Gashaw Getnet

Gashaw Getnet አንቺ የወላዲተ አምላክ የአሥራት አገር
ኢትዮጵያ ሆይ ተነሺ!!!

† የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር እየጨመረ ነው †« አንድ፡ጌታ፡አንድ፡ሃይማኖት፡አንዲት፡ጥምቀት» ኤፌ 4፥5★ በአፍሪካና በሌሎችም አህጉራት  የኦርቶዶክስ እምነትን ፈልገው እየመጡ የሚጠመቁ አማኞች ...
20/09/2025

† የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር እየጨመረ ነው †

« አንድ፡ጌታ፡አንድ፡ሃይማኖት፡አንዲት፡ጥምቀት» ኤፌ 4፥5

★ በአፍሪካና በሌሎችም አህጉራት የኦርቶዶክስ እምነትን ፈልገው እየመጡ የሚጠመቁ አማኞች ቁጥር እጅግ እየበዛ ነው።★

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት አስተምህሮና ሥርዓተ አምልኮ ውስጣቸው ያረፈ ፣ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነትና በመንፈስ የሚመልክባት ብቸኛዋ የእግዚአብሔር መንግሥት መሆኗ የገባቸው አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ጥሪ እየተማረኩ ብዙዎች ከፕሮቴስታንት ቤተ እምነት፣ከእስልምናና ከእምነት የለሽነት አመለካከት እየተላቀቁ በታላቅ ደስታ ወደ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እየመጡ ነው።

እነዚህ በማዳጋስካር በመጠመቅ ላይ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

ኢትዮጵያውያን ፕሮቴስታንትና ሙስሊም ወገኖቻችን የመዳን ቀን ዛሬ ነውና ወደ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መጥታችሁ ለነፍሳችሁ መዳንን ታገኙ ዘንድ ቤተክርስቲያን በፍቅር ትጠራችኋላች እስከዛሬ በስህተት የተጓዛችሁበት ዘመን ይበቃል ።

እግዚአብሔር ይወዳችኋል።

ለሌሎችም አጋሩት

ከዚህ በኋላ በማርክሲዛውን አስተምሮ የማሸወድ ትውልድ አይኖሮም****ግዕዝ እንደ ቋንቋ ዳግም ትንሳኤ የሚያገኝበት ዘመን እየመጣ ነው። በአማራ ክልል የተጀመረውን  ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ የማስ...
19/09/2025

ከዚህ በኋላ በማርክሲዛውን አስተምሮ የማሸወድ ትውልድ አይኖሮም
****
ግዕዝ እንደ ቋንቋ ዳግም ትንሳኤ የሚያገኝበት ዘመን እየመጣ ነው። በአማራ ክልል የተጀመረውን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ የማስተማር ዜና አጣጥመን ሳይንጨርስ በትግራይ ክልል በከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ሥር የሚተዳደረው የከሳቴ ብርሃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግዕዝን ከ1ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ ወስኗል።
ከዚህ በኋላ በማርክሲዛውን አስተምሮ የማሸወድ ትውልድ አይኖሮም። የአባቶቻችን የሆነውን ሁሉ ከፍ አድርገን ለልጆቻችን እናስተምራለን። ወደ ጥንቱ የከፍታ ዘመንም እንመለሳለን። ከዛ ከፍታ ላይ ሆነን በማንነታችን ላይ የሚመሰረት ዘመናዊ ስልጣኔን እናዋልዳለን።

"ማንም መንገደኛ አያደናግረን!"ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ እንደ ፃፈው(፩) የግዕዝን ቋንቋ ከሰኩላሪዝም (Secularism) አንጻር ስናዬው...የግዕዝ ቋንቋ የሦስተኛ ክፍል የተማሪዎች መጽሐፍ ደ...
18/09/2025

"ማንም መንገደኛ አያደናግረን!"

ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ እንደ ፃፈው

(፩) የግዕዝን ቋንቋ ከሰኩላሪዝም (Secularism) አንጻር ስናዬው...

የግዕዝ ቋንቋ የሦስተኛ ክፍል የተማሪዎች መጽሐፍ ደርሶኝ እያገላበጥኩ ሁሉንም አየሁት። የሶስተኛ ክፍል የተማሪዎች መጽሐፍ 83 ገጽ አለው። ሲያጠናቅቅ ከግዕዝ ቋንቋ ወደ አማርኛ ቋንቋ የሚፈታ የሙዳዬ ቃላት ይዟል።

መጽሐፉን ሳዬው በትክክል የተዘጋጀ መሆኑን አይቻለሁ። የንግግሩ ቃላት ሁሉ እምነትን እንዳይነካ ሆኖ በጥንቃቄ የተዘጋጀ መሆኑን አረጋግጫለሁ። የግዕዝ ቋንቋን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አስጠግታው እንደኖረች እሙን ነው። ይህን ሁሉም ያምናል። ሙስሊሙም ክርስቲያኑም። ግን ወደ ልጆቹ ሲመጣ አስጠግታ ያቆየችው ሃይማኖት አለችና የእነርሱን እምነት እንዳይሰብክ ልጆቻቸውን መከላከሉ ከእናትና ከአባት የሚጠበቅ ነው። ግን እነርሱ ሳይሆኑ የሚከራከሩት መጽሐፉን ያላዩት የፖለቲካ ጥገኞች የሆኑ ሰዎች መሆናቸውን መጽሐፉን እኔም ካየሁት በኋላ አረጋግጫለሁ። እንዲያውም ከተዋህዶ ሃይማኖት ጋር የግዕዝ ቋንቋ ተጠግቶ ስለኖረ አስጠግታው የኖረችውን ሃይማኖት ጥቅሶች እንዳያመጣ ስግቼ ነበር። እንደዛ ያለ ነገር ግን መጽሐፉን በማነብበት ወቅት አላገኘሁም። የግዕዝ ቋንቋ እና ሃይማኖት የተለያዩ እንደሆኑ ይህን መጽሐፍ ያዘጋጁት ሰዎች፣ ብልህ እንደሆኑ መጽሐፉን ሳነብ አረጋግጫለሁ። የመጽሐፉ "ኮፒ ራይት" ይዞኝ እንጂ ሙሉውን ለእናንተ እለጥፈው ነበር። የአዘጋጁት ሰዎች እና የተረከበው አካል መፍቀድ አለበት።

