Addisu Melese

Addisu Melese cominicat people with fun move

A daughter is a treasure & a cause of life. Thank you GOD!
29/09/2024

A daughter is a treasure & a cause of life. Thank you GOD!

13/02/2021
23/03/2020

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የግል ፍላጎትን መግታትና አንዱ ለሌላው ማሰብ ይገባዋል ተባለ
*********************************
(ኢፕድ)
የኖቭል ኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እንደ ህብረተሰብ የመቆምና ያለመቆም፤ እንዲሁም የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ውስጥ የሚከትት በመሆኑ፤ የግል ፍላጎታችንን ጨምሮ እንቅስቃሴያችን በሙሉ በተለመደው መልኩ መቀጠል የለበትም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር አሰፋ አድማሴ ገለጹ።
ከዚህ ችግር ለመውጣት ብቸኛ አማራጭም ይላሉ ዶ/ር አድማሴ እያንዳንዳችን በሃላፊነት ስሜት ልንቀሳቀስና አንዱ ለሌላው ሊያስብ ይገባል እንዲሁም ከመንግስት በየጊዜው የሚተላለፉ መልዕክቶችን በመከታተል ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል።
ዶ/ር አሰፋ አድማሴ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነውን የኖቭል ኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እያንዳንዱ ግለሰብ ለጊዜው የግል ፍላጎቱን ገታ በማድረግና ቆም ብሎ በማሰብ እያንዳንዷን እንቅስቃሴችንን ጥንቃቄ ልናጤናት እንደሚገባ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የገጠመን ችግር በጣም አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ውስብስብና በእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ወረርሽኙ ቢከሰት ለመቆጣጠር አዳጋች መሆኑን የገለፁት ዶክተር አሰፋ፤ ወረርሽኙ ቢከሰት በጤና፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ እንቅስቃሴያችን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ጥንቃቄ ሳይለየን የግል ፍላጎቶቻችንን ለጊዜው ገታ የምናደርግበት ፈታኝ ወቅትነው ሲሉ ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ተከትሎ የገጠመን ችግር ፈታኝ መሆኑን ያስታወሱት ዶክተር አሰፋ፤ የችግሩ አሳሳቢነት እንደ ህብረተሰብ የመቀጠል እና ያለመቀጠል ጥያቄ በመሆኑ የግለሰቦች የግል ፍላጎት መገታት አለበት እንጂ እያንዳንዳችን የግል ሀብት የምናጋብስበት እና የተለያዩ ፍላጎቶችን የምናሟላበት ወቅት አይደለም ብለዋል።

23/03/2020

እነዚህን በምንነካበት ሰሀት እጃችን በሳሙና በመታጠብ ወይም ሰኒታይዘር በመጠቀም እራስወንና ህብረተሰቡን ከተላላፊው እና ከአደገኛው ገዳይ በሽታ ኮሮና ቫይረስ
( COVID 19 )ይከላከሉ የምታገኙትን ጠቃሚ መረጃ ለጓደኞቻችሁ ሸር አድርጉ

22/02/2020

ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ ቀን
ጠባቂዎቻቸውን ለምን በእግራችን ወጣ ብለን
አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው
ወጡ።
አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው
ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው
ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ
ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ።
ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። ሰውዬው እየተመገበ
እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ
መሃል አንዱ "ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነው
መሰለኝ ።
እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር"ይላቸዋል ማዴባም "አይደለም!
ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር ። ብዙ ግዜ
ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ
እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ
ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናብኝ ነበር" አሁን
ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው"
ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም

ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም !!!
ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና!

