Gondar media ጎንደር ሚዲያ

Gondar media ጎንደር ሚዲያ ይህ ፔጅ ስለ ጎንደር ትውፊት ባህል ጥበብ እና ማንነት ይገለፅ?

22/01/2025

ጥምቀትን በጎንደር

11/09/2024
07/08/2023
"ጎንደር" የትንቢቷ ከተማበታዴ የማመይ ልጅ ለ251 ዓመት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የነገስታት መቀመጫ ሁና በኩራት መርታለች 28 ንጉሶች ነግሰውባታል 18ቱ ሀያል ነበሩ 10ሩ በጣም ሀያልና አስ...
23/03/2023

"ጎንደር" የትንቢቷ ከተማ
በታዴ የማመይ ልጅ

ለ251 ዓመት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የነገስታት መቀመጫ ሁና በኩራት መርታለች 28 ንጉሶች ነግሰውባታል 18ቱ ሀያል ነበሩ 10ሩ በጣም ሀያልና አስፈሪና አይደፈሬ ነበሩ ንጉሶቻችን እስከ ሱዳን ኑቢያ በጀብድ ገዝተዋል ነጮቹ ያን የስልጣኔ የጥበብ አሻራ ዘመን The Glorious Gondarine Period ,The Luxury Life Of Gondarians ይሉታል።
ጎንደር የአፍሪካ መናገሻ( The Camelot Of Africa) African Naples, African Paris
እያሉ ያንቆለጳጵሷት የነበረች የከተሞች እናት ነች
የጎንደር ስያሜ የተገኘው "ጉንደ ሀገር" ከሚለው የግዕዝ ቃል ሲሆን
ትርጉሙም
የሀገር መሰረት
የሀገር ግንድ
የሀገር ቁንጮ
የሀገር ቀንድ
የሀገር ምሰሶ
የሀገር ዳራ
የሀገር አውራ ታላቅ ምድር ማለት ነው።

ሌላኛው ደግሞ ጎን እደር ከሚል የወይኔ እና ሰይኔ እርቅ ጋር ተያይዞ በወንድምህ ጎን እደር ከሚል የተወሰደ ነው ይቺ ታሪካዊት የትንቢት ከተማ የተቆረቆረችው በ1624 በአለም ሰገድ ፋሲል ( አለም የሰገደለት ማለት ነው ) ሲሆን ንጉሶች ጎ ትነግስ መናገሻህ ጎ የሚል ህልም ያዩ ነበር በጎ የሚጀምር ቦታ ላይ ከነገሱ ንግስናቸው ይፀናልና በዚህ ትንቢት ምክንያት ገናናው ፋሲል ፈልጎ አፈላልጎ በሚያድነው ጎሽ ምክንያት አገኛት እና መቀመጫው አደረጋት በጥቁር አፍሪካ ምድር የአፍሪካ መናገሻይቱ ውብ ምድር የሚል ስያሜ ተሰጥቷታል ።
ጎንደር የኢትዮጵያ ዋና ከተማ መሆኗ ለኢትዮጵያ ይዞት የመጣው ጥበብና ስልጣኔ ገናናነት ጀግንነት የግንባታ ቴክኖሎጅ ብቻ አልነበረም ይልቁንስ ነገስታት ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ በመዞር ይገዙ ነበር እንጅ ከተማ አይመሰርቱም ነበር ጎንደር ከተመሰረተች በኋላ ግን ይሄ የመዘዋወር ባህል ቀርቶ በቋሚ ከተማ መምራት ተጀመረ።

የከተሞች እናት ጎንደር ዋናዋ የንግድ ማዕከል በመሆንም አገልግላለች ወደ ቀይ ባህርና ሱዳን የሚደረገው ንግድ ማዕከል ሁና ቆይታለች ።