በአማርኛም የትኛውንም እምነት መስበክ ይቻላል። የእስልምናንም ሆነ የትኛውንም የክርስቲያን እምነት በማንኛውም ቋንቋ መስበክ ይቻላል። የግዕዝን ትምህርት በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ለማስገባት ያሰቡ ሰዎች ሴኪውላር ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። በፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ሰኩውላሪዝምን (Secularism) ስናዬው፣ ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ ናቸው። እኔ ግን እንደ ሀሳብ የምሰጠው፣ ኢትዮጵያ ከፖለቲካ የፀዳ ትልቅ የቋንቋ ተቋም ያስፈልጋታል። በዛ ተቋም ተገምግሞ አልፎ ቢሄድ ኖሮ እስከ አሁን የግዕዝ ቋንቋ ባላነታረከን ነበር። ማንም መንገደኛ አያደናግረንም ነበር። ከቋንቋዎች ሁሉ ደግሞ የመጀመሪያውና ኢትዮጵያን የምናስጠራበት ቋንቋ አንዱና ዋነኛው ግዕዝ ነው። የኢትዮጵያ ቀርቶ የአፍሪካ ሁሉ ኩራት ነው።

ግዕዝ ቋንቋውን ግን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አስጠግታው ስለኖረች፣ ከዛ አንዳንድ ጥቅሶች እንዳይገቡ መጠንቀቅ ያሻል ብዬ ነበር ግን መጽሐፉን ሳነበው ምንም የሚያጨቃጭቅ ነገር አላዬሁበትም። በጥራዝ ነጠቅ ያወሩ ሰዎች ነበር የሚያደናግሩን። በተለይም ከዚህ በፊት የተለጠፉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎች መጽሐፍ ከጎግል ላይ እያወጡ በትምህርት ስርዐቱ ውስጥ የገባ መስሎን እኔም ብዙ ሰዎችን በስልክ መከራቸውን ሳበላ ነበር። ግን በፍፁም እንደዛ እንዳልሆነ መጽሐፉን ሳነብ አረጋገጥኩ። ወደ ፊት በስርአተ ትምህርቱ ውስጥ የግዕዝ ትምህርት እየሰፋ ሲሄድ፣ መጽሐፍ የሚያሰናዱ ሰዎች እንደዚህ መጽሐፍ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የማንኛውንም እምነት እንዳይነካ፣ የትኛውንም ሃይማኖት እንዳይጎሽም አድርገው የማስተላለፍ ግዴታ አለባቸው። ይህ ግዴታ ነው።

(፪) የግዕዝ ቋንቋ አስተማሪዎች እነማን ይሁኑ?

የግዕዝን ቋንቋ የሚያስተምሩት ዲያቆናትና ቄሶች ናቸው ይባላል። ሃይማኖቱ አስጠግቶት ስለኖረ፣ እምነትን እንዳነካ አድርገው የተማሩት እንዲያስተምሩ መሆን አለበት። ያውም ከዩኒቨርስቲ የተመረቁ ቢሆን ይመረጣል። የግዕዝ ቋንቋ ሰኩላር (Secular) እየሆነ ሲመጣ ግን ሙስሊሞቹ ሰኩላር (Secular) ሆነው ማስተማር አለባቸው። አንድን ቋንቋ እየተጸየፍክ ግን እንኳን ለማስተማር ለመማርም አትበቃም። አንዳንድ የወሎ ሙስሊሞች ግዕዝ ያውቃሉ። እኔ ዛምራ የተባለው ልቦለዴን በምጽፍበት ወቅት ያገኘኋቸው አንድ ሙስሊም ሰው በግዕዝ ቋንቋ አውርተውኛል። እንዴውም የመጀመሪያውን ምዕራፍ የሰጠሁት አንድ ሙስሊም ልጅ ወደ ቅኔ ቤት ሲገባ የሚያሳዬውን ጠባይ በመንተራስ የተፃፈ ነው።

(፫) የግዕዝ ቋንቋ የጠንቋዮች እና የደብተራዎች እውቀት ነው ለሚሉ...

ጠንቋይ ማለት አደናጋሪ ማለት ነው። አምታቺ ነው። የማታውቀውን ቃል ያነበልብልሃል። የማታውቀውን ቃል ከግዕዝ ቃል እያወጣ መተት ደገምኩልህ ሊልህ ይችላል። እንዲያውም ከድግምት ቃላት ውስጥ አረብኛም በብዛት አለበት። ትናንት አንዱ የለጠፈውን የመተት ቃል አይቼ በሳቅ ፈረስኩ። የለጠፈውም ሰው እርሱ ሙስሊም ነኝ ይላል። ግን ቃላቱን አይቼ ስመረምረው ባብዛኛው የአረብኛ ቃላት አሉበት። ጫጫጫጫ ጃጃጃጃጃ ከሚለው ውስጥ አንዳንድ በተን በተን ያሉ የግዕዝ ቃላት አሉበት። ጳጳጳጳ ፓፓፓፓፓፓ ከሚለው ውስጥ ደግሞ ብዙ የአረብኛ ቃላት አሉበት። አስማተኞች መተተኞች እንዳይበሉን እንወቅ። ካላወቅክ ደግሞ ይበሉሃል። ይሸጡሃል። እንዳትሸጥ እወቅ። በሁሉም ቋንቋ መተት አለ። ድግምት አለ። በእንግሊዝኛም፣ በጀርመንኛም፣ በፈረንሳይኛም ድግምት አለ። እንዲያውም በአፍሪካ ቋንቋዎች አይብስም? በናይጀሪያማ አስማቱን የግላቸው ያደረጉት ይመስላል። ከዛ ውጪ ወደ አስማቱ ስንወርድ የተለያዩ የሚያምታቱ እና ብዙሃኑ የማያውቃቸውን ቃላት አሰማተኞች ይደርታሉ። ካላወቅህ ተበላህ ነው የምልህ። ይሸጡሃል። ይለውጡሃል። ገንዘብህን ንብረትህን ትበላለህ።

የግዕዝ ትምህርትን አትማሩ ማለት ግን የጠንቋዮች ስብከት ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም አስማቱን ካወቅክባቸው በምን ሊደግሙት ይችላሉ? ይህ ይሰመርበት።

(፬)ከህክሞና አንፃር...

