21/04/2023
ዳግማዊ ትንሳኤ ምንድን ነው?
በዚች ሰንበት የትንሣኤው ዕለት ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋርያት
በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ
ይሁን»ብሎም ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ
አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ
ከሔደበት ሲመጣ የጌታችንን መነሣትና እንደተገለጸላቸው
በደስታ ሲነግሩት
«በኋላ እናንተ ዐየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ
ግን
«ሰምቼአለሁ» ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር? አይሆንም እኔም
ካላየሁ
አላምንም» በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው
ወዳጆቹን የልብ
ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው
የባሕርይ
አምላክ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ልክ እንደመጀመሪያው
ትንሣኤ ዕለት አበው
ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ
«ሰላም
ለሁላችን ይሁን» በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም
«ያመንክ እንጂ
ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣
የተወጋ ጐኔንም ናና
እይ» ብሎ አሳየው፡፡
እርሱም ምልክቱን በማየቱ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና
አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ «ጌታዬ አምላኬ ብሎ
መስክሮ» አመነ፡፡
- እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ
ለሐዋርያት የተገለጠበት
ዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤
ይከበርበታል፡፡
ዮሐ. 20-24-30