ጎንደር እኮ …
የሰርፀ ድንግል ፣ የሱስንዮስ ፣ የፋሲል፣ የአዕላፍ ሰገድ፣ የአድያም ሰገድ የእያሱ…የበካፋ ፣ የምንትዋብ ፣ የተዋበች… የቴዎድሮስ እና የገብርዬ… ብቻ ሀገር አይደለችም። የጦረኛው አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ …የግራኝ አህመድም ሀገር ነች ። ከአስር አመት በላይ ጠላቶቼ የሚላቸውን ነገስታት እያሳደደ ህልሙን ለማሳካት የተንከራተተባት …በኋላም በጀግንነት እየተፋለመ የወደቀባት ምድር ናት #ጎንደር!!
ማን ያውቃል? …ግራኝ አህመድ አሸንፎ ቢሆን ከፋሲል ቀድሞ መቀመጫው ያደርጋት ይሆን ነበር እኮ… ግራኝ እና ገላውዲዮስ… ሁለቱ ተፋላሚዎች የየራሳቸውን የተለያዩ ርዕዮተ ዓለሞች ተሸክመው መንግስታቸውን ለማፅናት ሲሉ ጎንደር ላይ ተፋልመዋል። ሽምብራ ኩሬ …ሸዋ ላይ ፣ የገላውድዮስን አባት የአፄ ልብነ ድንግልን ጦር ያሸነፈው ጦረኛው ኻሊፌቱ ግራኝ አህመድ… ጎንደር በጌምድር ፣ በለሳ ውስጥ ልዩ ስሟ "ወይና ደጋ" ከተባለች ቦታ ላይ ሲሰዋ የጎንደርን አፈር መቅመሱ እርግጥ ነው። ከአፋር እና ከሱማሌ በርሃዎች የፈለቀው በርኸኛው ግራኝ… በራስ ደጀን እና በጉና ተራሮች በተከበበችው …ከባለ ጣና ሃይቋ ምድር፣ "ከወይና ደጋዋ" ጎንደር ላይ አሸለቧልና አፋራዊያኑ ስለጎንደር ያገባቸዋል።
አፋር ተወልዶ አፋር ያደገው… ግራኝ ለህልሙ የተፋለመባትን ጎንደርን… አፋሩ እና ሱማሌው ሳይቀር "ሙቼ ነው ምወዳት" ቢል አልተሳሳተም። ጎንደር የግራኝም ሀገር ናት። የበረኸኞቹ፣ የሙስሊሞቹ ኢትዮጵያዊያን ደም እና የደገኞቹ የክርስቲያኖቹ ኢትዮጵያዊያን ደም የተጋመደባትን ምድር… ናት
#ክብርና ምስጋና

 #ጃፓንቤትህ አልበላሽ ያለህ "Sony" ቴሌቪዥን የነሱ ነው፣ ያሳደገህ ብረቱ "Hitachi" ፍሪጅ የነሱ እጅ ያረፈበት ነው፣ ሃገራችንን ብቻ ሳይሆን ዓለማችንን ያጥለቀለቀው "Toyota" ...
02/12/2022

#ጃፓን

ቤትህ አልበላሽ ያለህ "Sony" ቴሌቪዥን የነሱ ነው፣ ያሳደገህ ብረቱ "Hitachi" ፍሪጅ የነሱ እጅ ያረፈበት ነው፣ ሃገራችንን ብቻ ሳይሆን ዓለማችንን ያጥለቀለቀው "Toyota" መኪና የነሱ ጥበብ ውጤት ነው፣ "Nikon" እና "Canon" ካሜራዎች የነሱ አሻራዎች ናቸው፣ እንደዛ በፍቅር የምትወደው "Toshiba" ላፕቶፕህ የነሱ ነው፣ "Mazda", "Lexus", "Mitsubishi", "Honda", "Nissan", "Isuzu", "Suzuki" ምናምን የምትላቸው መኪናዎች የተፈበረኩት በነሱ ነው። እጃቸው የነካው ምርት ሁሉ ብሩክ እና ብረት ነው።

ከሁሉም በላይ የሚደንቀኝ የጃፓናዊያን የስራ ባህል ነው። የእረፍት ትርጉሙ አይገባቸውም! የዓለማችን ረጅም ሰዓታቸውን በስራ ላይ የሚያሳልፉ ዜጎች ጃፓናዊያን ናቸው። በስራ ብዛት የሰው ልጅ የሚሞተው ጃፓን ውስጥ ብቻ ነው! ሞቱን "Karoshi" ብለው ይጠሩታል። በዓመት ካላቸው የ 20 ቀን እረፍት ውስጥ 10 የሚሆነውን እንኳን በአግባቡ አይወስዱም። 63% የሚሆኑ ጃፓናዊያን በእረፍት ሰዓታቸው በሚከፈላቸው ገንዘብ ደስተኛ አይደሉም። ጌታዬ! መንግስት "....የአመት እረፍታችሁን እባካችሁ ውሰዱ! በስራ ብዛት እና ጭንቀት እየሞታችሁ ነው! እስቲ ትንሽ ዘና በሉ!..."ብሎ ሲለምን የምትሰማው የጃፓን መንግስትን ብቻ ነው።

