿ ላይ ደርባው ደረሰ..ያኔ "ተነሼ ከማለት "ጠጋ በይ" ማለት ቀልሎ ተገኘ።
ጠጋ አለች 😊🅦🦋

ደራሲ:- ዓለማየሁ ገላጋይ

"አንዴ ነው " ይሉኛል ፣ "በፍቅር መጎዳት""አንዴ ነው" ይሉኛል ፣ "ባመኑት መከዳት።"እኔ ግን አላምንም!ካለፈ ህይወቴ ፣ አላውቅም ተምሬአውቃለሁኝናብዙ ተጎድቼ ፣ ብዙጊዜ አፍቅሬ፡፡።።።በ...
25/12/2025

"አንዴ ነው " ይሉኛል ፣ "በፍቅር መጎዳት"
"አንዴ ነው" ይሉኛል ፣ "ባመኑት መከዳት።"
እኔ ግን አላምንም!
ካለፈ ህይወቴ ፣ አላውቅም ተምሬ
አውቃለሁኝና
ብዙ ተጎድቼ ፣ ብዙጊዜ አፍቅሬ፡፡
።።።
በፍቅር መንገድ ላይ ፣ ተክዤ ተጉዤ
የማውቃቸው ሁሉ
የሸለሙኝን መልክ ፣ ጠባሳ ልብ ይዤ
አንቺ ጋራ ስደርስ...
ልብሽና ልቤ ፣ እንደተሳሳበ
እንዳዲስ ሳፈቅር...
ወደ ነፍሴ ምድር ፣ ጥያቄ ዘነበ፡፡
።።፣
ቆይ ስንቴ ነው መውደድ ፣ ስንቴ ነው መጎዳት
ቆይ ስንቴ ነው ማመን ፣ ስንቴ ነው መከዳት?
ለስንት ጊዜ ነው?
ሲሄዱ መራገም ፣ ሲመጡ መመረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
እርሜ ነው እያሉ ፣ በመሃላ መታረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
መተው መርሳት ሲቻል ፣ በማስታወስ ማፍቀር
ስንቴ ነው መታቀፍ ፣ ስንቴ ነው መገፍተር?
።።።
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?!
በብቸኝነት ውስጥ ፣ በአብሮነት መቀጣት?
ለካንስ ለካንስ
ለመንገደኛ ልብ
ተራ ጥያቄ ነው ፣ መሄድና መምጣት!
አቦ ወግጅልኝ!
መልስ ነው በራሱ
ለተራ ጥያቄ ፣ ተራ መልስ ማጣት!!!

©በላይ በቀለ ወያ

24/12/2025

*ደህና መሽቶ ደህና ነጋ
🙏ተመስገን ነዉ ያንተ ዋጋ🥰

        !!" የሆነን ሰው መሆን እየተመኘህ በሄድክ ቁጥር የዛ ሰው ኮፒ ስብእና እንጂ የራስህ የሆነ ማንነትና እውቀት እንዲሁም ተጽዕኖ አይኖርህም! ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ልትጥለው የሚገባ...
24/12/2025


!!

" የሆነን ሰው መሆን እየተመኘህ በሄድክ ቁጥር የዛ ሰው ኮፒ ስብእና እንጂ የራስህ የሆነ ማንነትና እውቀት እንዲሁም ተጽዕኖ አይኖርህም! ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ልትጥለው የሚገባው ነገር እንደ እገሌ መሆን እፈልጋለሁ ወይም እንደ እሱ እሆናለሁ የሚለውን አባዜ ነው ። አንተ ማንንም ለመምሰልም ሆነ ማንንም ለመሆን አልተፈጠርክም ። አንተ አንተ ነህ እገሌም እገሌ ነው ። "

/ ኦሾ /

Address

Ethiopia~Bale Goba
Goba
FIDEL5747

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fidoriያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category