የግዕዝ መጻሕፍት የህክምና፣ የስነፈለግ፣ የኬሚስትሪ የእፅዋት ሳይንስን፣ የፊዚክስ ሁሉ አጭቀው ነው የያዙት። ይህን ፍለጋ ነው ነጮች የግዕዝን ቋንቋ ለማዎቅ የሚፈልጉት። ከዚህ አንጻር ሌላ ጊዜ መመለስ አለብኝ። አሁን ተዘርዝሮ አያልቅም።

እኔ በልጅነቴ ነው ሰባተኛ ክፍል ሆኜ ወደ ሀዋሳ የሄድኩት። ሀዋሳ ማለት የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ያለበት ከተማ ናት። ተማሪቹ አፋቸውን የፈቱበት የየራሳቸው ቋንቋ አላቸው። በተጨማሪም አማርኛ፣ እንግሊዝኛ እና ሲዳምኛ ትምህርት ቤት እንማራለን። ብዙዎቹ ተማሪዎች ባለ ብዙ ቋንቋ (Multilingual) ናቸው። እኔ ግን በልጅነቴ የግዕዝ ቋንቋ በመማሬ በእርሱ እንኳን ተጽናናሁ እንጂ ከአማርኛ በቀር በምንም አልግባባቸውም ነበር። አማርኞዬም ለእነርሱ ይከብዳቸው ይመስለኛል። ብቼኝነቴ ከመጽሐፍ ጋር አቆራኘኝ። ብቼኝነቴ እንድጽፍ ገፋፋኝ። ስለዚህ ሰናጠቃልለው የግዕዝ ቋንቋንተማሪዎች መማራቸው ሊበረታታ ነው የሚገባው። በሌላ ክፍለ ሀገር ያሉት ባለ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው። ቢያንስ አንድ ቋንቋ በተጨማሪ ቢማሩ ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ። ጥሩ ጊዜ ከመጣ ደግሞ በሁሉም ክፍለሀገር ቢሰጥ ጥሩ ነው። ግዕዝ ማለት የሁላችንሞ ቋንቋ ነው። ከመጽሀፉ ላይ አልፎ አልፎ ለምስክርነት እንዲረዳ ተጠቅሜአለሁ። ሰናይ ጊዜ።

 #የኢትዮጵያን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የአለምን ታሪክ በቅጡ ለመረዳትና ለማጥናት  #ግዕዝን መማር የግድ ይላል።‼️ #ግዕዝን ማጥናት/መማር ለምን አስፈለገ⁉️ #ኢትዮጵያዊያን እንዲገቡ የማይፈቀደ...
18/09/2025

#የኢትዮጵያን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የአለምን ታሪክ በቅጡ ለመረዳትና ለማጥናት #ግዕዝን መማር የግድ ይላል።‼️
#ግዕዝን ማጥናት/መማር ለምን አስፈለገ⁉️
#ኢትዮጵያዊያን እንዲገቡ የማይፈቀደው ''The britsh libraray Ethiopic Geez book''‼️

#ሀገራችን የሰው ልጅ መገኛ ናት ካልን የፊደል፣ የአሀዝ፣ የስነጽሁፍ፣ የሰነጥበብ መገኛ ናት ለማለት ያሰደፈራል፡፡ አንዳንድ መዛግብት እንደሚያስረዱት የግእዝ መገኛ ከአዳም፣ ኖህ፣ ካም አንዲሁም ከሴም እንደሆነ እና አዳምም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ አዳም የተፈጠረዉ ማእከላዊ ምደር ላይ ነዉ ሰለዚህ ማእከላዊ ምድረ ወይንም የምድር ወገብ የሚያልፈው በኢትዮጵያ ነዉ ስለዚህ አዳም ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ የግእዝ ቋንቋ ከ700 አመተ አለም በፊት ለስነፅሁፍ ሙያ ውሏል፡፡ የሚገረመው ነገር ከአሜረካ ሀርቫረድ ዩኒቨርስቲ፣ ከጀረመን ሀምበረግ ከጣሊያን ካረሚና እና በእንግሊዝ፣ በጀረመን በዩኒቨርስቲዎች በስፍት ይሰጣል፡፡

ለምን የግእዝን ቋንቋ ለማወቅ ፈለጉ❓❗
ምን ይጠቅማቸዋል❓❗

#የተወሳሰበዉን የአለማት ምስጢር ለማወቅ የኢትዮጵያን የሆነዉን ሀብት መፀሀፍ ሄኖክን በአጭበርባሪዉ በጀምስ ብሩስ የተሰረቀውን በግእዝ የተፃፍዉን የዚህን መፀሀፍ ምስጢር ለመፍታት ከአለም የተወጣጡ የሀይማኖት መሪወች፣ ተመራማሪወች ከኢትዮጵያውያን አባቶች ዉጭ ሚስጥሩን ለመፍታት በአወሮፓ ሁሌም ጥናት እና ምርምረ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ታዉቃላችሁ? ለምን? ብዙ መልሶች አሉት፡፡

#የኛ የኢትዮጵያን ንብረት የሆኑት ነገር ግን በተለያዩ አጋጣሚ ወደ ዉጭ ሀገረ ተሰርቀው የተወሰዱ መፃህፍት እንዳሉ ይታመናል ከእነዚህም የተወሰኑትን እንመልከት፡፡👇