ከለሊቱ 9 ሰዓት ላይ የጃፓን መንገዶችን ብትመለከት ሽክ ብሎ ሱፉን ለብሶ እና "briefcase" ይዞ ወደ ስራ የሚሄድ ብዙ ሰው ታያለህ። አብዛኛው ጃፓናዊ "ለምን ትሰራለህ?" ተብሎ ሲጠየቅ "ሃገሬን ስለምወድ እና ብቁ ዜጋ ሆኜ መገኘት ስላለብኝ!" ብሎ ይመልስልሃል። ያለ እረፍት ከመስራታቸው ብዛት የጃፓን መስሪያ ቤቶች ውስጥ ጠረጴዛቸውን ተደግፈው የሚያንቀላፉ ሰዎችን ማየት የተለመደ ነው። የታታሪነት፣ የብርቱነት እና ሃገር ወዳድነት መገለጫ ነው። ከአጠቃላይ ህዝብ ቁጥሩ ውስጥ 3% የሚሆነው ብቻ ስራ አጥ ሲሆን ሰዎች ስራ ፈትተው በመቀመጣቸው ምክንያት በጭንቀት እራሳቸውን የሚያጠፉባት ሃገር ናት።

ተማሪዎቿ!

ከዓለማችን ብቁ ተማሪዎች ተርታ ይሰለፋሉ። 100% የሚሆነው የሃገሪቷ ወጣቷ በሚገባ ፊደል የቆጠረ እና ቀጥቅጦ የተማረ ነው። ህፃናት ሃገራቸውን እንዲወዱ፣ ቤተሰባቸውን እና ማህበረሰባቸውን እንዲያከብሩ ተድርገው ያድጋሉ! የጃፓን ትምህርት ቤቶች ውስጥ የፅዳት ሰራተኛ አይቀጠርም! "ለምን?" ካልከኝ ከትምህርት በኃላ ሁሉም መምህራን እና ተማሪዎች ለ 15 ደቂቃ ልብሳቸውን ቀይረው ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙ ሁሉንም ክፍሎች(መፀዳጃ ቤትን ጨምሮ) እኩል ያፀዳሉ! የጃፓን ተማሪዎች በሂሳብ፣ ፊዚክስ እና ቋንቋ መጎበዝ ግዴታቸው ነው። ተማሪዎች የፍቅር ግንኙነት መመስረት አይችሉም! እሱ ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቤት ውስጥ መሳሳምም ሆነ መተቃቀፍ አይቻልም፣ ያስቀጣል፣ አለፍ ካለም ያስባርራል!

ገራሚ ነገር አንድ!

የዓለማችን ትልቁ አማካይ የመኖርያ እድሜ ያለው ጃፓን ነው። አንድ ጃፓናዊ በአማካይ 83 ዓመት ይኖራል። ውፍረት እንደ ሃጥያት የሚቆጠርባት ጃፓን ውስጥ የተዝረጠረጠው ህዝብ ከ 4% አይበልጥም። ጌታዬ! ይህ አሃዝ አሜሪካ ውስጥ 40% ነው! የመኖራችን ሚስጥር ስፖርት፣ አሳ እና ቅጠላ ቅጠል ነው ይላሉ! ብታምነኝም ባታምነኝም ጃፓን ውስጥ 50 ሺህ እድሜያቸው ከ 100 በላይ የሆኑ ሰዎች ይኖራሉ!

ገራሚ ነገር ሁለት!

