Bright future for all

Bright future for all Never gave up

18/10/2022

If you work on yourself from now on, you can beautify the rest of your stay in this world; Stop overthinking the things you can't change!

You cannot change yesterday; Be careful today, then you can beautify your tomorrow. My friend, you are not late for anything, start what you want now

Join bright future for all
19/08/2022

Join bright future for all

14/08/2022

Bright future for all

19/05/2022
15/02/2022

••❥ አንድ ሰማይ ሺህ ከዋክብት ፤ አንድ ህይወት ሺህ ፈተና።

••❥ከዋክብት የጨለመን ሰማይ በብርሃን
ያፈካሉ።

••❥ ፈተናና ችግር ትእግስት ያስተምራሉ።

••❥ ከፈተና ቡኃላ የምታገኘው ውጤት ህይወትህን በደስታ ሐሴት ይሞላታል

09/02/2022

የአለማችን ከባዱ ስራ ማሰብ ነው፤ አጥብቆ የሚያስብ ሰው ህይወት ቀያሪ ውሳኔዎችን ስለሚወስን ስኬታማ ይሆናል። ለዛም ይመስላል ቶማስ ኤዲሰን እንዲህ ያለው "ከመቶ ሰዎች አምስቱ ያስባሉ፣ አስሩ የሚያስቡ ይመስላቸዋል፤ ሰማንያ አምስቱ ግን ከሚያስቡ ቢሞቱ ይመርጣሉ።"
©source inspire Ethiopia

03/02/2022

በተስፋ መሞላት!

ሁሉም ነገሮች የሚሆኑት በምክንያት ነው፤ ስለማትቀይራቸው ነገሮች አብዝተህ አትጨነቅ! እንደዛ እያደረክ ከሆነ ግን ንፋስን እየተከተልክ ነው፤ ስለዚህ የትም አትደርስም! ወዳጄ ሌላውን ትተህ ስለምትቀይረው ነገር ብቻ አስብ፤ ያኔ መንፈስህ ይረጋጋል ጭንቀት ይራገፋል ተስፋ ትሞላና ሁሉን ነገር ትቀይራለህ።
©source inspire Ethiopia

31/01/2022

ባለትዳሮች ወደ መኝታቸው እያመሩ ነው፡፡ በድንገት ባልየው ከቤታቸው ጀርባ ያለውን አትክልት ቤት መብራት
እንዳላጠፋው ትዝ አለውና ተነስቶ ወደዛ አመራ፡፡
ነገር ግን አትክልት ቤቱ ውስጥ ሶስት ሌቦች ሰብረው ገብተው ተመለከተ፡፡
ወዳው ፖሊስ ጣቢያ ደውሎ እርዳታ ጠየቀ፡፡ ኦፊሰሩም "አሁን ሁሉም
ፖሊሶች ለስራ ወጥተዋል፤ ምንም ፖሊስ የለም፡፡ እንደተመለሱ
እልክልሀለው" አለ፡፡
ሰውዬው በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ከ ተወሰኑ ደቂቆች በኀላ መልሶ ደወለ፡፡
"አታስብ ኦፊሰር፤ ሶስቱንም ሌቦች ገደዬ ቆራርጬ ለውሻዬ ሰጥቻቸዋለው፤ ምንም ፖሊስ መላክ አይጠበቅብሕም" አለው፡፡
ብዙም ሳይቆይ በሶስት የፖሊስ መኪና የታጨቁ ከ10 የሚበልጡ ፖሊሶች የሰውዬውን መኖሪያ ቤት ከበቡት፡፡ ኦፊሰሩም አብሮ ነበረ፡፡ ነገር ግን ሌቦቹ እንደተባለው ተገለው ተቆራርጠው ለውሻ ተሰጥተው ሳይሆን ከእነነፍሳቸው ሲሰርቁ ተያዙ፡፡
ኦፊሰር ፡- "ገድዬ ቆራርጬ ለውሻዬ ሰጥቻቸዋለው ያልክ መስሎኝ"
ሰውዬው ፡- "አንተም አሁን ምንም ፖሊስ የለም፤ ሁሉም ስራ ወጥተዋል ያልክ መስሎኝ" አለው፡፡

#ጭብጥ :- ብዙ ግዜ አብዛኞቹ በህይወታችን ያሉ ሰዎች እኛ ስንፈልጋቸው
አናገኛቸውም፤ ነገር ግን በእኛ የውድቀት እና የመከራ ወቅት ያዘኑ መስለው ለማፌዝና ወደ ጥልቁ ስንወርድ ከንፈር ለመምጠጥ በዙሪያችን ይሰበሰባሉ፡፡
ታሞ አንድ ብርጭቆ ውሃ ያልሰጠነውን ሰው ሲሞት አፈር ለመጫንና
ንፍሮውን እየበላን "እንዲህ ነበር እሱ" እያልን የውሸት ድርሰታችን ለማንበብ አንጣደፍ፡፡
እውነት የምንላቸውን ሰዎች ከወደድናቸው፤ ስለ እነሱ የምናስብ ከሆነ ሰው በሚያስፈልጋቸው ወቅት ከጎናቸው እንሁን::

©ሩታ መንግስትአብ

Address

Gondar
44

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bright future for all posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share