1-እንግሊዝ...2804
2-ፈረንሳይ...854
3-ጀርመን ...511
4-እስራኤል...386
5-ቫቲካን...286
6-አሜሪካ ...401
7-ጣሊያን...108
8-ቤልጀም..71
9-ሲውዘረላንድ...38
10-ኦስትርያ..37
11-ሲዊዲን..12
12-ሆላንድ..4
13-ካናዳ....3
#በአጠቃላይ 5,515 መፃሂፈት በላይ ከብዙ የአለማት ሀገራት በብዛት መፃሂፍቶቻችን የተወሰዱት እንግሊዝ ሲሆን 2,804 የብራና መፃሂፍቶች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የፍልስፍና፣ የዜማ፣ የቅዱሳን ህይወት፣ ህክምና፣ የጥበብ......የመሳስሉት ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ነገር ማንም ሀበሻ ወደ ''The britsh libraray Ethiopic Geez book'' ከዚህ ሙዚየም ገብተው መጎብኘት አይችልም፡፡ ይህ እንዴት የማል? ግን የኢትዮጵያውያን የከፈታ ዘመን ይመጣል በተስፋ እንጠብቃለን፡፡

10/09/2025

መልካም አዲስ አመት👏
2018🌻

‹‹መድኃኔዓለም›› ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒትማለት ነው።ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክ...
02/09/2025

‹‹መድኃኔዓለም›› ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት
ማለት ነው።

ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው፡፡ምን ዓይነት ፍቅር ነው?

ወንድሜ/ እህቴ አስባችሁታል ግን ለኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው፡፡ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን፡፡

ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው፡፡ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት፡፡እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር።

ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት
አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር፡፡

ምክንያቱም እንዲህ ነው ተብሎ ሊነገር በማይቻል ፍቅር የወደደን በደሙም የዋጀን ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ እኛን አዳነን።

መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን!

+ ድንግል ማርያም ተነሥታለች! +        ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በልጅዋ ፈቃድ ከሞት መነሣት ኦርቶዶክውያን አባቶች ሲያስተምሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሱት ማስረጃ በመዝ. ...
22/08/2025

+ ድንግል ማርያም ተነሥታለች! +

ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በልጅዋ ፈቃድ ከሞት መነሣት ኦርቶዶክውያን አባቶች ሲያስተምሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጠቅሱት ማስረጃ በመዝ. 131፡8 ላይ ያለውን ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን ቃል ነው፡፡ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ትንሣኤ ጋር አያይዞ መጥቀስ አሁን የተጀመረ ነገር ሳይሆን ብዙ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነገር ነው፡፡ ሠላሳ ሦስተኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ከእርሱ ቀድመው የተነሡ አበው ያስተላለፉለትን የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ ታሪክ የዛሬ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊት በጻፈው ድርሳን ላይ ፣ በነገረ ማርያም ሊቃውንት ዘንድ Doctor of Dormition በመባል የሚታወቀው ሊቁ ዮሐንስ ዘደማስቆ ፣ ሐዋርያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በድርሳኖቻቸው ላይ ስለ ድንግል ማርያም ትንሣኤ ባነሡና በዓለ ዕርገትዋን ባከበሩ ቁጥር የሚያነቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ቃል ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? ‹ማርያም ተነሣች› የሚል ነገር አለውን? የሚለውን ጥያቄ በዚህች አጭር ጽሑፍ እንመለከታለን፡፡ ወደዚህ ጉዳይ ከመግባታችን በፊት ግን አንድ ቁምነገርን እናስቀድም፡፡

በሐዲስ ኪዳን ለምናምን ፣ በወንጌል ለምንመራ ክርስቲያኖች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ምን ያደርጉልናል? የሙሴ ሕግጋት ፣ የነቢያት መጻሕፍት ፣ የዳዊት መዝሙራት ለክርስቲያኖች ምን ይጠቅሙናል? ብለን ከመጠየቅ እንጀምር፡፡ የዚህ ጥያቄ መልሱ ጌታችን ‹‹በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ሊፈጸም ይገባል›› እንዳለው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ በምሥጢር የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ስለሆነ ነው፡፡ (ሉቃ. 24፡44) ‹ከሙሴና ከነቢያት ጀምሮ ስለ እርሱ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ተብሎ የተነገረላቸው የኤማሁስ መንገደኞች ‹በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትን ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?› ብለው እንደተናገሩ ብሉይ ኪዳን በእርግጥ ስለ ክርስቶስ እንደሚናገር በሚገባ ትርጉሙን ከተረዳን ልባችን በጥልቅ ተመሥጦ ይቃጠላል፡፡ ይህንን የአባቶችን ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ መነፅር በዓይናችን ካጠለቅን ብሉይ ኪዳንን እያነበብን በሐዲስ ኪዳን ባሕር ውስጥ መዋኘት እንችላለን፡፡ በኅብረ አምሳል (Typology) አስቀድሞ የተነገረበትን ምክንያት (Primary application) እና ፍጻሜውን (Ultimate fulfillment) ስንረዳ በታሪክና ትንቢት ሁሉ ውስጥ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን እያገኘነው ስንደነቅ እንኖራለን፡፡

በገነት መካከል ተኝቶ ከጎኑ የሁላችንን እናት ሔዋንን ያስገኘውን አዳም ታሪክ ስናነብ በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ በመስቀል ላይ አንቀላፍቶ ከጎኑ በፈሰሰው የጥምቀት ውኃ የሁላችን እናት ቤተ ክርስቲያንን ያስገኘውን ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ ወይን ጠጥቶ ሰክሮ ዕርቃኑን የወደቀውንና ካም ሲዘብትበት ፣ ሴምና ያፌት ዕርቃኑን የሸፈኑለትን የኖኅን ታሪክ ስናነብ የሞትን ጽዋ ጠጥቶ በሰው ልጅ ፍቅር ሰክሮ ዕርቃኑን የተሰቀለውንና አይሁድ ሲዘብቱበት ፀሐይና ጨረቃ ዕርቃኑን የሸፈኑለትን ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ አብርሃም የሚወደውን ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ መፍቀዱንና በግ የመሠዋቱን ታሪክ ስናነብ አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን የወደደውን እግዚአብሔር አብንና እስከ ሞት ድረስ የታዘዘ ልጁን ንጹሑን በግ ክርስቶስን እናየዋለን፡፡ ዳዊት ጎልያድን ድል አድርጎ እስራኤልን ነጻ ሲያወጣ ስናይ ክርስቶስ ዲያቢሎስን ድል አድርጎ የሰው ልጅን ነጻ ሲያወጣ ይታየናል፡፡ እስራኤል በበረሃ ተጉዘው በበትር ከተመታው ከዓለት ውኃ ፈልቆላቸው ሲጠጡ ስናይ በዕለተ ዓርብ ጎኑን በጦር ተወግቶ በደሙ ጥማችንን ያረካልን መድኃኔ ዓለም ይታየንና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ‹ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ› እንላለን፡፡

