Gashaw Getnet

Gashaw Getnet አንቺ የወላዲተ አምላክ የአሥራት አገር
ኢትዮጵያ ሆይ ተነሺ!!!

12/11/2025

☦️ የነበረ ያለና የሚኖር

#እግዚአብሔር #ማርያም #ኦርቶዶክስ
IN THE NAME OF THE FATHER AND THE SON AND THE HOLY SPIRIT ONE GOD. AMEN.

12/11/2025

እግዚአብሔር አይተወንም!

12/11/2025

ባዕታ ማርያም እናቴ❤❤❤

12/11/2025

መድሃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ

🚸🚸🚸

07/11/2025

ክርስትና ፍሬዋ መንግስት ሰማዕት ነው!

ይኼንን ጽሑፍ ቁጭ ብለህ እያነበብህ ያለኸው በዚህ ሰዓት ምሥራቅ አርሲ ገጠር ውስጥ ስላልተገኘህ ብቻ ነው:: በዚህች ቅጽበት በሥጋት ውስጥ ሆነው "ከአሁን አሁን ምን ይመጣብን ይሆን?" እያሉ...
04/11/2025

ይኼንን ጽሑፍ ቁጭ ብለህ እያነበብህ ያለኸው በዚህ ሰዓት ምሥራቅ አርሲ ገጠር ውስጥ ስላልተገኘህ ብቻ ነው:: በዚህች ቅጽበት በሥጋት ውስጥ ሆነው "ከአሁን አሁን ምን ይመጣብን ይሆን?" እያሉ ያሉ የኦሮሚያ ምእመናን ቁጥራቸው ብዙ ነው:: ከቀናት በፊት የተገደሉትን ተናግረን ሳናበቃ አሁን ደግሞ ሌላ ቦታ አምስት እንደተገደሉ እየሰማን ነው::

ሰሞኑን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ሔሮድስ ስላሳደዳት እመቤታችን "ሰቆቃወ ድንግል" እያልን እያዘንን ነው:: ከሰይፍ ልጅዋን ማስጣል ያልቻለች የአርሲዋን እናትስ እንዴት ዝም እንበላት? ይህንን የማያቆም ሞት ዜና ሰምተን ወደ ጉሮሮአችን የሚወርድ ምግብና መጠጥ የምንተኛውም እንቅልፍ የለም:: የእነርሱ ሞት የእኛ ሞት ነው:: የእነርሱ መቁሰል የእኛ ቁስል ነው:: የቦታ ለውጥ እንጂ በእነርሱ የደረሰው በእኛም ሊደርስ ይችላል::

ቤተ ክርስቲያን ምሕላ እንድታውጅ ፣ ለተሠዉት ተገቢውን ክብር እና ጸሎተ ፍትሐት እንድታደርግ እንጠብቃለን:: ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ቦታ የንጹሐን ደም ዳግመኛ እንዳይፈስስ እንደ ራሔል ዕንባዋን የምትረጭበት ጊዜ አሁን ነው::

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ትኩረት ያልሠጠውን ችግር ሌላ አካል ሊጨነቅበት አይችልም:: ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደራዊ መዋቅርዋ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በሙሉ ትኩረት የምትሠራበት ጊዜም አሁን ነው:: ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ዓይነት ጊዜ የሚያሳየው ምላሽ ከሌለ ሌላ ቀን ቢጣራ የማይሰማውን ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስቲያን በራሱ ላይ ይፈጥራል:: ሐዋርያዊትዋ ቤተ ክርስቲያንም በክህነት ከማትመራ የመሆን አደጋ ይገጥማታል::

ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንም ይህንን ጊዜ ለመካሰስ ፣ አባቶችን ለመሳደብ ፣ አንዱ ሌላውን ለማስጠቆርና ለመናቆር ሳይሆን ለጸሎት ለምሕላና ለሰብአዊ ሥራና መሬት ላይ ቢወርዱ ችግሮችን የሚፈቱ ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ምክንያት ብናደርገው የተሻለ ነገር ማምጣት እንችላለን::

የሌላ እምነት ተከታዮች ሆነው ይህ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ጥቃት ብለው ጉዳዩን በተቋምም በግልም ያወገዙ ሰዎችን እናከብራለን:: "ይበላችሁ" ብለው የተሳለቁትን እና በክፉ ቀን ክፋታቸውን ላሳዩን ደግሞ እውነተኛ ማንነታቸውን ስላሳዩን እያመሰገንን "አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ “እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ፡” ያሉአትን" ብለን ለሰማያዊው ዳኛ ሠጥተናቸዋል:: መዝ. 137:7




