30/08/2024
አንድ ግዙፍ የሆነ መርከብ ሞተሩ ተበላሽቶ ማንም ሊጠግነው ስላልቻለ ከ40 ዓመት በላይ ልምድ ያለው መካኒካል መሐንዲስ ተፈልጎ ይገኝና እንዲሰራው ይጠየቃል።
መሃንዲሱም ከላይ እስከ ታች ሞተሩን በጥንቃቄ መረመረው።
ሁሉንም ነገር ካየ በኋላ ቦርሳውን አውርዶ ትንሽ መዶሻ አወጣ። ሞተሩ ላይ የሆነ ነገር በእርጋታ መታ መታ አደረገ።
ብዙም ሳይቆይ ሞተሩ እንደገና መስራት ጀመረ። ሞተሩ ተስተካከለ!
ከዚያም መሐንዲሱ የመርከቡን ሞተር ለጠገነበት የሚያስፈልገውን አጠቃላይ ክፍያ 20,000 ዶላር እንደሆነና ክፍያው እንዲፈጸምለት ለመርከቡ ባለቤት ጥያቄ አቀረበ።
የመርከቡ ባለቤት የተጠየቀውን የገንዘብ መጠን ሲሰማ በድንጋጤ ''ምን?!" አለ።
'’ይህን ያህል ከፍተኛ ዋጋ የሚያስጠይቅ ምንም አላደረክም። ዝርዝር ሂሳብ ስጠን።" በማለት መሃንዲሱን መለሰለት።
መሃንዲሱም እንዲህ አለ ‘’መልሱ ቀላል ነው:
በመዶሻ መታ መታ ያደረኩበት ዋጋ= 2 ዶላር ነው።
ነገር ግን የት እንደምመታው እና ምን ያህል መምታት እንዳለብኝ ላወኩበት=19,998 ዶላር’’ በማለት አብራራ።
ክፍያውም ወዲያው ተፈፀመለት።
የዚህ ታሪክ ዋና መልእክት:-የአንድን ሰው ችሎታ እና ልምድ የማድነቅ አስፈላጊነት ነው። ምክንያቱም ይህ ችሎታና ልምድ የበርካታ አመታት የትግል፣ የሙከራዎች እና የእንባዎች ውጤት ነው።
አንድ ሰው በ30 ደቂቃ ውስጥ ሥራ ከሠራ፣ በ30 ደቂቃ ውስጥ እንዴት መሥራት እንዳለበት እየተማረ 20 እና ከዚህ በላይ ዓመታትን ስላሳለፈ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።
ክፍያው ለደቂቃዎች ለተከናወነ ስራ ሳይሆን ለዓመታት የተከፈለ የህይወት ዘመን ጥረት ውጤት እንደሆነ እንወቅ!
አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ ያድርጉት🙏
የገፃችን Lighthouse-Academy of Success/የስኬት አካዳሚ/ ቤተሰብ ይሁኑ
የላቁ እይታዎች!