05/11/2019

Ethio 360 Media
የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓለም አደባባዮች የሃፍረት ሸማ
እንዲላበስ ተደርጓል።-የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ
ሕብረት
(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 24/2012)የኢትዮጵያ ሕዝብ
በዓለም አደባባዮች የሃፍረት ሸማ እንዲላበስ ተደርጓል
ሲል የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት አስታወቀ።
ሕብረቱ “በማራቶን ደጋግመን ያሸነፍነውን ያህል፣ ሰሞኑን
በጭካኔ ሬከርድ ሰብረናል!” በሚል ርዕስ ሰሞኑን
በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ ከ80 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን
ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የቀጠፈውን ክስተት አስመልክቶ
መግለጫ አውጥቷል።
ሕብረቱ ለኢትዮ 360 በላከው መግለጫ እንዳለው
ኢትዮጵያ ሃገራችን ፈታኝ ወቅት ላይ ትገኛለች።
ሕወሃትን ለማውረድ ብዙ መስዋእትነት የተከፈለበት
ለውጥም በመቀልበስ ላይ መሆኑ ሃሜት ሳይሆን ሃቅ ነው
ብሏል ሕብረቱ በመግለጫው።
ጁሃር መሃመድ ጥበቃዬ ሊነሳ ነው ድረሱልኝ ብሎ በደረቅ
ለሊት ለተከታዮቹ ያደረገው ጥሪ ንፁህና ሰላማዊ
ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን እንደበግ በገጀራና በቆርቆሮ
እንዲታረዱ፣ ቤንዚን ተርከፍክፎ እንዲቃጠሉ፤ በድንጋይ
እንደእባብ ተቀጥቅጠው እንዲገደሉ ምክንያት ሆኗል
ይላል።
የጀዋር መሐመድ ተከታዮች የገደሏቸው በአብዛኛው
“ነፍጠኛ” ከሚሉት የአማራ ወገን ቢሆኑም ይላል
መግለጫው ከጋሞ፣ ከጉራጌ እና ከዶርዜ ማህበረሰብ፣
እንዲሁም ሙስሊምም ክርስቲያንም ይገኙበታል ሲል
ያስቀምጣል።--ቀሳውስት ታርደዋል፣ ቤተክርስቲያንና
መስጊድ፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ተቋማት
መቃጠላቸውም እንዲሁ።
ሕብረቱ የተከሰተው ጭካኔ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን
የዓለምን ሕዝብ ድንጋጤ ላይ ጥሎት ከርሟል ብሏል።
ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሰላም
የኖቤል ሽልማት ማሸነፍ አገራችን በዓለም ጋዜጦች
በአድናቆት ሲዘገብላት እኛ ኢትዮያውያኖች በያለንበት
አንገታችንን ቀና አድርገን የነበርነውን ያህል ሰሞኑን
በተከሰተው ጭካኔ ደግሞ አንገታችንን እንድንደፋ
ተደርገናል ሲል ይናገራል።
ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብም በቀየው በተከሰተው ኢሰብአዊ
ድርጊት ከሌላው ወገኑ ጋር እንደተሸማቀቀና በእጅጉ
እንዳዘነ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም ሲል ተናግሯል።
አንድ መረሳት የሌበትና ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር
ይላል ንቅናቄው በመግለጫው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትናንት
የልጆቹን ደም ገብሮ ሕወሃትን ያስወገደው የባሰ ዘመን
ለማስተናገድ አይደለም።
ሌላው አሳዛኝና አሳፋሪ ክስተት ደግሞ ይላል ሕብረቱ
የወገኖቻችን እልቂት ሳይቆምና እሬሳቸው ስይነሳ፣
የአንዳንድ ድርጅት መሪዎች ጀዋር መሐመድን በቪላው
ውስጥ ተገኝተው እጅ ሲነሱትና ሲያባብሉት ማየት ነው።
ሕብረቱ አሁንም ቢሆን ይላል ሕዝብን በማበጣበጥ ሕግ
የሚጥሱትን መንግሥት ፈጥኖ በመያዝ ሕጋዊ እርምጃ
እንዲወሰድባቸው ካላደረገ የዜጎቹን ክብርና እምነት
ያጣል።- ሌሎች ሕግ እንዳያከብሩ ያበረታታል ሲል
ገልጿል።
ሕዝብ ለመንግሥት ሃላፊነት የሰጠው ከሁሉም በላይ
የሕግን የበላይነት እዲያስከብርለት ነው። ስለዚህ
አጥፌዎች ያላቸው ጡንቻ ተፈርቶ ፍትህ መዘግየትና
መጓደል የለባትም ሲልም ያስጠነቅቃል የኢትዮጵያ
ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት ።
ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት መንግሥት ጀዋር መሐመድንና
ሕዝቡን የፈጁትን ተከታዮቹን ለቃቅሞ ለፍርድ ከማቅረብ
ሌላ አማራጭ የለውም ብሏል መግለጫው።
እንዲሁም በየጊዜው ከፋፋይ ዘር ተኮር መልዕክቶችን
በማስተጋባት ሕዝቡን ለማናቆር በስፋት ቅስቀሳ
የሚያደርጉትን አቶ በቀለ ገርባን፣ ሕዝቅኤል ጋቢሳን፣
ፀጋዬ አራርሳን፣ “ፕሮፌሰር” ገመቹን መንግሥት በሕግ
አብሮ ተጣያቂ እንዲያደርጋቸው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች
ንቅናቄ ሕብረት በመግለጫው አሳስቧል።
ሊሰመርበት የሚገባው ሕዝቡ በማንነቱ ምክንያት ካደገበት
ቀዬው መፈናቀል አንገፍግፎታል፤ በየጊዜው መታረድ
በቅቶታል።
በማንነቱ ምክንያት በቡራዩ፣ በናዝሬት፣ በአምቦ፣ በዶዶላ፣
በሰበታ በሲዳማ እና በሌሎችም የሃገሪቱ ክፍሎች
የታረደው ህዝብ ዛሬ ላይ መንግሥት ይደርስልኛል በሚል
እሳቤ እንደገና በዝምታ የሚታረድ አይደለም ይላል
ሕብረቱ።
ሕዝቡ በሚመስለውና በእጁ ባለው እራሱን መከላከል
ከጀመረ አሸናፊው በውል የማይለይና ማቆሚያ የሌለው
እልቂት ሊከሰት ይችላል ሲል ሕብረቱ ስጋቱን ገልጿል።
ይህ ቃል ካልተጠበቀና ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው
ካልቀረቡ ሕዝቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያለው እምነት
በይበልጥ እየተሸረሸረ ከመሄዱም በላይ በወገንተኛነት
እንዳይፈርጃቸው ሊያግደው የሚችል ምክንያት ሊኖር
አይችልም።-ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ
የሚመለከተው አካል አስቸኳይ የሚባለውን ርምጃ
ወስደው ሃገሪቱን የማረጋጋት ሃላፊነት አለባቸው ብሏል።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት በመግለጫው
ማጠቃለያ ለሞቱና ለተጎዱ ቤተሰቦች መጽናናትን
ተመኝቶ፣ ፍትህ ለታረዱ ወገኖቻችን ይሁን ሲል ጥሪውን
አቅርቧል።