የጃፓን ዋና ከተማ የሆነችው "ቶክዮ" ውስጥ ብቻ 38 ሚልዮን ህዝብ ይኖራል! አባዬ! አዲስ አበባ ከ 10 ሚልዮን በታች ሆና ነው እንግዲህ ልንፈነዳ የደረስነው!😀

የአማራን ሕዝብ የማገት ፣ የማዋረድ እና የመጎንተል “ፖለቲካ” ከሽብርተኞቹ ትሕነግ/ወያኔ እና ኦነግ/ሸኔ አጋርነት ተለይቶ የሚታይ አይደለም ሲል አብን አሳሰበ።ባሕር ዳር፡ መስከረም 23/20...
03/10/2022

የአማራን ሕዝብ የማገት ፣ የማዋረድ እና የመጎንተል “ፖለቲካ” ከሽብርተኞቹ ትሕነግ/ወያኔ እና ኦነግ/ሸኔ አጋርነት ተለይቶ የሚታይ አይደለም ሲል አብን አሳሰበ።

ባሕር ዳር፡ መስከረም 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

የአብን ሙሉ መግለጫ ቀጥሎ አቀርቧል፦

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፣

የአማራን ሕዝብ የማገት ፣ የማዋረድ እና የመጎንተል “ፖለቲካ” ከሽብርተኞቹ ትሕነግ/ወያኔ እና ኦነግ/ሸኔ አጋርነት ተለይቶ የሚታይ አይደለም!

በኦሮሚያ ክልል የወለጋ ዞኖች ያለማቋረጥ እየተካሄደ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚመለከታቸው የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለስልጣናት ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም!

ከአማራ ክልል በሚነሱ እና የአማራ ተወላጅ በሆኑ ተጓዥ መንገደኞች ላይ የማገት ፣ የማዋረድ እና ከጉዞ የማስተጓጎል ወንጀል በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ቀጥተኛ ትዕዛዝ በተከታታይ እና እያሰለሰ እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህ የአማራን ሕዝብ ኢላማ ያደረገ የማገት ፣ የማዋረድ እና የመጎንተል ነውረኛ “ፖለቲካ” በጦር ግንባር ሽንፈት እየተከናነቡ ላሉት ለሽርብተኞቹ ትሕነግ/ወያኔ እና ኦነግ/ሸኔን ከሽንፈት ለመታደግ እየተሰጠ ያለ ስልታዊ ድጋፍ መሆኑን ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ያምናል፡፡ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ተጓዥ መንገደኞችን የማገት ፣ የማጉላላት እና አንዳንድ ጊዜም የመደብደብ ወንጀል የሚፈጽሙት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተብለው የተመደቡና በየቦታው ኬላ የጣሉ የጸጥታ አካላት ናቸው፡፡ ጉዳዩ በተደጋጋሚ ቅሬታ የቀረበበት ፣ በሚዲያዎች በሰፊው የተዘገበ እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣናት በኩል ማስተካከያ ይደረግበታል እየተባለ የለበጣ ምላሽ ሲሰጥበት የቆየ ነው፡፡ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው የማገት ፣ የማዋረድ እና ተጓዥ መንገደኞችን ከጉዟቸው የማስተጓጎል ጥቃት ከሽብርተኞቹ ትሕነግ/ወያኔ እና ኦነግ/ሸኔ አጋርነት ተለይቶ የሚታይ አይደለም!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣናት የፌደራል መንግሥት በሚያስተዳድራቸው አውራ ጎዳናዎች ላይ እያሰለሱ እየፈጸሙ ያሉትን ሰፊ የመብት ረገጣ የፌደራል መንግሥቱ ለማስቆምና ለማረም አለመንቀሳቀሱ የጥፋቱ ተባባሪ ነው ብለን እንድንወስደው የሚያደርግ ነው፡፡ ከፌደራል መንግሥቱ መቀመጫ አፍንጫ ሥር ይህ ሁሉ ግፍ እና ነውር ሲፈጸም በዝምታ መመልከት ከፍ ያለ ሀገራዊ ውድቀት ውስጥ ስለመሆናችን ዋና ማሳያ ተድርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት የአማራ ሕዝብ መብትና ክብር እንዲጠበቅ መስራት የሚጠበቅበት ቢሆንም የዳር ተመልካች ሆኖ ታይቷል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በክልሉ ውስጥ የሚኖረውን የአማራ ሕዝብ ደኅንነት ለአደጋ አጋልጠው በሽህዎች እየተጨፈጨፉ እና እየተፈናቀሉ ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል ለጨፍጫፊዎች ሽፋን መስጠታቸውን እንደቀጠሉ ይገኛሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ ቁመንለታል የሚሉት የኦሮሞ ሕዝብ ሳይቀር በሽብር ቡድኑ ግድያና መሳደድ ሲደርስበት እያዩ ጥቃቱን ለማስቆም ሲንቀሳቀሱ አይታይም:: የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግስቱ ባለስልጣናትም በዝምታ ለጥቃቱ ተባባሪ ሁነዋል፡፡ ሁለቱም ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም፡፡ በቅርቡ እንኳ በምእራብ ኦሮሚያ (ወለጋ) በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ሲጨፈጨፉ የክልሉ እና የፌዴራል ባስልጣናት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው አልፈዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል እና የፌዴራል መንግስቱ ባለስልጣናት የወለጋ ዞኖች ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በጭፍጨፋ ፣ ከአማራ ክልል የሚነሱ የአማራ