ወደ መገናኛው ድንኳን ገብተን ደብተራ ኦሪትን ብንጎበኝ እንኳን ክርስትናችን አይለቀንም፡፡ በመሠዊያ ላይ የሚሠዋውን በግ ስናይ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕሊናችን ይመጣብናል፡፡ ወደ ድንኳኑ ዘልቀን በመቅረዙ ላይ መብራት ሲበራ ስናይ እውነተኛው ብርሃን ክርስቶስ ፣ ዕጣን ስናይ የኃጢአት ሽታችንን ያራቀልን ክርስቶስ ፣ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ስናይ በመለኮቱ መለወጥ የሌለበትን ክርስቶስ ፣ መናውን ስናይ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስ እየታየን እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ‹‹ልባችን እየተቃጠለ ለካስ ኦሪትና ነቢያት ሁሉ የሚናገሩት ስለ ክርስቶስ ነበረ?›› እንላለን፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ከሆንን ደግሞ ጌታን ባገኘንበት ሥፍራ ሁሉ እመቤታችንን ፍለጋ ማማተራችን አይቀርም፡፡ አዳምን የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ስናየው አዳምን ያለ አባት ያስገኘችዋ መሬት ያለ ወንድ ዘር የወለደችውን ድንግል ሆና ትታየናለች፡፡ አብርሃም የሠዋውን ከዱር ቀንዱ እንደታሰረ የወጣ በግ ስናይ የድንግልናዋ ማኅተም ሳይፈታ የወለደችው የበጉ እናት ትታየናለች፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ገብተንም አናርፍም ፣ እርሱ መብራት ሆኖ ሲታየን እርስዋ መቅረዝ ትሆንልናለች፡፡ እርሱ ዕጣን ሲሆን እርስዋ ማዕጠንት ትሆናለች ፣ እርሱ ታቦት ሲሆን እርስዋ ታቦቱ ያለበት ቅድስተ ቅዱሳን ትሆናለች ፣ እርሱ ጽላት ሲሆን እርስዋ የጽላቱ ማደሪያ ታቦት ትሆናለች ፣ እርሱ በጽላት ላይ የተጻፈው ቃል ሲሆን እርስዋ ጽላት ትሆናለች ፣ እርሱ የተሰወረ መና ሲሆን እርስዋ የመናው መሶበ ወርቅ ትሆናለች፡፡ ለሰብአ ሰገል ‹ሕጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት› እንደተባለላቸው እኛም በሔድንበት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ የጌታችንን ምሳሌ ባነበብንበት ሥፍራ ሁሉ እናቱንም እናያታለን፡፡

እውነቱን ለመናገር ለመመርመር ትዕግሥት ላለው ሰው ስለ ክርስቶስ በሚናገሩት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እንኳን ድንግል ማርያምን ቀርቶ ከሐዲው ይሁዳንም ማግኘት ይቻላል፡፡ ዮሴፍ የክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ዮሴፍ በሃያ ብር እንዲሸጥ ሃሳብ ያቀረበው ወንድሙ ይሁዳ የአስቆሮቱ ይሁዳ ምሳሌ አይደለምን? ፍልስጤማውያንን ድል ያደረገው ናዝራዊው ሶምሶን የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ሶምሶንን እየሳመች አሳልፋ የሠጠችው ደሊላ ስሞ የሸጠው የይሁዳ ምሳሌ አይደለችምን? አባቱን ለመግደል ሲያሴር ኖሮ መጨረሻ በዛፍ ላይ ተሰቅሎ የሞተው አቤሴሎምስ ጌታውን አሳልፎ ሠጥቶ ተሰቅሎ የሞተው የይሁዳ ምሳሌ አይደለምን? ‹የታመንሁበት የሰላሜ ሰው እንጀራዬን የበላ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ› ተብሎ የተነገረው ስለ ይሁዳ አይደለምን? ብሉይ ኪዳን እንኳን አምላክን ስለወለደችው ቅድስት ድንግል ቀርቶ አምላኩን ስለሸጠው ይሁዳም ትንቢት ተናግሯል፡፡

አሁን ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ! ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ብሎ ዳዊት ስለ ቤተ መቅደስ መሠራትና ታቦቱም ወደ ቤተ መቅደሱ ስለመግባቱ የዘመረው መዝሙር ፣ ልጁ ሰሎሞንም መቅደሱ ተሠርቶ ሲያልቅ ደግሞ የዘመረው ይህ መዝሙር ከድንግል ማርያም ጋር ምን ያገናኘዋል? (2ዜና 6፡41) ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ከጥንት ጀምሮ ይህንን ጥቅስ ከድንግል ማርያም ጋር የሚጠቅሱት ዳዊት ስለ መቅደሱ መሠራትና ስለ ታቦቱ መግባት የተናገረ መሆኑ ጠፍቷቸው ነው? ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት› የሚለውን የዳዊት መዝሙር ከድንግል ማርያም ጋር አገናኝተን እንድናስብ ያነሣሣን ምንድር ነው? ወደሚለው እንምጣ፡፡