09/10/2019

ህሊና ደሳለኝ
"እርሙን ተደፋፍሮ ፣ አንድ ቀን ቢዋጋ
አላስቀምጥ አለን
በየ መድረኩ ላይ ፣ ያንኑ እያወጋ"
ያለውን ባናውቅም
እኛም እንላለን
"ነፍጠኛ" ሲባል ፣ ወይ
እነሱም ይላሉ ፣ " ወዬ " ሲባል "መንጋ"
ሳይጠሩት አቤት ባይ
በመንጋ መሃል ሀገር ተሰንጋ
እንዴት ብሎ ይንጋ?
የመንጋ ምስ

19/01/2019

መልካም የጥምቀት ባህል ለመላው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች

29/11/2018

★በተለያየ አጋጣሚ የምናገኛቸው 60 ምህጻረ ቃል እና
ፍቻቸውን
√ጠቃሚ ስለሆነ ሼር ያድርጉት።
1.) GOOGLE : Global Organization Of
Oriented Group Language Of Earth .
2.) YAHOO : Yet Another Hierarchical
Officious Oracle .
3.) WINDOW : Wide Interactive Network
Development for Office work Solution
4.) COMPUTER : Common Oriented Machine
Particularly United and used under Technical
and Educational Research.
5.) VIRUS : Vital Information Resources
Under Siege .
6.) UMTS : Universal Mobile
Telecommunications System .
7.) AMOLED: Active-matrix organic light-
emitting diode
8.) OLED : Organic light-emitting diode
9.) IMEI: International Mobile Equipment
Identity .
10.) ESN: Electronic Serial Number .
11.) UPS: uninterrupted power supply .
12). HDMI: High-Definition Multimedia
Interface
13.) VPN: virtual private network
14.) APN: Access Point Name
15.) SIM: Subscriber Identity Module
16.) LED: Light emitting diode.
17.) DLNA: Digital Living Network Alliance
18.) RAM: Random access memory.
19.) ROM: Read only memory.
20) VGA: Video Graphics Array
21) QVGA: Quarter Video Graphics Array
22) WVGA: Wide video graphics array.
23) WXGA: Wide screen Extended Graphics
Array
24) USB: Universal serial Bus
25) WLAN: Wireless Local Area Network
26.) PPI: Pixels Per Inch
27.) LCD: Liquid Crystal Display.
28.) HSDPA: High speed down-link packet
access.
29.) HSUPA: High-Speed Uplink Packet
Access
30.) HSPA: High Speed Packet Access
31.) GPRS: General Packet Radio Service
32.) EDGE: Enhanced Data Rates for Global
Evolution
33.)NFC: Near field communication
34.) OTG: on-the-go
35.) S-LCD: Super Liquid Crystal Display
36.) O.S: Operating system.
37.) SNS: Social network service
38.) H.S: HOTSPOT
39.) P.O.I: point of interest
40.)GPS: Global Positioning System
41.)DVD: Digital Video Disk / digital versatile
disc
42.)DTP: Desk top publishing.
43.) DNSE: Digital natural sound engine .
44.) OVI: Ohio Video Intranet
45.)CDMA: Code Division Multiple Access
46.) WCDMA: Wide-band Code Division
Multiple Access
47.)GSM: Global System for Mobile
Communications
48.)WI-FI: Wireless Fidelity
49.) DIVX: Digital internet video access.
50.) .APK: authenticated public key.
51.) J2ME: java 2 micro edition
53.) DELL: Digital electronic link library.
54.)ACER: Acquisition Collaboration
Experimentation Reflection
55.)RSS: Really simple syndication
56.) TFT: thin film transistor
57.) AMR: Adaptive Multi- Rate
58.) MPEG: moving pictures experts group
59.)IVRS: Interactive Voice Response System
60.) HP: Hewlett Packard

Address

Maraki
Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addisu Melese posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share