በቀደም እንዳልኋችሁ አማራን የሚከፋፍል ሴራ የሚሰሩ፣ ፀረ ጎጃም አቀንቃኞች በቁጥር ከ 50 በታች ናቸው።  "ህዝብ ጀግናውን ያውቃል!!!"  ለዚህም የፈሲል ከነማ ደጋፊዎች ምስክሮች ናቸው። ...
03/10/2022

በቀደም እንዳልኋችሁ አማራን የሚከፋፍል ሴራ የሚሰሩ፣ ፀረ ጎጃም አቀንቃኞች በቁጥር ከ 50 በታች ናቸው። "ህዝብ ጀግናውን ያውቃል!!!" ለዚህም የፈሲል ከነማ ደጋፊዎች ምስክሮች ናቸው።
የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ዛሬ በባህር ዳር ስታዲዬም ላይ ደገሙት💪

በለው ዘመነ ካሴ
በለው ዘመነ ካሴ
ያአሳምነው ልጅ ያውም ጎንደሬ እያሉ ነው!
በጥቂት ሆድ አደሮች ከአማራነታችን አንወርድም ብለዋል ።
እኔም ለፋሲል ከነማ ደጋፊዎች እንዲህ ልበላቸው!

ሀቀኛ ናችሁ ያውም ጎንደሬ
የምትለያዩ ብስል ከጥሬ
ጎንደሬ ናችሁ ያውም አጅሬ
እናመሰግናለን
እንዳላማው ክንዴ!!!

12/07/2022

ታሪክ በዛሬው ዕለት!

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ vs ሻለቃ ደጀኔ ማሩ

የሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ሌሊቱ ነግቷል፡፡ ኮሎኔል ወደ ቅርብ ሰዎቹ የድረሱልኝ ስልክ መደወል ጀምሯል፡፡ኮሎኔል እንዳጫወተኝ፣ ጠዋት ከ3-4 ሰዓት ሲሆን ሰሮቃ ለሚገኘው ጓደኛው ለመቶ አለቃ ደጀኔ ማሩ፣ “ታፍኛለሁና ከቻልክ ድረስልኝ” ይለዋል፡፡ ደጀኔም ወሬ ሳያበዛ፣ “ስንት ጥይት አለህ?” ሲል ኮሎኔልን ይጠይቀዋል፡፡ ኮሎኔልም፣ “30 ጥይት አለኝ” ይለዋል፡፡

“በል ለመድረስ እሞክራለሁ፤ ከመድረሴ በፊት አንድ የሆነ ነገር ከተፈጠረ ግን እጅህን እንዳትሰጥ! ለሁሉም አንዲት ጥይት አውጥተህ ከጠረጴዛህ ላይ አስቀምጥ፤ ቁርጥ ከሆነ በመጨረሻ በዝች ጥይት ራስህን አጥፋ” ይለዋል፡፡ በዚህ የደጀኔ ምክር የተበረታታው ኮሎኔል ደመቀ፣ “ችግር የለም፡፡ ሽጉጥም አለኝ … የእኔን፣ ያንተን ወንድም እጅ ማንም ወንበዴ አይዛትም! እንደ አጼ ቴዎድሮስ ጥይቴን ጠጥቼ ነው የምሞት!” በማለት መለሰለት፡፡