ዳዊት ስለ ታቦቱ የተናገረውን እኛ ስለ ድንግል ማርያም ሆኖ እንዲሰማን ያደረገው ራሱ ዳዊት ነው፡፡ ዳዊትን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እርሱ ስትመጣ ‹‹የእግዚአብሔር ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?›› ሲል አልሰማነውምን? (2ሳሙ. 6፡9) ይህን ንግግርስ ኤልሳቤጥ ‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?›› ብላ ለድንግል ማርያም አልደገመችውምን? (ሉቃ. 1፡43) ዳዊት የፈራው ታቦት ወደ እርሱ ሲቀርብ ከዙፋኑ ተነሥቶ በታቦቱ ፊት እየዘመረ ሚስቱ ሜልኮል እስክትንቀው አልዘለለምን? (2ሳሙ. 6፡16) በኤልሳቤጥ ማኅፀን የነበረው ዮሐንስስ የድንግልን ‹‹የሰላምታዋን ድምፅ በሰማ ጊዜ› እናቱ እስክታደንቀው ‹ፅንሱ በደስታ ዘለለ›› አልተባለምን? (ሉቃ. 1፡44) ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የድንግል ማርያምና የልጅዋ ክብር ላልገባቸው ሰዎች ‹‹እንደ ዮሐንስ በማኅፀን ውስጥ መዝለል ቢያቅታችሁ ምነው ነፍስ ካወቃችሁ በኋላ እንኳን ለእግዚአብሔር ማደሪያ እንደ ዳዊት በምስጋና ብትዘሉ?›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ እኛ ምን እናድርግ የእግዚአብሔር ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች እንደተባለ ‹‹ማርያምም በዘካርያስ ቤት ሦስት ወር ያህል ቆየች›› ተብሎ ተጽፎ አነበብን፡፡ (2ሳሙ. 6፡11 ፤ ሉቃ. 1፡56) ታዲያ የድንግል ማርያም ታሪክ ከእግዚአብሔር ማደሪያ ከታቦቱ ታሪክ ጋር አንድ ሆኖ ስናገኘው ዳዊት ስለ ታቦት የተናገረውን ስለ ድንግል ማርያም እንደምን አንጠቅስ? የነገረ ማርያምን ታሪክ እንጥቀስ ካልንማ ታቦቱ በወርቅ እንደተለበጠ በንጽሕና ያጌጠችውን ፣ ታቦቱ በመቅደስ እንደኖረ በመቅደስ ያደገችውን ፣ ታቦቱን በትሩ አብባ የተገኘች አሮን እንደ ጠበቃት በትሩ ያበበች ዮሴፍ የጠበቃትን፣ ታቦቱን የነካ ዖዛ እንደተቀሠፈ (2ሳሙ. 6፡7) የድንግልን ሥጋ ነክቶ የተቀሠፈውን ታውፋንያ ታሪክ እንጠቅስ ነበር፡፡

‹የመቅደስህ ታቦት› ማለት መቅደስ የተባለው የሰውነትህ ማደሪያ እናት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ሰውነቱን ‹ይህን መቅደስ አፍርሱት› አላለምን? ‹በጉ መቅደስዋ ነው› ተብሎ አልተጻፈምን? ስለዚህ ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› ማለት ጳውሎስ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት እንትጋ እንዳለው ‹‹ጌታ ሆይ ‹ዕረፍትህ› ወደተባለ ወደ ሰማያት አንተ ብቻ ተነሥተህ አትቅር የመቅደስ ሰውነትህ ማደሪያ እናትህንም ይዘህ ተነሥ›› ማለት ነው፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤ ብዙዎችን ማከራከሩ እንዴት ያሳዝናል? ክርስቶስ ‹ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ› ብሏል፡፡ እውነት ትንሣኤን ለወለደች እናት መነሣትዋ ትልቅ ነገር ነው? የሕይወት እናት ሕያው ሆነች ቢባል ያስቆጣልን? ሞትን የሞተው በልጅዋ አይደለምን? የሕይወትን እናት ሞት ይዞ አስቀራት ማለት ደስታ የሚሠጠው ለሞት አበጋዞች ነው፡፡ ‹‹አምላክ ያደረባት የምትናገር ታቦት ፈርሳ ቀርታለች ማለት ፣ ታቦተ ጽዮን ድንግል በሞት ፍልስጤም ተማርካ ቀርታለች›› ማለት የሚያስደስተው በማኅፀንዋ ፍሬ የተፈረካከሰው ዲያቢሎስ ነው፡፡ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን የሚደንቀን መሞትዋ እንጂ መነሣትዋ አይደለም፡፡

ቅዱስ ያሬድ ‹‹የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል›› እንዳለው ሕይወትን ያስገኘች ድንግል ፣ አምላክን የታቀፉ ክንዶች ፣ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆኑ ጉልበቶች በሞት መሸነፋቸው ያስደንቀናል፡፡ መነሣትዋ ግን የምንጠብቀው ነው፡፡ አልዓዛርን ‹አልዓዛር አልዓዛር› ብሎ ያስነሣ ጌታ ፣ በዕለተ ዓርብ በሞቱ ብዙ ሙታንን ያስነሣ ጌታ እናቱን አስነሣ ሲባል የሚቆጡ እንዴት ያሉ ናቸው?

ሁለቱ ምስክሮች የተባሉ ሄኖክና ኤልያስ ወደ ምድር መጥተው አስተምረው ከተገደሉ ‹‹ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ… በሰማይም ፡- ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ ወጡ›› ይላል፡፡ (ራእ. 11፡4-12) ሄኖክና ኤልያስን ከምጽአቱ በፊት ዳግም ላይሞቱ ከሞት አስነሥቷቸው በጠላቶቻቸው ፊት ወደ ሰማይ የሚያሳርጋቸው አምላክ እናቱን በወዳጆችዋ ፊት አስነሥቶ አሳርጓታል ሲባል በቁጣ መቃወም ምን ይባላል?

እንደልጅዋ በራስዋ ዐረገች (Ascension) በማለትና ልጅዋ ወደ ራሱ ነጥቆ ወሰዳት (Assumption) በማለት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ከቻልን የእመቤታችን ማረግ ምኑ ያከራክራል? ዝናምን ከከለከለው ኤልያስ ንጹሑን ዝናም ያስገኘችው ድንግል አትበልጥምን ፣ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረገው ሄኖክስ ይልቅ ለእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችው እመ አምላክ አትበልጥምን?