‹‹ማርያም›› ማለት "መርህ ለመንግሥተ ሰማያት" መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው።ቅድስት ድንግል ማርያም አባቷ ኢያቄም እናቷ ደግሞ ሃና ይባላሉ::እመቤታችን ማርያም ለእናት ለአ...
30/10/2025

‹‹ማርያም›› ማለት "መርህ ለመንግሥተ ሰማያት" መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታስገባ ማለት ነው።

ቅድስት ድንግል ማርያም አባቷ ኢያቄም እናቷ ደግሞ ሃና ይባላሉ::

እመቤታችን ማርያም ለእናት ለአባቷ አንዲት ስትሆን የተወለደቸው በጸሎት በመሆኑና የስለት ልጅ በመሆኗ እናትና አባቷ ለእግዚአብሔር በተሳሉት መሰረት ፫ ዓመት ሲሞላት ወደ ቤተመቅደስ ወሰደው ለካህኑ ለዘካርያስ አስረከቧት::

በዚያን ጊዜ የነበረው ሊቀ ካህናት ዘካርያስ ይባላል፤ እርሱም ስለ ምግቧ ነገር ሊያስወስን መጥቅዕ (ደወል) ደውሎ ሕዝቡን ሰብስቦ እየተወያዩ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል የሰማይ ኅብስትና የሰማይ ጽዋ ይዞ ከሰማይ ወርዶና ረብቦ ታየ፡፡

ሕጻን ማርያምን ከወላጆቿ ተቀብለው ወደ ቤተ መቅደስ አግብተዋት በዚያ ፲፪ ዓመት ኖራለች፡፡ይህም ሲደመር ጠቅላላ ፲፭ ዓመት ሆናት ማለት ነው::

በዚህ ስዓት አይሁድ ከቤተመቅደስ ትውጣልን ብለው አመለከቱ ፤ ለጻድቁ ለቅዱስ ዮሴፍም እንዲጠብቃት ታጨች ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አበሰራት::በ ፲፭ አመቷ እግዚአብሔር ወልድን ፀነሰች::

ይህ አምላክም ወይም እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወለደ::በሌላ አገላለጽ አምላክ ሰው ሆነ::በዚህም ምክንያት ቅድስት ድንግል ማርያምን የጌታ እናት ወይም የእግዚአብሔር እናት(ወላዲተ አምላክ) ትባላለች::

ቅድስት ድንግል ማርያም በ 64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ እንደ ልጇ በሦስተኛው ቀን አርጋለች።

የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ አይለየን🙏

የብፁዕ አቡነ ሔኖክ መልዕክት ***“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ...
29/10/2025

የብፁዕ አቡነ ሔኖክ መልዕክት
***
“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮

በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዝተን እየተለማመድነው የመጣነው የኦርቶዶክሳውያን ሞት ሊበቃ እና የሰው ልጆች ሁሉ የመኖር ሰብዓዊ መብት ሊረጋገጥ ይገባል።

በአካባቢው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በተደጋጋሚ በአማኙ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ሊያስቆሙ እና መፍትሔ ሊያበጁለት ይገባል።

ለወደፊቱም ቢሆን እንደ ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቁብንን በርካታ ሥራዎች አለመሥራታችን ትውልዱን ዋጋ እያስከፈለው እንዳይኖር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መሥራት የሚገባን አያሌ ተግባራት መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም።

በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን ያድልልን፤ ለቤተሰቦቻቸው አጽናኝ ቅዱስ መንፈስን ይላክላቸው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !

29/10/2025

የደስታ መላእክት ነው ቅዱስ ገብርኤል❤👏

‎«ገብርኤል» ማለት “እግዚእ ወገብር” የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።🎤🙏😍‎‎ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው‎‎ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት ...
28/10/2025

‎«ገብርኤል» ማለት “እግዚእ ወገብር” የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።🎤🙏😍

‎ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው

‎ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም

‎የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ ፤ የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ

‎ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው

‎ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው

‎ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ

‎ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው

‎ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው

‎ይህንን ሁሉ ያደረገ ቅዱስ ገብርኤል ነው።

‎የመልአኩ ጥበቃ እና ረድኤት አይለየን🙏🙏🙏

Address

Gond

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gashaw Getnet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gashaw Getnet:

Share