ደጀኔ እንደነገረኝ፣ ከኮሎኔል የተደወለ ስልክ ሲያይ፣ የሆነ ነገር ተሰምቶታል፤ የፈራው አልቀረም፤ ድረስልኝ የሚል ድምጽ ነበር፡፡ደጀኔም ጣጣ ሳያበዛ፣ ሰሮቃ ላይ ወደ 13 ያህል የታጠቀ ኃይሉን ይዞ ከቀኑ 5 ሰዓት ሲሆን፣ ጉዞ ወደ ጎንደር አደረገ፡፡ እግረ መንገዱን ለሕዝቡ እየተናገረ ስላለፈ ተከታዩ ቁጥር፣ ወደ 40 ደረሰ፡፡ ይህ ኃይል ጎንደር ከተማ ብልኮ አካባቢ ከመኪና ከወረደ በኋላ፣ በፍጥነት በእግሩ ቀሀ ወንዝን ተከትሎ ወደ ኮሎኔሉ ቤት አመራ፡፡ አሁን ጊዜው ወደ 12 ሰዓት እየተጠጋ ነው፡፡

ለዐይን ወደ መያዝ እያመራ ነው፡፡ ደጀኔና ጦሩ ከኮሎኔል ቤት ሲደርሱ፣ አካባቢው በሠራዊት ተወረርዋል፡፡ መደበኛ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል ሁሉም ተፋጠዋል፡፡ሠራዊቱ ኮሎኔሉን አምጡ ብሎ አስቸግሯል፤ ኮሎኔል ደመቀ ደግሞ፣ “እሞታለሁ እንጂ፣ ለፌደራል ኃይል እጄን አልሰጥም!” የሚል አቋም ወስዷል፡፡

“እጄን የምሰጠው ለፌደራል አሳልፈው የማይሰጡኝ ከሆነ፣ ለክልሉ ልዩ ኃይልና ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ብቻ ነው!” ብሏል፡፡ ጊዜ እየሄደ ነው፣ ሀገር ተጨንቋል፡፡ በዚህ መካከል ነበር ደጀኔና ጦሩ የኮሎኔልን ቤት ከቦ አስቸግሮ በነበረው የፌደራል ፖሊስ ላይ የቶክስ እሩምታ የከፈቱበት፡፡

ይህ በደጀኔ ጦር የተከፈተው ማጥቃት ከባድ ስለነበር፣ የመንግሥት የጸጥታ አካለት ጉዳዩን መቋቋም አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ደጀኔና ጦሩ የሚገድለውን ገሎ፣ የሚማረከውን ማርኮ፣ የኮሎኔልን ቤትና አካባቢውን ተቆጣጠረው፡፡ከዚህ በኋላ ጉዳዩ በሽምግልና እንዲቋጭ ስምነት ተደረሰ፡፡ በዚህም መሠረት ደጀኔ ማሩና ኮማንደር ዋኛው (የልዩ ኃይል አመራር) የተወሰኑ ሽማግሌዎችን (በሪ፣ ዘለቀ አሰማራው ... )

በማስከተል፣ ለ2 ቀናት ያህል ከሙሉ ቤተሰቡ ጋር ቤቱን ዘግቶ ሲፋለም ወደ ነበረው ኮሎኔል ደመቀ ቤት፣ “እኛ ሽማግሌዎች ነን! እኔ ደጀኔ ነኝ” እያሉ ድምጻቸውን እያሰሙ ወደ ኮሎኔል ቤት ተጠጉ፡፡ ኮሎኔልም ጦርነቱ እንዲያ ሲበረታ፣ እነ ደጀኔ መጥተው እንደሚሆን ጠርጥሮ ነበርና እኔ “ደጀኔ ነኝ!” እያለ ሲጠጋው አመነ፡፡ ቤቱንም ከፈተላቸው፡፡

ደጀኔና ኮሎኔል ተገናኙ- ሁለቱም የደስታ እንባ አነቡ፡፡ ሽማግሌዎቹና እነ ደጀኔ በፍጥነት በል ተነስ ብለው እጁን ይዘው ከዛች መከረኛ ቤት ሐምሌ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ አወጡት፡፡ሽማግሌዎቹና ደጀኔ፣ የከተማው አስተዳደርና የክልሉ መንግሥት በደረሱበት ስምምነት፣ ኮሎኔል ለፌደራል ተላልፎ አይሠጥም፡፡ ነገር ግን ሕግ አለና ኮሎኔል በክልሉ መንግሥት ኃላፊነት መሠረት፣ በዞኑ ፖሊስ መምሪያ እንዲቆይ ተደረገ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሽ

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar media ጎንደር ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share