እኛ ግን ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹‹በሞትዋ ምድር መራራ ኀዘን ስታዝን በሰማይ ደስታ ሆነ እንዳለ›› እመቤታችን ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገርም ሆነ ፣ በልጅዋ ሥልጣን ተነሥታ ስታርግ በሰማይ የሚኖረውን ደስታ በእምነት እናስተውላለን፡፡ ያ ደሃ አልዓዛር እንኳን ሲሞት መላእክት ነፍሱን ወደ አብርሃም አጅበው ወስደውት ነበር ፣ ኤልያስም ሲያርግ መላእክት በእሳት ሰረገላና በእሳት ፈረሶች ነጥቀውት ነበር፡፡ የአምላክን እናት ዕርገት ስናስብ ከዚህ በላይ ዝማሬ ይታየናል ፤ ቅዱስ ቴዎዶስዮስ እንደጻፈው ቅዱስ ያሬድም ‹በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ› እንዳለው አባትዋ ዳዊት ‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› እያለ እየዘመረ ወላዲተ አምላክ ወደዚያኛው ዓለም ተሸጋግራለች፡፡ ኤልያስ ወደ ሰማይ ሲነጠቅ መጎናጸፊያውን ለበረከት እንዲሆነው ለደቀ መዝሙሩ ኤልሳዕ እንደሠጠው እመቤታችንም በልጅዋ ሥልጣን ወደ ሰማይ ስታርግ መግነዝዋን (መታጠቂያዋን) ለቶማስ በመሥጠትዋ ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት አሁንም ድረስ ተከፋፍለው በታላቅ ፍቅር በረከትዋን ይቀበሉበታል፡፡

እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ስለ እመቤታችን መነሣት ስናስብ የምንጠይቀው ‹ተነሣች ወይስ አልተነሣችም ፤ ወደ ሰማይ ዐረገች ወይንስ ዐላረገችም› ሳይሆን ‹በሰማይ የተደረገላት አቀባበል ምን ይመስል ይሆን?› ብለን ነው፡፡ ደሃው አልዓዛር በሞተ ጊዜ መላእክት ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት ከተባለ የአምላክን እናት ምን ያህል አጅበዋት ይሆን? ወደ ሰማይ ማረግ ለእርስዋ ቁምነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰማይን በእጆቹ የሚይዘውን አምላክ በእጆችዋ የያዘች ሁለተኛ ሰማይ ናት፡፡ እርስዋ ወደ ሰማይ በማረግዋም ዕድለኛዋ እርስዋ ሳትሆን ሰማዩ ነው፡፡ ሰማይ ዙፋኑ ነው ፣ ምድርም የእግሩ መረገጫ ናት ድንግል ማርያም ግን እናቱ ናት፡፡ ከእናትና ከዙፋን እናት ትበልጣለች፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ሰማይ አልወለደውም ፣ አላሳደገውም ፣ አላጠባውም ድንግል ግን ይህንን ሁሉ አድርጋለች፡፡ ስለዚህ ወደ ሰማይ ማረግዋ ክብሩ ለሰማዩ እንጂ ለእርስዋ አይደለም፡፡

እመቤታችን ወደ ሰማይ ስታርግ በእርግጥ አቀባበሉ እንዴት ይሆን? እኛ የሰው ልጆች እናታችንን ማክበርም መጦርም የምንችለው በምድር እስካለችና እኛም እስካለን ድረስ ነው፡፡ ‹እናትና አባትህን አክብር› ያለን ፈጣሪ ግን እናቱን ማክበር የሚችለው በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ጭምር ነው፡፡ እናቱ ወደ እርሱ ስትመጣ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንዴት ተቀብሏት ይሆን?

ንጉሥ ሰሎሞን እናቱ ቤርሳቤህ ወደ ቤተ መንግሥቱ በመጣች ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ‹‹ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ ሳማትም ፤ በዙፋኑም ተቀመጠ ፤ ለእናቱም ወንበር አስመጣላት በቀኙም ተቀመጠች፡፡ እርስዋም ፡- አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች፡፡ ንጉሡም ፡- እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ለምኚ አላት›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (1ነገሥ. 2፡19-20) ከዳዊት ሆድ ፍሬ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ንጉሥ ሰሎሞን ይልቅ በዳዊትን ዙፋን ለዘለዓለሙ ይነግሣል የተባለለት ክርስቶስ ይበልጣል፡፡ ስለ ክርስቶስ ‹‹ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ›› ተብሎ ተጽፎአል፡፡ (ማቴ. 12፡42) ክርስቶስ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከሆነ የክርስቶስ እናትም ከሰሎሞን እናት ትበልጣለች፡፡ ሰሎሞን ለእናቱ ከሠጣት ክብርም በላይ ክርስቶስ ለእናቱ የሚሠጣት ክብር ይበልጣል፡፡ የሰሎሞን ቤተ መንግሥት በምድር ነው ፤ የክርስቶስ ቤተ መንግሥት ግን በሰማይ ነው፡፡ መድኃኔ ዓለም ወደ ሰማያዊው መንግሥቱ እናቱን በጠራት ጊዜ እንደምን ተቀብሏት ይሆን? እንደ ሰሎሞን እናት ወንበር አስመጣላት እንዳንል በሰማይ መቆም መቀመጥ የለም፡፡ ነገር ግን ‹‹የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች›› ተብሎ ድንግሊቱ ስለተሠጣት ክብር ተጽፎአል፡፡ ወርቅ መልበስዋ አነሳት የሚል ካለ ደግሞ ‹‹አሕዛብን በብረት በር የሚገዛቸውን ወንድ ልጅ የወለደችው›› ድንግል ‹‹ፀሐይን ተጎናጽፋ ፤ ጨረቃም ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ፣ ዐሥራ ሁለትም ከዋክብት አክሊል የሆኑላት አንዲት ሴት ነበረች›› ተብሎ ተጽፎላታል፡፡ (መዝ. 44፡9 ፣ ራእ. 12፡1)

ለእኛ ለኦርቶዶክሳዊያን ድንግል ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገር የነበራትን የክብር አቀባበል በሕሊናችን ከማሰብ በቀር ምን የሚያውከን ነገር የለም፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ድንግልን ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? እዚህ ‹ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ› ብሎ ሰላምታ ያቀረበላት ይህ መልአክ ጸጋን የተሞላችው ወደ እርሱ ስትመጣ ምን ብሎ ተቀብሏት ይሆን? ቅድስት ኤልሳቤጥስ አሁንም ‹ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?› ብላት ይሆን? መጥምቁስ ዳግም በሰማይ በደስታ ዘልሎ ይሆን? ነቢያቱ ድንግልን እንዴት ተቀበሏት? ኢሳይያስ ‹ትፀንሳለች› ያላትን ድንግል ሲያያት ምን ይል ይሆን? ሕዝቅኤልስ ‹የተዘጋችዋ ደጅ› ወደ እርሱ ስትመጣ ምን አለ? ጌዴዎን ጸምሩን ፣ ኤልሳዕ ማሰሮውን ፣ አሮን በትሩን ፣ ኖኅ መርከቡን ባየ ጊዜ ምን ብሎ ይሆን? ሙሴስ ያልተቃጠለችው ዛፍ ወደ እርሱ ስትመጣ ዳግም እንደ ሲና ተራራው ጊዜ ጫማውን አውልቆ ይሆን? አዳም የልጅ ልጁን ሲያይ ሔዋንስ ዳግሚት ሔዋንን ስታይ ምን ብላ ይሆን? ሁሉንም በሰማይ ለመረዳት ያብቃን!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

‹‹ነሐሴ 7›› በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀነሰች።ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱና የመጀመሪያው ነው።የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄም እና ሃና ይባላሉ። እነዚህ ቅዱሳን...
13/08/2025

‹‹ነሐሴ 7›› በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀነሰች።

ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱና የመጀመሪያው ነው።

የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄም እና ሃና ይባላሉ። እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑዋሉ። ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፦

ኢያቄም፦"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ።

ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋየምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች።

እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች።

እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተእግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን ፤ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።

ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ፤

ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው።

እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡

ነሐሴ ሰባት በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ ዕለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች።

ምልጃዋ በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን🙏

"ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች"             መዝ. 44 (45)፥9
10/08/2025

"ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች"
መዝ. 44 (45)፥9

" የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?"          ሉቃ. ፩፥፵፫ /1፥43/
10/08/2025

" የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?"
ሉቃ. ፩፥፵፫ /1፥43/

07/08/2025

እንኳን ለፆም ፍልሰታ አደረሳችሁ አደረሰን👏👏👏
የእመቤታችን ድንግል ማርያም ምልጃ ፣ ረድኤትና በረከት አይለየን ! እግዚአብሔር በምህረቱ ይመልከተን!

የኦርቶዶክስን ንዋያተ ቅድሳት በየጭፈራ መድረኩ የማርከስ እንቅስቃሴ ተራ ብሽሽቅ ይምሰል እንጂ ተልእኮ እና ድጋፍ ያለው ነውብዙ ነገሮችን እና ጭካኔዎችን የተለማመድነው እንዲህ ነው። ሰዉ ጭራ...
06/08/2025

የኦርቶዶክስን ንዋያተ ቅድሳት በየጭፈራ መድረኩ የማርከስ እንቅስቃሴ ተራ ብሽሽቅ ይምሰል እንጂ ተልእኮ እና ድጋፍ ያለው ነው

ብዙ ነገሮችን እና ጭካኔዎችን የተለማመድነው እንዲህ ነው።

ሰዉ ጭራሽ በጨዋታ እያዋዛ፣ ለmeme አውሎት ቀልድ እየፈጠረበት የሚቀባበለው ነውር፣ ነገ በብዛት ሲታይ ማስደንገጡ ይቀንሳል።

ጧት ማታ በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትን በማጣጣል ሥራ የተጠመዱ የአገርን መሠረቶች "ኋላ ቀር" በሚል ታርጋ ለማናጋት የሚጥሩ "ተራማጆች" ሳይቀር አሁን "እኛም ስንሰማ ደንግጠናል" ብለዋል።

ጭራሽ የእሱ "እምነታችሁን ተዉ" ማለትና ስንት አገር እንዳጠና ሰው ሕዝብን በጅምላ ማንኳሰስ፣ ለባህል መበረዝ እና ለነውር መብዛት አስተዋጽኦ የሌለው ይመስል፣ "ቅድስት አገር የምትሏት" ሁሉ ብሎ ለማሸማቀቅ የሚሞክር አለ።

ኋላ ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን እንጂ፣ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እስካለች የምዕራቡን ዓለም አጀንዳ በይፋ መዘርገፍ ከባድ ነው፤ ብለው በገንዘብ ድጋፍ ጭምር ከጀንደር እስከ ሀይማኖት አጀንዳ ይዘው የሚሰሩ እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

እንኳን ሌላው በማርያምና ተዋሕዶ ስም ወደ ድሮ ሄደናል የሚሉት harmless ቀውስ መስለው የሚታዩት እነ እህተ ማርያም ሳይቀር እምነት የማዳከምና አገርን በመጠበቅ ስም መሰረት የመሸርሸር ተልእኮ አያጡም። የኦርቶዶክስን ንዋያተ ቅድሳት በየጭፈራ መድረኩ የማርከስ እንቅስቃሴ ተራ ብሽሽቅ ይምሰል እንጂ፣ ተልእኮ እና ድጋፍ ያለው ነው።

በውስጡ የተደበቀውን የጥቃት ፍላጎትም ይህን ታክኮ የሚተነፍስ አለ። በነውር ብዙ ዓመት ወደፊት፣ በጨዋነት ብዙ ዓመት ወደ ኋላ ነው የተወረወርነው ብቻ። የሴቶችን ጉዳይ መነገጃ ባደረጉ ሰዎች ነውር ነገ ወላጅ ሴት ልጁን ከጥቃት ለማስጣል ቢሞክር እንኳን፣ መሸማቀቅ እንዲያተርፍ ያደርጋል። ነገ ያስፈራኛል።

ሁሌ እጠይቃለሁ። ራዲካል ፌሚኒስት ነን ባይ ሴቶች ላይ በዚህ ልክ ሴቶች ላይ መጨከን ለምን ይፈልጋሉ?

Via Yohannes Molla

Address

Gond

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gashaw Getnet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gashaw Getnet:

Share